የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 11/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ!
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ያላቸው እውነተኛ ተስፋ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ትንሣኤ—ለማንና የት?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 11/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በእርግጥ ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን አስነስቷል?

ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር እንዲወጣ በመጣራት ከሞት ሲያስነሳው

ኢየሱስ ለአራት ቀናት ሞቶ የቆየውን አልዓዛርን ከሞት አስነስቶታል

ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር እንዲወጣ በመጣራት ከሞት ሲያስነሳው

ኢየሱስ ለአራት ቀናት ሞቶ የቆየውን አልዓዛርን ከሞት አስነስቶታል

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን እንዳስነሳ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን እንዳስነሳ የሚገልጹት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ተረት አይደሉም፤ የተፈጸሙበት ጊዜም ሆነ ቦታ በትክክል ተጠቅሷል። ለምሳሌ ያህል፣ በ31 ዓ.ም. የበጋ ወቅት ላይ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን አስከትሎ ከቅፍርናሆም ወደ ናይን እየተጓዘ ነበር። ወደ ከተማዋ ሲደርሱ ብዙ ሕዝብ ከከተማዋ ሲወጣ አገኙ። በዚህ ወቅት ትንሣኤ እንደተፈጸመ በሚናገረው ታሪክ ላይ እምነት መጣል ትችላለህ፤ ምክንያቱም ይህ ታሪክ የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፤ በተጨማሪም ሁኔታው ሲፈጸም የተመለከቱ በርካታ የዓይን ምሥክሮች ነበሩ።—ሉቃስ 7:11-15⁠ን አንብብ።

በተጨማሪም ኢየሱስ ለአራት ቀናት ሞቶ የቆየውን ወዳጁን አልዓዛርን ከሞት አስነስቷል። ኢየሱስ ይህንንም ተአምር የፈጸመው ብዙ የዓይን ምሥክሮች ባሉበት በመሆኑ ትንሣኤው ስለ መፈጸሙ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።—ዮሐንስ 11:39-45⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ያስነሳው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ያስነሳው ርኅሩኅ ስለነበረ ነው። በተጨማሪም ይህን ያደረገው የሕይወት ምንጭ የሆነው አባቱ በሞት ላይ ሥልጣን እንደሰጠው ለማሳየት ነው።—ዮሐንስ 5:21, 28, 29⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ የሞቱ ሰዎችን ማስነሳቱ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጠው ተስፋ እንደሚፈጸም እንድንተማመን ያደርገናል። ኢየሱስ ስለ እውነተኛው አምላክ ምንም የማያውቁ ዓመፀኛ ሰዎችን ጨምሮ ሌሎች እጅግ ብዙ ሰዎችን ከሞት ያስነሳል። እነዚህ ሰዎች ስለ ይሖዋ አምላክ የመማርና እሱን እንደሚወድዱ ማሳየት የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ።—የሐዋርያት ሥራ 24:15⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 7 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ