የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 10/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ድህነትን ለማስወገድ የተደረጉ ጥረቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ለድሆች የሚሆን ምሥራች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ድህነት
    ንቁ!—2015
  • ድህነት ለዘለቄታው ይወገድ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 10/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ድህነት የማይኖርበት ዓለም ይመጣል?

አንዲት ሴት ባዶ ሳህን ይዛና ትንሽ ልጅን አቅፋ

አምላክ ድህነት የሌለበት ዓለም የሚያመጣው እንዴት ነው?—ማቴዎስ 6:9, 10

የከፋ ድህነት በሚያስከትለው የምግብ እጥረትና በሽታ ሳቢያ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይሞታሉ። ምንም እንኳ ሀብታም የሆኑ አገሮች ቢኖሩም አብዛኛው የሰው ዘር ግን አሁንም በድህነት እየማቀቀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ድህነት ከሰው ልጆች ጋር የኖረ ችግር እንደሆነ ይናገራል።—ዮሐንስ 12:8⁠ን አንብብ።

ድህነትን ለማጥፋት መላውን ዓለም የሚገዛ አንድ መንግሥት ያስፈልጋል። ይህ መንግሥት በምድር ላይ ያለው ሀብት ለሁሉም እኩል እንዲዳረስ ለማድረግና ለድህነት ዋነኛ መንስኤ የሆነውን ጦርነትን ለማስወገድ ኃይል ያለው ሊሆን ይገባል። አምላክ እንደዚህ ዓይነት መንግሥት ለማምጣት ቃል ገብቷል።—ዳንኤል 2:44⁠ን አንብብ።

ድህነትን ማጥፋት የሚችለው ማን ነው?

አምላክ ልጁን ኢየሱስን በመላው የሰው ዘር ላይ እንዲገዛ ሾሞታል። (መዝሙር 2:4-8) ኢየሱስ ድሆችን ከችግራቸው የሚገላግላቸው ከመሆኑም ሌላ ጭቆናንና ዓመፅን ያጠፋል።—መዝሙር 72:8, 12-14⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ በትንቢት የተነገረለት “የሰላም መስፍን” እንደመሆኑ መጠን በዓለም ላይ ሰላምና ደህነት ያሰፍናል። ከዚያም በምድር ላይ ያለ ሁሉ የግል ንብረቱ በሆነ ቤት ውስጥ የሚኖር ሲሆን አርኪ ሥራና የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል።—ኢሳይያስ 9:6, 7⁠ን እና 65:21-23⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ