የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 11/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ!
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ትንሣኤ ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 11/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሞቱ ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ?

በገነት ውስጥ ሰዎች ከሞት የተነሱትን ሲቀበሉ

የሕይወት ፈጣሪ መልሶ ሕይወትን መስጠት ይችላል

የሕይወት ምንጭ ይሖዋ አምላክ ነው። (መዝሙር 36:9) ታዲያ ፈጣሪ የሞቱ ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ያቅተዋል? አምላክ ወደፊት ይህን እንደሚፈጽም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 24:15⁠ን አንብብ።) ሆኖም አምላክ እንዲህ የሚያደርገው ለምንድን ነው?

ፈጣሪያችን ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ ዓላማው ነው። (ዘፍጥረት 1:31፤ 2:15-17) አሁንም ቢሆን ሰዎች ለዘላለም እንዲኖሩ ይፈልጋል። በአሁኑ ጊዜ ሕይወታችን በመከራ የተሞላና በአጭሩ የሚቀጭ በመሆኑ በጣም ያዝናል።—ኢዮብ 14:1, 14, 15⁠ን አንብብ።

ከሞት የሚነሱ ሰዎች የሚኖሩት የት ነው?

አምላክ ሰውን የፈጠረው በሰማይ እንዲኖር ነው? በፍጹም። አምላክ በሰማይ እንዲኖሩ የፈጠረው መላእክትን ነው። ሰዎችን የፈጠረው በምድር ላይ እንዲኖሩ ነው። (ዘፍጥረት 1:28፤ ኢዮብ 38:4, 7) ይህንን በአእምሮህ በመያዝ እስቲ ኢየሱስ ከሞት ስላስነሳቸው ሰዎች አስብ። ከሞት ያስነሳቸው ሰዎች የኖሩት እዚሁ ምድር ላይ ነው። ወደፊትም ቢሆን ትንሣኤ የሚያገኙ አብዛኞቹ ሰዎች የሚኖሩት በምድር ላይ ነው።—ዮሐንስ 5:28, 29⁠ን እና 11:44ን አንብብ።

ሆኖም አምላክ እሱ የመረጣቸው የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በሰማይ መኖር እንዲችሉ መንፈሳዊ አካል ይዘው ከሞት እንዲነሱ ያደርጋል። (ሉቃስ 12:32፤ 1 ቆሮንቶስ 15:49, 50) በሰማይ ለመኖር ትንሣኤ የሚያገኙ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ነገሥታት ሆነው ምድርን ይገዛሉ።—ራእይ 5:9, 10⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 7 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ