የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp17 ቁጥር 1 ገጽ 4
  • መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር የምችለው እንዴት ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር የምችለው እንዴት ነው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ለማንበብ ትጋ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ማንበብና ያነበቡትን ማስታወስ የሚቻልበት መንገድ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ መጠቀም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
wp17 ቁጥር 1 ገጽ 4

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብን አስደሳች ማድረግ

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር የምችለው እንዴት ነው?

አንዲት ሴት መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበቧ በፊት ስትጸልይ

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ አስደሳች እንዲሆንልህና ከንባብህ ይበልጥ ጥቅም ማግኘት እንድትችል ምን ሊረዳህ ይችላል? ብዙ ሰዎች ውጤታማ ሆነው ያገኟቸውን አምስት ነጥቦች ተመልከት።

ለማንበብ አመቺ የሆነ ቦታ ምረጥ። ጸጥ ያለ ቦታና ጊዜ ለማግኘት ሞክር። በምታነበው ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንድትችል ሐሳብ የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግድ። በቂ ብርሃንና ንጹሕ አየር ያለበት ቦታ ሆነህ ማንበብህ ከንባብህ የተሻለ ጥቅም እንድታገኝ ሊረዳህ ይችላል።

አእምሮህን ክፍት አድርገህ አንብብ። መጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ ካለው አባታችን ያገኘነው ስጦታ ነው፤ አንድ ልጅ አፍቃሪ ከሆነ ወላጁ ለመማር እንደሚጓጓ ሁሉ አንተም እንዲህ ዓይነት ዝንባሌ ይዘህ ማንበብህ ከንባብህ የተሻለ ጥቅም እንድታገኝ ይረዳሃል። አምላክ እንዲያስተምርህ ከፈለግክ በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ ያሉህን አሉታዊ አመለካከቶች ከአእምሮህ ማውጣት አለብህ።—መዝሙር 25:4

ማንበብ ከመጀመርህ በፊት ጸልይ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የአምላክ ሐሳብ ነው፤ በመሆኑም ሐሳቡን መረዳት እንድንችል የአምላክ እርዳታ የሚያስፈልገን መሆኑ አያስገርምም። አምላክ ‘ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጣቸው’ ቃል ገብቷል። (ሉቃስ 11:13) መንፈስ ቅዱስ የአምላክን አስተሳሰብ እንድትረዳ ያግዝሃል። በጊዜ ሂደት፣ ‘የአምላክን ጥልቅ ነገሮችም’ ሳይቀር መረዳት እንድትችል አእምሮህን ይከፍትልሃል።—1 ቆሮንቶስ 2:10

የምታነበውን ነገር ለመረዳት ሞክር። የተወሰኑ ገጾችን ለመሸፈን ብቻ ብለህ አታንብብ። የምታነበውን ነገር ለማስተዋል ጥረት አድርግ። ራስህን እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቅ፦ ‘በዘገባው ላይ የተጠቀሰው ግለሰብ ምን ጥሩ ባሕርያት አሉት? እነዚህን ባሕርያት በሕይወቴ ውስጥ ማንጸባረቅ የምችለው እንዴት ነው?’

ግብ አውጣ። መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ ለራስህ አንድ ጠቃሚ ትምህርት ለማግኘት ግብ አድርግ። ለምሳሌ ስለ አምላክ ይበልጥ ለማወቅ ግብ አድርገህ ልታነብ ትችላለህ። አሊያም ደግሞ የተሻለ ሰው ወይም ባል መሆን የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለመማር ግብ ማውጣት ትችላለህ። ከዚያም ያወጣኸው ግብ ላይ ለመድረስ የሚረዱህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ምረጥ።a

እነዚህ አምስት ነጥቦች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እንድትጀምር ይረዱሃል። ሆኖም ንባብህ ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? የሚቀጥለው ርዕስ በዚህ ረገድ የሚረዱህን አንዳንድ ሐሳቦች ይዟል።

a ያወጣኸው ግብ ላይ ለመድረስ የሚረዳህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የቱ እንደሆነ ካላወቅክ የይሖዋ ምሥክሮች ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው።

ከንባብህ ይበልጥ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

  • ሳትጣደፍ ረጋ ብለህ አንብብ

  • በምታነበው ነገር ተመሰጥ፤ ማለትም በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ጥረት አድርግ

  • እያንዳንዱ ጥቅስ በዙሪያው ካለው ሐሳብ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ለማስተዋል ሞክር

  • ከምታነበው ነገር ትምህርት ለማግኘት ሞክር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ