የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp17 ቁጥር 3 ገጽ 3
  • ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚገልጸው ራእይ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚገልጸው ራእይ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አራቱ ፈረሰኞች—እነማን ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • መግቢያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • አራት ፈረሰኞች እየጋለቡ ናቸው!
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
  • የመንግሥቲቱ ፈረሰኛ በመጋለብ ላይ ነው
    “መንግሥትህ ትምጣ”
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
wp17 ቁጥር 3 ገጽ 3
አራቱ ፈረሶች ጋለቡ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | የአራቱ ፈረሰኞች ግልቢያ​—በሕይወትህ ላይ ለውጥ ያመጣል?

ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚገልጸው ራእይ

በፍጥነት የሚጋልቡት አራቱ ታላላቅ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸው አእምሯችን ላይ የሚፈጥሩት ምስል ጥርት ያለ ከመሆኑ የተነሳ በዓይናችን የምናያቸው ያህል ሆኖ ይሰማናል! የመጀመሪያው ፈረስ ነጭ ነው፤ ጋላቢው ደግሞ ክብር የተጎናጸፈ አዲስ ንጉሥ ነው። ከእሱ በኋላ ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ፈረስ የመጣ ሲሆን ጋላቢው ከምድር ሁሉ ላይ ሰላምን እንዲወስድ ሥልጣን ተሰጥቶታል። ከዚያም ሦስተኛ ፈረስ እየጋለበ መጣ፤ ቀለሙ ጥቁር ሲሆን በእሱ ላይ የተቀመጠው ጋላቢ በእጁ ሚዛን ይዟል፤ የምግብ እጥረት እንደሚኖር የሚገልጽ አሳዛኝ መልእክት ተሰማ። አራተኛው ፈረስ ግራጫ ሲሆን በሽታና ሌሎች ቀሳፊ ነገሮች እንደሚከሰቱ ያመለክታል፤ የዚህ ፈረስ ጋላቢ ሞት ነው። ከኋላው ደግሞ መቃብር የሞቱትን ሰዎች እየዋጠ ይከተለዋል።—ራእይ 6:1-8

“ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ አራቱ ፈረሰኞች ሳነብ በጣም ፈርቼ ነበር። የፍርድ ቀን እየመጣ እንደሆነ ተሰማኝ፤ እኔ ደግሞ ለዚያ ቀን ስላልተዘጋጀሁ አልተርፍም ብዬ አስቤ ነበር።”—ክሪስታል

“የተለያየ ቀለም ያላቸውን ፈረሶች ስለሚጋልቡ አራት ፈረሰኞች የሚገልጸው ራእይ በጣም አስደንቆኝ ነበር። የራእዩን ትርጉም ስረዳ ሁሉም ነገር ግልጽ ሆነልኝ።”—ኤድ

አንተም በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ስለተጠቀሱት አራት ፈረሰኞች ስታስብ እንደ ክሪስታል አሊያም ደግሞ እንደ ኤድ ዓይነት ስሜት ተሰምቶህ ይሆናል። ስለ እነዚህ ፈረሰኞች ግልቢያ የሚናገረው ራእይ የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ መጽሐፍ በሆነው በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱት በብዙዎች ዘንድ የሚታወቁ ዘገባዎች መካከል አንዱ ነው። የዚህን ራእይ ትርጉም መረዳትህ በግለሰብ ደረጃ የሚጠቅምህ እንዴት ነው? በዚህ ትንቢታዊ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጹትን ነገሮች ማንበብ፣ በመጽሐፉ ላይ ከሰፈሩት ሐሳቦች ትምህርት መቅሰምና የተማርነውን ነገር ተግባራዊ ማድረግ እውነተኛ ደስታ እንደሚያስገኝልን አምላክ ተናግሯል።—ራእይ 1:1-3

ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚገልጸው ራእይ አንዳንዶችን የሚያስፈራቸው ቢሆንም አምላክ ይህን ራእይ የገለጠው ሰዎችን ለማስፈራራት ፈልጎ አይደለም። እንዲያውም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይህ ራእይ እምነት የሚያጠናክርና ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ የሚፈነጥቅ እንደሆነ ተገንዝበዋል። አንተም ከዚህ ራእይ ተመሳሳይ ጥቅም ማግኘት ትችላለህ። በመሆኑም ማንበብህን እንድትቀጥል እናበረታታሃለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ