“ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
በሃማስ፦ 1,294 የደረሱት አስፋፊዎች በ“መለኮታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባቸው ላይ 3,149 ሰዎች ሲገኙ 38 ሰዎች ደግሞ ሲጠመቁ ማየታቸው አስደስቷቸዋል።
ብራዚል፦ በ1993 የአገልግሎት ዓመት በሐምሌ ወር 348,634 የደረሰ ለአራተኛ ጊዜ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች።
ጋቦን፦ በ1993 የአገልግሎት ዓመት በሐምሌ ወር 1,332 የደረሰ አምስተኛውን ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች። እነዚህ ቀናተኛ አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት በአማካይ 17.8 ሰዓት አሳልፈዋል፣ 22,658 ተመላልሶ መጠየቅ አድርገዋል፤ እንዲሁም 4,280 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርተዋል።
ኬንያ፦ የማሊንዲ የመንግሥት አዳራሽ 213 ተሰብሳቢዎች በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን ተመርቋል።
ታንዛንያ፦ መስከረም 4 ቀን የዳሬሰላም ማዕከላዊ ጉባኤ የመንግሥት አዳራሽ የምረቃ ፕሮግራም ሲካሄድ በጠቅላላው 330 ተሰብሳቢዎች ተገኝተው ነበር።