የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/94 ገጽ 2
  • ንጽሕና አምላክን ያስከብራል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ንጽሕና አምላክን ያስከብራል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ንጹሕ የሆኑ ሰዎችን ይወዳል
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • ንጽሕና—ትክክለኛ ትርጉሙ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ንጽሕና ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ንጽሕና አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 4/94 ገጽ 2

ንጽሕና አምላክን ያስከብራል

1 የሙሴ ሕግ ንጽሕና እንዲጠበቅ የሚያዙ ጥብቅ ደንቦችን ይዞ ነበር። እነዚህ ደንቦች እስራኤላውያን አካላዊና መንፈሳዊ ንጽሕናቸውን የሚጠብቁ ከሌሎች አህዛብ ሁሉ የተለዩ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። (ዘሌ. 11:35, 36፤ 15:1–11፤ ኢሳ. 52:11) ይህ የንጽሕና አቋም ለአምላክ ክብር አምጥቷል፤ ለሕዝቡም ጤንነት አስተዋጽኦ አድርጓል።

2 ዛሬም ቢሆን ንጽሕና የይሖዋ ሕዝቦች ከሌሎቹ ሰዎች የሚለዩበት ምልክት ነው። የይሖዋ ሕዝቦች በቡድን ደረጃ ተለይተው የሚታወቁት በንጽሕናቸው ቢሆንም እያንዳንዳችን በግለሰብ ደረጃ በንጽሕናችን ተለይተን እንታወቃለንን? ለሥርዓታማነትና ለግል ንጽሕና ምን ያህል የምንጨነቅ መሆናችን ይሖዋ ያወጣቸውን ደንቦች ምን ያህል እንደምናደንቅ ያሳያል።

3 ስለ ቤታችን ሁኔታስ ምን ማለት ይቻላል? ሰዎች የምናደርስላቸውን መልእክት እንዲጠሉት ምክንያት ሆኗልን? የራሳችን ቤት ዝርክርክና የግቢው ሣር በጣም ያደገ ወይም አረም የሞላበት ሆኖ እያለ ምድር ወደ ገነትነት ትለወጣለች እያልን ብንናገር አንድ ሰው የምንናገረውን ከልብ የምናምንበት ስለመሆኑ ሊጠራጠር አይችልምን? ንጹሕ ባልሆኑ ልማዶች የተነሣ ቤታችን የተዝረከረከ ወይም ደስ የማይል ጠረን ያለው ቢሆን “በአምላክ መንግሥት ለሚቋቋመው አዲስ ሥርዓት የሚስማማ ጥሩ የንጽሕና ልማድና ጠባይ” ኮትኩተናል ሊባል ይቻላልን? — አገልግሎታችን ገጽ 130–1 (በአማርኛው ገጽ 68–69)

4 ለመስክ አገልግሎት የምንጠቀምበት መኪናስ? የውስጡና የውጪው ጽዳት የተጠበቀ በመሆኑ ሰዎች ለስብከት ሥራችን የሚሰጡትን ትኩረት የማይቀንስ ነውን? ልብሳችን፣ መጽሐፍ የምንይዝበት ቦርሳና አጠቃላይ የሰውነታችን ሁኔታስ እንዴት ነው? ንጹሕ፣ ያልተዝረከረኩና ቅር የማያሰኙ ናቸውን? አዘውትረን ገላችንን በመታጠብና ልብሳችንን በማጠብ ራሳችንን በንጽሕና መያዛችን ተገቢ ነው።—መግ 11–110 ገጽ 15-20

5 አንድ ወንድም የግል ወይም የአካባቢውን ንጽሕና በመጠበቅ ረገድ ግድየለሽ ከመሆኑ የተነሳ በጉባኤው ላይ ነቀፋ ቢያመጣስ? ምናልባት በዕድሜው ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ፍቅራዊ እርዳታ ያስፈልገው ይሆናል። ነገሩ እንዲህ ከሆነ እርሱን መርዳት ደግነት ይሆናል። አንድ ሰው ንጽሕናውን የመጠበቅ ችግር እያለበት ላይገነዘበው ስለሚችል በደግነት መንፈስ ምክር መስጠቱ ሁኔታውን እንዲያስተካክል ሊገፋፋው ይችል ይሆናል። ንጽሕናቸውን በመጠበቅ በኩል ምንጊዜም ጥሩ ምሳሌ የማይሆኑ ግለሰቦች በጉባኤው ውስጥ ጎልተው የሚታዩ ኃላፊነቶችን ለመቀበል ብቃት አይኖራቸውም። እርግጥ ነው፣ ሽማግሌዎች የራሳቸውን የመመዘኛ ደንብ ወይም የግል ምርጫቸውን ሌሎች እንዲቀበሉ እንዳያስገድዱ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።

6 ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በመንግሥት አዳራሻችን በሚደረገው የመንፈሳዊ ግብዣ ላይ ተገኝተው እንዲደሰቱ ጥሪ ይደረግላቸዋል። ብዙውን ጊዜ፣ አዳራሹ በጣም የሚስብ፣ ንጹሕና ሥርዓት ያለው ስለሆነ ሌሎች ሰዎችንም የመጋበዝ ፍላጎት ይኖረናል። ሆኖም አዳራሹ ሁልጊዜ ንጹሕ ሆኖ እንዲገኝ ጥረት ይጠይቃል። አዳራሻችሁን በደንብ ፈትሹት። ወንበሮቹ፣ ወለሉ ግድግዳዎቹ ንጹሕ ናቸውን? የመጸዳጃ ቤቱስ በየጊዜው በደንብ ይወለወላልን? የቆሸሸ ወለል ወይም ቀለሙ የተላላጠ ግድግዳ ሁልጊዜ የምናይ ከሆነ ይህ ዓይነቱን ሁኔታ ተቀባይነት እንዳለው አድርገን እንቆጥረው ይሆናል። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መንግሥት አዳራሹ በሚመጡ እንግዶች ላይ ግን መጥፎ ስሜት ሊያሳድርባቸው ይችላል። አዳራሹ በሚጸዳበት ወይም በሚታደስበት ወቅት ደስ የሚልና ማራኪ ይሆን ዘንድ በምንችለው ሁሉ የበኩላችንን ድርሻ ማበርከት ይኖርብናል።

7 የግል ንጽሕህናችንን በመጠበቅ፣ ቤታችንን፣ መኪናችንንና የመንግሥት አዳራሻችንን ንጹሕና ሥርዓታማ አድርገን በመያዝ ምንም ቃል ሳንናገር አምላክን ለማስከበር እንችላለን። መልካም አርአያችን ለመደናቀፍ አንዳችም ምክንያት አይሰጥም፤ ከዚህ ይልቅ አምልኮታችን ንጹሕና ትክክለኛ መሆኑን ይመሠክራል። — 1 ቆሮ. 10:31, 32፤ ያዕ. 1:27

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ