የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/94 ገጽ 1
  • በበረከት እየዘራህ ነውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በበረከት እየዘራህ ነውን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በበረከት መዝራት በረከት ያስገኛል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ጽድቅን በመዝራት የአምላክን ፍቅራዊ ደግነት እጨዱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 6/94 ገጽ 1

በበረከት እየዘራህ ነውን?

1 “ብዙ ከዘራህ ብዙ ታጭዳለህ” የሚል አባባል አለ። በተለይ አምልኮታችንን በተመለከተ ይህ እውነት ነው። ለስብሰባዎች በመዘጋጀት፣ የመንግሥቱን መልእክት በማወጅና ለወንድሞቻችን ፍቅር በማሳየት ብዙ ጊዜ ባጠፋንና ጥረት ባደረግን ቁጥር በመንፈሳዊ ይበልጥ እያደግን እንሄዳለን። ተቃራኒውን ካደረግን ደግሞ በመንፈሳዊ መቀጨጫችን የማይቀር ነው። ዳተኞች ብንሆን ወይም በግማሽ ልብ ብንሠራ የሚያረካ ውጤት እናገኛለን ብለን ልንጠብቅ እንችላለንን?

2 ሐዋርያው ጳውሎስ በ2 ቆሮንቶስ 9:6 ላይ “በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፣ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል” በማለት ይህን መሠረታዊ ሥርዓት ገልጾታል። አንተስ በበረከት እየዘራህ ነውን?

3 የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ውጤታማ አገልጋዮች ለመሆን በመጀመሪያ የግል ጥናታችንን በተመለከተ በበረከት የምንዘራ መሆን አለብን። መንፈሳዊ ነገሮችን የመመገብ ከፍተኛ ፍላጎት ሊኖረን ይገባል። (መዝ. 119:97, 105፤ ማቴ. 5:3 አዓት) በዕለታዊ ኑሯችን የሚደራረቡብን ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ለሚያስፈልጉን መንፈሳዊ ነገሮች ንቁዎች ሆነን ለመገኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠይቅብናል። አብዛኞቻችን ይህን ለማድረግ ‘ጊዜ መዋጀት’ ያስፈልገናል። (ኤፌ. 5:16) አንዳንዶች በተወሰኑ ቀናት ጠዋት ጠዋት ቀደም ብለው በመነሣት የግል ጥናት ለማድረግ ዝግጅት አድርገዋል። ሌሎች አንዳንድ ምሽቶችን ለጥናት መድበዋል። በበረከት የምናጭደው በምን መንገድ ነው? እምነታችን ይጠነክራል፣ ብሩህ ተስፋ እንዲሁም ደስታ ያለበትና አዎንታዊ የሆነ አመለካከት ይኖረናል። — ሮሜ 10:17፤ 15:4፤ 1 ጴጥ. 1:13

4 የጉባኤ ስብሰባዎች፦ ዳዊት በመዝሙር 122:1 ላይ “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ” ብሏል። አንተስ እንደዚህ ይሰማሃልን? በበረከት መዝራት አዘውትሮ በአምስቱም ሳምንታዊ ስብሰባዎቻችን ላይ መገኘት ማለት ነው። በመጥፎ የአየር ጠባይ አሳበህ ላለመቅረት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። ብዙውን ጊዜ በርካታ እንቅፋቶችን በተወጣን መጠን የምናገኛቸው በረከቶችም ይጨምራሉ።

5 ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብለህ ተገኝ። ከወንድሞችህ ጋር የሚያንጹ ጭውውቶችን ለማድረግ ስብሰባው ካለቀ በኋላም ትንሽ ቆይ። የምትችለውን ያህል ከብዙ ወንድሞችንና እኅቶችን ጋር ተቀራረብ። በመጠበቂያ ግንብ ጥናትና በሌሎች ስብሰባዎች ላይ አጋጣሚ ስታገኝ ሐሳብ በመስጠት በበረከት መዝራት ትችል ዘንድ በደንብ ተዘጋጅ። በስብሰባ ጊዜያት ሌሎችን ‘በነፃ በማጠጣትህ’ አንተም ‘በነፃ ትጠጣለህ።’ — ምሳሌ 11:25 አዓት

6 የመስክ አገልግሎት፦ በበረከት መዝራት የሚለው መሠረታዊ ሥርዓት ከመስክ አገልግሎት ይበልጥ የሚሠራበት መስክ የለም ለማለት ይቻላል። ለመስክ አገልግሎት ብዙ ሰዓት በመደብን ቁጥር አስደሳች ተሞክሮዎችን፣ ፍሬያማ ተመላልሶ መጠየቆችንና ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማግኘታችን አይቀርም።

7 በመስክ አገልግሎት በበረከት ስንዘራ በጥራትና በብዛት መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱን ማስረዳት የተባለው መጽሐፍ የአገልግሎታችንን ጥራት እንድናሻሻል ከፍተኛ እርዳታ ያደርግልናል። ከገጽ 9–15 ላይ ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል የመስማት ፍላጎትን ለመቀስቀስ የሚረዱ ከ40 በላይ የሚሆኑ መግቢያዎች በ18 ርዕሶች ሥር ተዘርዘረዋል። ተመልሰህ በመሄድ የዘራኸውን ፍሬ ማጨድ ትችል ዘንድ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ስታገኝ በማስታወሻ ደብተርህ ላይ መመዝገብን አትርሳ። ያደረግኸው ጥረት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስገኝቶልህ አንድ ሰው እንዴት በበረከት መዝራት እንደሚችል ልታስተምር ትችላለህ።

8 በበረከት ከዘራን ከይሖዋ የምናገኘው በረከት እንደሚጨምር ልንጠብቅ እንችላለን። — ሚል. 3:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ