ወደ ሌላ ቦታ ለመጓዝ ስትነሱ . . .
ለጉዞ ወይም ለእረፍት ዕቅድ ስታወጣ የመንግሥቱን ጉዳዮች ለማስቀደም የሚረዱህ ጥቂት ማሳሰቢያዎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል:-
◼ በአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ቁርጥ ያለ ዕቅድ ይኑርህ። ችግር ውስጥ እንዳትወድቅ መጓጓዣህንና ማረፊያህን ቀደም ብለህ አዘጋጅ።
◼ የምትጓዘው ለእረፍትም ሆነ ለሌላ ጉዳይ በምትሄድበት ቦታ ባለው ጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘትና በአገልግሎት ለመካፈል ዕቅድ አውጣ። የመስክ አገልግሎት ሪፖርትህን መመለስ አትርሳ፤ አስፈላጊ ከሆነ ሪፖርቱን ለጉባኤህ ጸሐፊ በፖስታ ላክ።
◼ በእውነት ውስጥ የማይመላለሱ ዘመዶችህን የምትጠይቅ ከሆነ መደበኛ ያልሆነ ውጤታማ ምሥክርነት ለመስጠት አጋጣሚ ሊከፍትልህ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስህንና ጽሑፎች መያዝህን አረጋግጥ።
◼ ክልሉን ለመሸፈን እርዳታ የሚያስፈልገውን በአቅራቢያህ የሚገኝ ጉባኤ ስለመርዳት አስበሃልን? በአካባቢህ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች መረጃ ለማግኘት ከሽማግሌዎች ወይም ከወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጋር ተነጋገር።
◼ የትምህርት ቤት የእረፍት ጊዜ ወጣቶች የአገልግሎት እንቅስቃሴያቸውን እንዲያሰፉ ግሩም አጋጣሚ ይከፍትላቸዋል። ወጣቶች፣ ረዳት አቅኚ መሆን ትችላላችሁን?
◼ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችህ አንተ በማትኖርበት ጊዜ ከሌላ ሰው ጋር እንዲያጠኑ አመቻች። ከመሄድህ በፊት የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪውን ሊረዳው ይችላል ብለህ እምነት ከምትጥልበት አስፋፊ ጋር አስተዋውቀው።
◼ ሽማግሌዎች የጉባኤው እንቅስቃሴ እንደተደራጀ እንዲቀጥልና ተጓዡ በጉባኤ ውስጥ የሚሠራቸውን ሥራዎች ሌላ ሰው እንዲይዛቸው በማድረግ በኩል ንቁዎች መሆን አለባቸው።
‘በጥንቃቄ ዕቅድ አውጥቶ መሥራት እንደሚጠቅም’ አስታውስ። (ምሳሌ 21:5 የ1980 ትርጉም) የክረምት የእረፍት ጊዜህን በተቻለህ መጠን በቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ለማሳለፍ ዕቅድ አውጣ።