የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/98 ገጽ 2
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 5/98 ገጽ 2

ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

አንጎላ፦ በታኅሣሥ ወር 35,034 አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሰዋል።

ባንግላዴሽ፦ በዳካ “በአምላክ ቃል ማመን” የተባለው የአውራጃ ስብሰባ ተደርጎ 142 ሰዎች ሲገኙ 14 ተጠምቀዋል። ይህም እስከ አሁን ድረስ በባንግላዴሽ በአንድ ጊዜ ከተጠመቁ ሰዎች ሁሉ ይኼኛው በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ነው።

ቤኒን፦ “በአምላክ ቃል ማመን” የተባለው የአውራጃ ስብሰባ በተከታታይ ተደርጎ በጠቅላላ 15,633 ተሰብሳቢዎች ሲገኙ 403 ተጠምቀዋል። የታኅሣሥ ወር ሪፖርት እንደሚያሳየው የአስፋፊዎቸ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር 5,351 ደርሷል።

ኢትዮጵያ፦ በሰኔ ወር አጋማሽ በመካከለኛው ዩናይትድ ስቴትስ፣ በዴትሮይት አቅራቢያ በሚቺጋን፣ ፓንትያክ በሚደረገው “የአምላክ የሕይወት መንገድ” በተባለው ብሔራት አቀፍ እና የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ቢያንስ አሥራ አምስት የሚያክሉ ወንድሞችና እህቶች ቅርንጫፍ ቢሯችንን ወክለው ለመሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። ከበርካታ ዓመታት በኋላ ወንድሞቻችን የስብሰባ ልዑክ በመሆን በይፋ ሲጓዙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

በጥር ወር በርካታ ጉባኤዎች ጽሑፍ በማበርከቱ ሥራ ጥሩ ውጤት አግኝተዋል። ለምሳሌ ያህል 105 አስፋፊዎች ያሉት በአዲስ አበባ የሚገኘው የመካኒሳ ጉባኤ 120 መጻሕፍት ሲያበረክት 45 አስፋፊዎች ያሉት የአጋሮ ጉባኤ 44 አበርክቷል፤ 11 አስፋፊዎቸ ያሉት የበደሌ ጉባኤ ደግሞ 30 አበርክቷል። በጊምቢ፣ በጅማ፣ በኮምቦልቻ፣ በመቱ፣ በሚዛንና በባኮ የሚገኙ ጉባኤዎች አንድ አስፋፊ ከአንድ የሚበልጥ መጽሐፍ አበርክቷል። አንድ የዘወትር አቅኚ 16 መጻሕፍት ሲያበረክት ሁለት ረዳት አቅኚዎች ደግሞ 19 መጻሕፍት አበርክተዋል።

ላይቤሪያ፦ በሞንሮቪያ በታኅሣሥ ወር አምስት የአውራጃ ስብሰባዎች ተደርገው 5,158 ሰዎች ተገኝተዋል። በዚያ ወር 2,127 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት ተደርጓል።

ማዳጋስካር፦ በታኅሣሥ ወር ባለፈው ዓመት በነበረው የአስፋፊዎች አማካይ ቁጥር ላይ የ11 በመቶ ጭማሪ ተገኝቷል። 9,226 አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት ተካፍለዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ