የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/98 ገጽ 3-6
  • አቅኚ መሆን ትችላለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አቅኚ መሆን ትችላለህን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 11 በዚህ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ የምታደርጋቸው ውሳኔዎች የወደፊት ሕይወትህን ሙሉ በሙሉ ሊቀርጹት ይችላሉ። ቀደም ሲል ራስህን ወስነህ የተጠመቅህ የይሖዋ ምሥክር ከሆንክ በሙሉ ነፍስ ራስህን ለይሖዋ ሰጥተሃል ማለት ነው። (ዕብ. 10:7) በመጀመሪያ ማድረግ የምትችለው ነገር ለአንድ ወር ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆነህ በማገልገል መሞከር ነው። እንዲህ ማድረግህ ከዘወትር አቅኚነት ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ደስታዎችና ኃላፊነቶች እንድትቀምስ ከማስቻሉም በላይ በሕይወትህ ውስጥ ምን ነገር ማድረግ እንዳለብህ ይበልጥ ግልጽ አመለካከት እንደምትይዝ እንደሚረዳህ ጥርጥር የለውም። ታዲያ ትምህርት ከጨረስክ በኋላ የሚኖረውን ክፍተት ሙሉ ቀን በሰብዓዊ ሥራ ከማስያዝ ይልቅ ለምን የዘወትር አቅኚነትን አትጀምርም? አንዳንዶች የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኘውን ደስታ በኋለኞቹ የሕይወት ዘመናቸው ሲቀምሱ አስቀድመው ባለመጀመራቸው ይቆጫሉ።
  • 12 ወጣት እንደመሆንህ መጠን በነጠላነት ለመቆየት የሚያስችልህን አጋጣሚ በመጠቀም በሙሉ ጊዜ የስብከት ሥራ መካፈል ትችላለህ። ከጊዜ በኋላ ትዳር ለመመሥረት ብትፈልግ እንኳ መጀመሪያ በዘወትር አቅኚነት በማገልገል ለትዳር ጥሩ መሠረት መጣልን የመሰለ ነገር የለም። በአካልም ሆነ በመንፈሳዊ እየጎለመስክ ስትሄድ ተመሳሳይ ዝንባሌ ካላት የትዳር ጓደኛ ጋር አቅኚነትን ሙያ አድርገህ ለመያዝ ትመርጥ ይሆናል። አብረው በአቅኚነት ያገለገሉ አንዳንድ ባልና ሚስት በወረዳ የበላይ ተመልካችነት ወይም በልዩ አቅኚነት ማገልገላቸውን ቀጥለዋል። ይህ በእርግጥ አርኪ የሆነ የሕይወት ጎዳና ነው!
  • 13 በአቅኚነት የቆየህበት ጊዜ ይብዛም ይነስም የተሟላ እውቀት ከማግኘትህም በተጨማሪ በምድር ላይ ያለ የትኛውም ሌላ ዓይነት ሙያ ሊሰጥህ የማይችለውን በዋጋ የማይተመን ስልጠና ታገኛለህ። አቅኚነት ሥርዓታማነትን፣ የተደራጀ ሕይወት መምራትን፣ ከሌሎች ጋር ተግባብቶ መኖርን፣ በይሖዋ ላይ መመካትን እንዲሁም ትዕግሥትንና ደግነትን እንዴት ማዳበር እንደሚቻል ያስተምርሃል፤ እነዚህ ከፍተኛ ኃላፊነቶችን እንድትቀበል የሚያስችሉ ባሕርያት ናቸው።
  • 14 የአሁኑን ያክል ሕይወት አስተማማኝ ያልሆነበት ጊዜ የለም። ይሖዋ ተስፋ ከሰጠው ነገር በስተቀር ዘላቂ የሆኑ ነገሮች የሉም ማለት ይቻላል። ከፊትህ ብሩህ ተስፋ የተዘረጋልህ በመሆኑ በመጪዎቹ ዓመታት በሕይወትህ ምን እንደምታደርግ ለመወሰን በቁም ነገር ልታስብበት የሚገባ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ይኖራልን? የአቅኚነትን መብት በጥሞና አመዛዝነው። የአቅኚነት አገልግሎትን ሙያ አድርገህ በመምረጥህ በፍጹም አትጸጸትም።
  • 15 የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ በምትሞላበት ጊዜ “ብዙ ሳትባክን በዓመት ውስጥ የሚፈለግብህን የ1,000 ሰዓት ግብ ለማሟላት እንድትችል የግል ሁኔታዎችህን አመቻችተሃልን?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብህ። እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ በየቀኑ በአማካይ ለሦስት ሰዓት ያህል ማገልገል አለብህ። ይህ ደግሞ ጥሩ ፕሮግራም ማውጣትና ራስን መገሰጽ እንደሚጠይቅ የታወቀ ነው። አብዛኞቹ አቅኚዎች በጥቂት ወራት ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ልማድ ያዳብራሉ።
  • 16 ሆኖም መክብብ 9:11 [NW] ‘ጊዜና አጋጣሚ ሁሉን ይገናኛቸዋል’ በማለት አንድ ሐቅ ያስቀምጣል። ከባድ ሕመም ወይም ያልተጠበቁ ሁኔታዎች አንድ አቅኚ ከሰዓት ግቡ ወደኋላ እንዲቀር ሊያስተጓጉሉት ይችላሉ። ችግሩ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ካልሆነና በአገልግሎት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከተከሰተ የጎደለውን ሰዓት ለማሟላት የሚያስፈልገው ነገር ረዘም ላለ ሰዓት ለማገልገል ፕሮግራም ማውጣት ሊሆን ይችላል። ሆኖም የአገልግሎት ዓመቱ ሊገባደድ ጥቂት ወራት ብቻ ሲቀሩት አንድ ከባድ ችግር ቢፈጠርና አቅኚው ሰዓቱን ማሟላት የማይችል ከሆነስ?
  • 17 ለጥቂት ወራት ብቻ ለጊዜው ከታመምክ ወይም ከአቅምህ በላይ በሆነ አስቸኳይ ጉዳይ የተነሳ የሰዓት ግብህን ማሟላት ካቃተህ ከጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት ወደ አንዱ ቀርበህ ችግርህን መግለጽ ትችላለህ። ሽማግሌዎቹ የጎደለውን ሰዓት ስለማሟላት ሳትጨነቅ በአቅኚነት አገልግሎት እንድትቀጥል መፍቀዳቸውን ተገቢ ሆኖ ካገኙት እንድትቀጥል ሊፈቅዱልህ ይችላሉ። ጸሐፊው የጎደለውን ሰዓት ማሟላት እንደማይጠበቅብህ ለመግለጽ የጉባኤው የአስፋፊ መዝገብ ካርድህ ላይ ምልክት ያደርግበታል። ሆኖም ይህ ከአገልግሎት እንድታርፍ የተሰጠህ ፈቃድ ሳይሆን የገጠሙህን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ልዩ አስተያየት ነው።—የነሐሴ 1986 የመንግሥት አገልግሎታችን (የእንግሊዝኛ) አባሪ፣ አንቀጽ 18⁠ን ተመልከት።
  • 18 ተሞክሮ ያላቸው አቅኚዎች በአገልግሎት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ብዙ ሰዓት ያገለግላሉ። የአቅኚነት አገልግሎታቸው ቀዳሚውን ቦታ ስለሚይዝ አንዳንድ ጊዜ አላስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን መተዉን አስፈላጊ ሆኖ ያገኙታል። አንድ አቅኚ ሰዓቱ ሳይሟላለት የቀረው ጥሩ ፕሮግራም ሳያወጣ በመቅረቱ ወይም ፕሮግራሙን በጥብቅ ለመከተል ራሱን መገሰጽ ተስኖት ከሆነ የጎደለውን ሰዓት የማሟላት ኃላፊነት እንዳለበት ሊሰማው ይገባል። እንዲሁም ልዩ አስተያየት እንዲደረግለት መጠበቅ የለበትም።
  • 19 አንድ አቅኚ በሁኔታዎቹ ላይ የተከሰተ ሊያስቀር የማይችለው ለውጥ ሊገጥመው የሚችልበት ጊዜ አለ። ቀጣይ በሆነ የጤና እክል፣ ተጨማሪ የቤተሰብ ኃላፊነት በመምጣቱ እና በሌሎች ነገሮችም የተነሳ በረጅም ጊዜ ውስጥ የሰዓት ግቡን ማሟላት የማይቻል ሊሆንበት ይችላል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ወደ አስፋፊነት መመለስና የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በረዳት አቅኚነት አገልግሎት መካፈሉ የጥበብ እርምጃ ይሆናል። አንድ ሰው ሁኔታዎቹ የሰዓት ግቡን ማሟላት የማይፈቅዱለት ከሆነ አቅኚ ሆኖ እንዲቀጥል ደጋግሞ በመፍቀድ ያልተቋረጠ ዝግጅት አይደረግም።
  • 21 እውነተኛ ደስታ በአመዛኙ የተመካው ከይሖዋ ጋር የጠበቀ የግል ዝምድና በመመሥረትና እሱን በታማኝነት ለማገልገል ባለን የጸና እምነት ላይ ነው። ኢየሱስ በመከራው እንጨት ላይ የጸናው ‘ከፊቱ ያለውን ደስታ’ በማሰብ ነው። (ዕብ. 12:2) ደስታ ሊያገኝ የቻለው ደግሞ የአባቱን ፈቃድ በመፈጸሙ ነው። (መዝ. 40:8) በዚህ የነገሮች ሥርዓት ውስጥ አብዛኛው የሕይወታችን እንቅስቃሴ ለይሖዋ ከምናቀርበው አምልኮ ጋር የተያያዘ ከሆነ እውነተኛ ደስታ ማግኘት እንችላለን። መንፈሳዊ ነገሮችን መከታተል ሕይወታችን ዓላማ እንዲኖረው ያስችላል። ይህ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ልባችን ትክክል የሆነውን ነገር እንደምናደርግ ስለሚነግረን ነው። ደስታ የሚገኘው በመስጠት ስለሆነ በአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ሌሎችን ለማስተማር ስንል ራሳችንን መስጠት የምንችልበት የተሻለ መንገድ አለመኖሩን እናውቃለን።—ሥራ 20:35
  • 22 በመግቢያው አንቀጽ ላይ የተጠቀሰው አቅኚ ጉዳዩን እንዲህ ሲል ገልጾታል:- “ታስጠኑት የነበረ ሰው የይሖዋ አወዳሽ ሲሆን ከማየት የበለጠ ደስታ ሊኖር ይችላልን? የአምላክ ቃል ሰዎች ይሖዋን ለማስደሰት ሲሉ በሕይወታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያደርጉ በማንቀሳቀስ ረገድ ምን ያህል ኃይል እንዳለው መመልከት የሚያስደስትና እምነትን የሚያጠነክር ነገር ነው።” (የጥቅምት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 18-23 ተመልከት።) ስለዚህ ደስታ የሚያስገኝልህ ነገር ምንድን ነው? ዓለም ከሚያቀርብልህ ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ዘላቂና ዋጋ የሚያስገኙ ግቦችን ከፍ አድርገህ የምትመለከት ከሆነ አቅኚነት አንድን ሥራ ከማከናወን የሚገኝ እውነተኛ ደስታ እንድታገኝ በማድረግ አስደሳች ስሜት ይሰጥሃል።
  • 23 እርግጥ ነው አቅኚ ለመሆን መወሰን ያለብህ አንተው ራስህ ነህ። በሕይወትህ ውስጥ ያሉትን የግል ሁኔታዎችህን ማወቅ የሚችለው ይሖዋ ብቻ ነው። (ሮሜ 14:4) በሙሉ ልብህ፣ ነፍስህ፣ ሐሳብህና ኃይልህ እርሱን እንድታገለግለው መጠየቁ ትክክል ነው። (ማር. 12:30፣ ገላ. 6:4, 5) ይሖዋ እያጉረመረመ ወይም በግዴታ የሚያገለግለውን ሳይሆን በደስታ የሚያገለግለውን ደስተኛ ሰጪ ይወዳል። (2 ቆሮ. 9:7፤ ቆላ. 3:23) በሙሉ ጊዜ የምታገለግልበት ምክንያት ይሖዋንና በክልልህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ስለምትወድ መሆን አለበት። (ማቴ. 9:36-38፤ ማር. 12:30, 31) እንዲህ ዓይነት ስሜት ካለህ የአቅኚነት አገልግሎትን በቁም ነገር ልታስብበት ይገባል።
  • 24 እዚህ ላይ የሰፈረው ነጥብ አቅኚ ለመሆን ያለህን አጋጣሚ ለማመዛዘን እንደሚረዳህ ተስፋ እናደርጋለን። በዘወትር አቅኚነት ለማገልገል ሁኔታዎችህን ማስተካከል ትችላለህን? ከታች “ሳምንታዊ የአቅኚነት አገልግሎት ፕሮግራሜ” የሚል ሰንጠረዥ አለ። በየሳምንቱ በአማካይ ወደ 23 ሰዓት ገደማ በአገልግሎት ለማሳለፍ የሚያስችልህን ተግባራዊ የሆነ ፕሮግራም ለማውጣት ትችል እንደሆነ ሞክር። ከዚያም እምነትህንና ትምክህትህን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣል። እሱ በሚሰጥህ ድጋፍ ሊሳካልህ ይችላል! ይሖዋ ‘በረከትንም አትረፍርፌ አፈስላችኋለሁ’ ሲል ቃል ገብቷል።—ሚል. 3:10
  • 25 ስለዚህ “አቅኚ መሆን ትችላለህን?” በማለት እንጠይቅሃለን። “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ሳትዘገይ አቅኚነት ለመጀመር ቀን ወስን፣ ይሖዋ አስደሳች በሆነ ሕይወት እንደሚባርክህ እርግጠኛ ሁን!
  • አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኛቸው በረከቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • “ይሖዋን ለማክበር አሁን ከምታደርገው የበለጠ መሥራት ትችላለህን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • አቅኚነት ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና ያጠናክርልናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 7/98 ገጽ 3-6

አቅኚ መሆን ትችላለህን?

1 “ሌላ ሥራ ፈጽሞ አይታየኝም። እንዲህ ዓይነት ደስታ የሚያስገኝ ሌላ ሥራ ይኖራል ብዬ በፍጹም አላስብም።” ይህን የተናገረው ማን ነው? በሕይወታቸው ውስጥ የሙሉ ጊዜ አገልግሎትን አስደሳች ሙያ አድርገው ከያዙት በመቶ ሺህ ከሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች አንዱ ነው። አቅኚ ሆነህ ማገልገል ትችል እንደሆነና እንዳልሆነ በጥሞና አስበህበት ታውቃለህን? ራሳችንን ያላንዳች ገደብ ለይሖዋ የወሰንን እንደመሆናችን መጠን የመንግሥቱን ምስራች በማዳረስ ረገድ የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ የምንችልበትን አቅጣጫ ማጤን ይገባናል። ይህን ግብ በመያዝ ብዙዎች ስለ አቅኚነት አገልግሎት የሚጠይቋቸውን አንዳንድ ጥያቄዎች እባክህ መርምር።

ጥያቄ 1፦ “አንዳንዶች አቅኚነት ለሁሉም ሰው አይደለም ይላሉ። ታዲያ እኔ አቅኚ መሆን እችል እንደሆነና እንዳልሆነ እንዴት አውቃለሁ?”

2 መልሱ በሁኔታዎችህና ባሉህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ኃላፊነቶች ላይ የተመካ ነው። ጤንነታቸው ወይም አሁን ያሉበት ሁኔታ በየወሩ 90 ሰዓት በአገልግሎቱ ማሳለፍ የማይፈቅድላቸው ብዙ ወንድሞችና እህቶች አሉ። ክርስቲያን ሚስቶችና እናቶች የሆኑትን በርካታ ታማኝ እህቶች አንደ ምሳሌ እንውሰድ። ሁኔታዎቻቸው በሚፈቅዱላቸው መጠን አዘውትረው በአገልግሎት ይካፈላሉ። ሁኔታቸው ሲመቻች በየዓመቱ ለአንድ ወር ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ ረዳት አቅኚ ስለሚሆኑ በአገልግሎቱ ያላቸውን ተሳትፎ ከፍ በማድረግ የሚገኘውን ደስታ ያጭዳሉ። (ገላ. 6:9) ምንም እንኳ ሁኔታቸው በአሁኑ ወቅት የሙሉ ጊዜ አቅኚዎች ሆነው እንዲያገለግሉ ባይፈቅዱላቸውም የአቅኚነትን መንፈስ ከማበረታታቸውም በላይ የምሥራቹ ቀናተኛ አገልጋዮች ስለሆኑ ለጉባኤው በረከት ናቸው።

3 በሌላ በኩል ደግሞ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ ብዙ ኃላፊነቶች የሌሉባቸው ብዙ ወንድሞችና እህቶች ቅድሚያ በሚሰጡዋቸው ነገሮች ረገድ ማስተካከያዎች በማድረግ በአቅኚነት አገልግሎት መካፈል ችለዋል። ያንተስ ሁኔታ እንዴት ነው? ዓለማዊ ትምህርትህን ጨርሰህ ቁጭ ያልክ ወጣት ነህን? ሚስት ከሆንሽ ባልሽ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር በበቂ መጠን ማሟላት ይችላልን? የምታሳድጓቸው ልጆች የሌሉዋችሁ ባለ ትዳሮች ናችሁን? ከዓለማዊ ሥራህ ጡረታ ወጥተሃል? አቅኚ መሆን ወይም አለመሆን እያንዳንዱ ግለሰብ በግሉ የሚያደርገው ውሳኔ ነው። ጥያቄው ግን አቅኚ መሆን ትችላለህ ወይ? የሚል ነው።

4 ሰይጣን ሕይወታችን በሚከፋፍሉ ነገሮች እንዲያዝ ለማድረግና በራስ ወዳድነት የሕይወት ጎዳና እኛን ለማጥመድ በእሱ ቁጥጥር ስር ባለው ዓለማዊ የነገሮች ሥርዓት ይጠቀማል። የዓለም ክፍል ላለመሆን ቁርጥ ውሳኔ ካደረግን ይሖዋ የመንግሥቱን ጉዳዮች በአንደኛ ደረጃ እንድናስቀምጥና ለእኛ ክፍት የሆኑልንን ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት መብቶች በሙሉ እንድንደርስባቸውና እንድንቀበላቸው ይረዳናል። አቅኚ ሆነህ ለማገልገል ሁኔታዎችህን ማስተካከል የምትችል ከሆነ ለምን እንደዚያ አታደርግም?

ጥያቄ 2፦ “በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ከሆንኩ ራሴን ችዬ መኖር እንደምችል እንዴት እርግጠኛ ልሆን እችላለሁ?”

5 በብዙ አገሮች ውስጥ ለሕይወት አስፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ነገሮች ለማግኘት በየሳምንቱ ለሥጋዊ ሥራ የሚጠፋው ሰዓት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ አይካድም። ይሁን እንጂ ብዙዎች ለአሥርተ ዓመታት በአቅኚነት ያገለገሉ ሲሆን ይሖዋም እነሱን መደገፉን ቀጥሏል። በአቅኚነት ለመቀጠል እምነትና የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ አስፈላጊ ናቸው። (ማቴ. 17:20) በመዝሙር 34:10 ላይ ‘ይሖዋን የሚፈልጉ መልካም ነገር ሁሉ እንደማይጎድልባቸው’ ማረጋገጫ ተሰጥቶናል። የአቅኚነት አገልግሎትን የጀመረ ማንኛውም ሰው ይሖዋ የሚያስፈልገውን ነገር እንደሚያሟላለት ሙሉ ትምክህት ሊኖረው ይገባል። ይሖዋ በየትኛውም ቦታ ላሉ ታማኝ አቅኚዎች ይህንኑ እያደረገላቸው ነው! (መዝ. 37:25) እርግጥ በ2 ተሰሎንቄ 3:8, 10 እና በ1 ጢሞቴዎስ 5:8 ላይ ካሉት መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር በመስማማት አቅኚዎች ገንዘብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ሌሎች እንዲደግፏቸው አይጠብቁም።

6 አቅኚ ለመሆን የሚያስብ ማንኛውም ሰው ኢየሱስ እንደተናገረው ‘አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን መቁጠር’ ይኖርበታል። (ሉቃስ 14:28) እንዲህ ማድረግ ጥበብ ነው። ለበርካታ ዓመታት በአቅኚነት የተሳካላቸውን በማነጋገር ይሖዋ እንዴት እንደደገፋቸው ጠይቃቸው። የወረዳ የበላይ ተመልካችህ ተሞክሮ ያለው አቅኚ እንደመሆኑ መጠን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል አንዳንድ ሐሳቦች ለመስጠት ደስተኛ ነው።

7 አንድ ሰው ኢየሱስ በማቴዎስ 6:33 ላይ የገባውን ቃል እውነተኝነት የሚገነዘበው ራሱን በይሖዋ እጅ ላይ ሙሉ በሙሉ ሲጥል ብቻ ነው። አንዲት አቅኚ እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “እኔና የአገልግሎት ጓደኛዬ በአቅኚነት እንድናገለግል አዲስ ወደተመደብንበት ቦታ ስንደርስ የነበረን የሚበላ ነገር ጥቂት አትክልትና አንድ እሽግ ቅቤ ብቻ ሲሆን ገንዘብ የለንም ነበር። ያለችዋን ምግብ ለእራት ከበላን በኋላ ‘እንግዲህ ለነገ ምንም የለንም’ አልን። በነገሩ ላይ ጸለይንና ተኛን። በነጋታው ጠዋት አንዲት በአካባቢው የምትኖር የይሖዋ ምሥክር መጥታ ራስዋን ካስተዋወቀችን በኋላ ‘ይሖዋ አቅኚዎች እንዲልክ ጸልዬ ነበር። አሁን ቀኑን ሙሉ አብሬያችሁ ማሳለፍ እችላለሁ። ነገር ግን የምኖረው ከከተማው ውጪ በመሆኑ ምሳዬን አብሬያችሁ ስለምበላ ለሁላችንም ይህንን ምግብ ይዤ መጥቻለሁ’ አለችን። ብዛት ያለው ሥጋና አትክልት ነበር።” ኢየሱስ ‘ስለ ነፍሳችን መጨነቅ’ እንደሌለብን ማረጋገጫ መስጠቱ ምንም አያስደንቅም! ቀጥሎ ሲናገርም “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?” ብሏል።—ማቴ. 6:25, 27

8 በዙሪያችን ያለው ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ቁሳዊ ሀብት የማሳደድ መንፈስ እየተጠናወተው ነው። ይህን አመለካከት እንድንይዝ የሚያደርግ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለብን። ሆኖም ለሙሉ ጊዜ አገልግሎት ያለን አድናቆት ባሉን ጥቂት ቁሳዊ ነገሮች ረክተን እንድንኖር ያስችለናል። (1 ጢሞ. 6:8) ቀላልና ሥርዓታማ ሕይወት የሚመሩ አቅኚዎች ለአገልግሎት ሰፊ ጊዜ የሚኖራቸው ከመሆኑም በላይ እውነትን ለሌሎች በማስተማር ከፍተኛ ደስታና መንፈሳዊ ጥንካሬ ያገኛሉ። ምንም እንኳ የባሕታዊነት ሕይወት መምራት ባይፈልጉም ላሉበት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የያዙት ሚዛናዊ አመለካከት አቅኚነት በሚያስገኛቸው በረከቶች እንዲደሰቱ አስችሏቸዋል።

9 በመጨረሻው ቀን ውስጥ እንደምንኖርና ይህ ክፉ ዓለም የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ካስተዋልን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ምሥራቹን ለመስበክ ስንል በመንፈሳዊ ሁኔታ አስፈላጊ የሆኑ መሥዋዕቶችን ለመክፈል እንነሳሳለን። ኢኮኖሚያዊ ሁኔታህን በድጋሚ በመገምገምና ጉዳዩን በይሖዋ እጅ ላይ በመተው እሱን ሙሉ ጊዜ ማገልገል እንደምትችል ትገነዘብ ይሆናል። ምንም እንኳ በአቅኚነት ለማገልገል ስትል አንዳንድ ቁሳዊ ፍላጎቶችህን መተው ቢኖርብህም የይሖዋን የተትረፈረፈ በረከት ታገኛለህ።—መዝ. 145:16

ጥያቄ 3፦ “በአሥራዎቹ ዕድሜ የምገኝ እንደመሆኔ መጠን የአቅኚነት አገልግሎትን ሙያዬ አድርጌ ለመምረጥ ማሰብ ያለብኝ ለምንድን ነው?”

10 የመጨረሻዎቹን ጥቂት የትምህርት ዓመታት በምታገባድድበት ጊዜ ስለ ወደፊቱ ሕይወትህ ማሰብህ ያለ ነገር ነው። የወደፊቱ ጊዜ የተረጋጋ፣ አስደሳችና አርኪ እንዲሆንልህ ትፈልጋለህ። በትምህርት ቤት ያሉ የተማሪ አማካሪዎች የበርካታ ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ወይም ሌላ ዓይነት ከፍተኛ ትምህርት መከታተል የሚጠይቅ ሀብት የሚያስገኝ ሙያ እንድትይዝ ሊገፋፉህ ይሞክሩ ይሆናል። በአግባቡ የሰለጠነው ክርስቲያናዊ ሕሊናህ ደግሞ አቅምህ በሚፈቅደው መጠን ይሖዋን ሙሉ በሙሉ ለማገልገል መዘጋጀት እንደሚኖርብህ ይነግርሃል። (መክ. 12:1) ውሎ አድሮ ደግሞ ለማግባትና ቤተሰብ ለመመሥረት ታስብም ይሆናል። ምን ታደርግ ይሆን?

11 በዚህ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ የምታደርጋቸው ውሳኔዎች የወደፊት ሕይወትህን ሙሉ በሙሉ ሊቀርጹት ይችላሉ። ቀደም ሲል ራስህን ወስነህ የተጠመቅህ የይሖዋ ምሥክር ከሆንክ በሙሉ ነፍስ ራስህን ለይሖዋ ሰጥተሃል ማለት ነው። (ዕብ. 10:7) በመጀመሪያ ማድረግ የምትችለው ነገር ለአንድ ወር ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆነህ በማገልገል መሞከር ነው። እንዲህ ማድረግህ ከዘወትር አቅኚነት ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ደስታዎችና ኃላፊነቶች እንድትቀምስ ከማስቻሉም በላይ በሕይወትህ ውስጥ ምን ነገር ማድረግ እንዳለብህ ይበልጥ ግልጽ አመለካከት እንደምትይዝ እንደሚረዳህ ጥርጥር የለውም። ታዲያ ትምህርት ከጨረስክ በኋላ የሚኖረውን ክፍተት ሙሉ ቀን በሰብዓዊ ሥራ ከማስያዝ ይልቅ ለምን የዘወትር አቅኚነትን አትጀምርም? አንዳንዶች የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኘውን ደስታ በኋለኞቹ የሕይወት ዘመናቸው ሲቀምሱ አስቀድመው ባለመጀመራቸው ይቆጫሉ።

12 ወጣት እንደመሆንህ መጠን በነጠላነት ለመቆየት የሚያስችልህን አጋጣሚ በመጠቀም በሙሉ ጊዜ የስብከት ሥራ መካፈል ትችላለህ። ከጊዜ በኋላ ትዳር ለመመሥረት ብትፈልግ እንኳ መጀመሪያ በዘወትር አቅኚነት በማገልገል ለትዳር ጥሩ መሠረት መጣልን የመሰለ ነገር የለም። በአካልም ሆነ በመንፈሳዊ እየጎለመስክ ስትሄድ ተመሳሳይ ዝንባሌ ካላት የትዳር ጓደኛ ጋር አቅኚነትን ሙያ አድርገህ ለመያዝ ትመርጥ ይሆናል። አብረው በአቅኚነት ያገለገሉ አንዳንድ ባልና ሚስት በወረዳ የበላይ ተመልካችነት ወይም በልዩ አቅኚነት ማገልገላቸውን ቀጥለዋል። ይህ በእርግጥ አርኪ የሆነ የሕይወት ጎዳና ነው!

13 በአቅኚነት የቆየህበት ጊዜ ይብዛም ይነስም የተሟላ እውቀት ከማግኘትህም በተጨማሪ በምድር ላይ ያለ የትኛውም ሌላ ዓይነት ሙያ ሊሰጥህ የማይችለውን በዋጋ የማይተመን ስልጠና ታገኛለህ። አቅኚነት ሥርዓታማነትን፣ የተደራጀ ሕይወት መምራትን፣ ከሌሎች ጋር ተግባብቶ መኖርን፣ በይሖዋ ላይ መመካትን እንዲሁም ትዕግሥትንና ደግነትን እንዴት ማዳበር እንደሚቻል ያስተምርሃል፤ እነዚህ ከፍተኛ ኃላፊነቶችን እንድትቀበል የሚያስችሉ ባሕርያት ናቸው።

14 የአሁኑን ያክል ሕይወት አስተማማኝ ያልሆነበት ጊዜ የለም። ይሖዋ ተስፋ ከሰጠው ነገር በስተቀር ዘላቂ የሆኑ ነገሮች የሉም ማለት ይቻላል። ከፊትህ ብሩህ ተስፋ የተዘረጋልህ በመሆኑ በመጪዎቹ ዓመታት በሕይወትህ ምን እንደምታደርግ ለመወሰን በቁም ነገር ልታስብበት የሚገባ ከዚህ የተሻለ ጊዜ ይኖራልን? የአቅኚነትን መብት በጥሞና አመዛዝነው። የአቅኚነት አገልግሎትን ሙያ አድርገህ በመምረጥህ በፍጹም አትጸጸትም።

ጥያቄ 4፦ “የሰዓት ግብ ማሟላት አንድ ራሱን የቻለ ጭንቀት አይደለምን? ከሰዓት ግቤ ወደኋላ ብቀርስ?”

15 የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ በምትሞላበት ጊዜ “ብዙ ሳትባክን በዓመት ውስጥ የሚፈለግብህን የ1,000 ሰዓት ግብ ለማሟላት እንድትችል የግል ሁኔታዎችህን አመቻችተሃልን?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብህ። እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ በየቀኑ በአማካይ ለሦስት ሰዓት ያህል ማገልገል አለብህ። ይህ ደግሞ ጥሩ ፕሮግራም ማውጣትና ራስን መገሰጽ እንደሚጠይቅ የታወቀ ነው። አብዛኞቹ አቅኚዎች በጥቂት ወራት ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ልማድ ያዳብራሉ።

16 ሆኖም መክብብ 9:11 [NW] ‘ጊዜና አጋጣሚ ሁሉን ይገናኛቸዋል’ በማለት አንድ ሐቅ ያስቀምጣል። ከባድ ሕመም ወይም ያልተጠበቁ ሁኔታዎች አንድ አቅኚ ከሰዓት ግቡ ወደኋላ እንዲቀር ሊያስተጓጉሉት ይችላሉ። ችግሩ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ካልሆነና በአገልግሎት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከተከሰተ የጎደለውን ሰዓት ለማሟላት የሚያስፈልገው ነገር ረዘም ላለ ሰዓት ለማገልገል ፕሮግራም ማውጣት ሊሆን ይችላል። ሆኖም የአገልግሎት ዓመቱ ሊገባደድ ጥቂት ወራት ብቻ ሲቀሩት አንድ ከባድ ችግር ቢፈጠርና አቅኚው ሰዓቱን ማሟላት የማይችል ከሆነስ?

17 ለጥቂት ወራት ብቻ ለጊዜው ከታመምክ ወይም ከአቅምህ በላይ በሆነ አስቸኳይ ጉዳይ የተነሳ የሰዓት ግብህን ማሟላት ካቃተህ ከጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ አባላት ወደ አንዱ ቀርበህ ችግርህን መግለጽ ትችላለህ። ሽማግሌዎቹ የጎደለውን ሰዓት ስለማሟላት ሳትጨነቅ በአቅኚነት አገልግሎት እንድትቀጥል መፍቀዳቸውን ተገቢ ሆኖ ካገኙት እንድትቀጥል ሊፈቅዱልህ ይችላሉ። ጸሐፊው የጎደለውን ሰዓት ማሟላት እንደማይጠበቅብህ ለመግለጽ የጉባኤው የአስፋፊ መዝገብ ካርድህ ላይ ምልክት ያደርግበታል። ሆኖም ይህ ከአገልግሎት እንድታርፍ የተሰጠህ ፈቃድ ሳይሆን የገጠሙህን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ልዩ አስተያየት ነው።—የነሐሴ 1986 የመንግሥት አገልግሎታችን (የእንግሊዝኛ) አባሪ፣ አንቀጽ 18⁠ን ተመልከት።

18 ተሞክሮ ያላቸው አቅኚዎች በአገልግሎት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ብዙ ሰዓት ያገለግላሉ። የአቅኚነት አገልግሎታቸው ቀዳሚውን ቦታ ስለሚይዝ አንዳንድ ጊዜ አላስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን መተዉን አስፈላጊ ሆኖ ያገኙታል። አንድ አቅኚ ሰዓቱ ሳይሟላለት የቀረው ጥሩ ፕሮግራም ሳያወጣ በመቅረቱ ወይም ፕሮግራሙን በጥብቅ ለመከተል ራሱን መገሰጽ ተስኖት ከሆነ የጎደለውን ሰዓት የማሟላት ኃላፊነት እንዳለበት ሊሰማው ይገባል። እንዲሁም ልዩ አስተያየት እንዲደረግለት መጠበቅ የለበትም።

19 አንድ አቅኚ በሁኔታዎቹ ላይ የተከሰተ ሊያስቀር የማይችለው ለውጥ ሊገጥመው የሚችልበት ጊዜ አለ። ቀጣይ በሆነ የጤና እክል፣ ተጨማሪ የቤተሰብ ኃላፊነት በመምጣቱ እና በሌሎች ነገሮችም የተነሳ በረጅም ጊዜ ውስጥ የሰዓት ግቡን ማሟላት የማይቻል ሊሆንበት ይችላል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ወደ አስፋፊነት መመለስና የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በረዳት አቅኚነት አገልግሎት መካፈሉ የጥበብ እርምጃ ይሆናል። አንድ ሰው ሁኔታዎቹ የሰዓት ግቡን ማሟላት የማይፈቅዱለት ከሆነ አቅኚ ሆኖ እንዲቀጥል ደጋግሞ በመፍቀድ ያልተቋረጠ ዝግጅት አይደረግም።

20 ብቁ ለሆኑት የሚደረግላቸው ልዩ የአሳቢነት ዝግጅት ብዙዎች አላስፈላጊ የሆነ ጭንቀት ባለመፍጠር በአቅኚነት አገልግሎት ለመመዝገብ ያደፋፍራቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህ ዝግጅት ቀደም ሲል በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ላይ ያሉትንም በአቅኚነት እንዲቀጥሉ ሊያበረታታቸው ይገባል። አቅኚዎች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዲሳካላቸው እንፈልጋለን።

ጥያቄ 5፦ “አንድ ነገር ማከናወንና መደሰት እፈልጋለሁ። የአቅኚነት አገልግሎት እርካታ ያስገኝልኝ ይሆን?”

21 እውነተኛ ደስታ በአመዛኙ የተመካው ከይሖዋ ጋር የጠበቀ የግል ዝምድና በመመሥረትና እሱን በታማኝነት ለማገልገል ባለን የጸና እምነት ላይ ነው። ኢየሱስ በመከራው እንጨት ላይ የጸናው ‘ከፊቱ ያለውን ደስታ’ በማሰብ ነው። (ዕብ. 12:2) ደስታ ሊያገኝ የቻለው ደግሞ የአባቱን ፈቃድ በመፈጸሙ ነው። (መዝ. 40:8) በዚህ የነገሮች ሥርዓት ውስጥ አብዛኛው የሕይወታችን እንቅስቃሴ ለይሖዋ ከምናቀርበው አምልኮ ጋር የተያያዘ ከሆነ እውነተኛ ደስታ ማግኘት እንችላለን። መንፈሳዊ ነገሮችን መከታተል ሕይወታችን ዓላማ እንዲኖረው ያስችላል። ይህ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ልባችን ትክክል የሆነውን ነገር እንደምናደርግ ስለሚነግረን ነው። ደስታ የሚገኘው በመስጠት ስለሆነ በአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ ሌሎችን ለማስተማር ስንል ራሳችንን መስጠት የምንችልበት የተሻለ መንገድ አለመኖሩን እናውቃለን።—ሥራ 20:35

22 በመግቢያው አንቀጽ ላይ የተጠቀሰው አቅኚ ጉዳዩን እንዲህ ሲል ገልጾታል:- “ታስጠኑት የነበረ ሰው የይሖዋ አወዳሽ ሲሆን ከማየት የበለጠ ደስታ ሊኖር ይችላልን? የአምላክ ቃል ሰዎች ይሖዋን ለማስደሰት ሲሉ በሕይወታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያደርጉ በማንቀሳቀስ ረገድ ምን ያህል ኃይል እንዳለው መመልከት የሚያስደስትና እምነትን የሚያጠነክር ነገር ነው።” (የጥቅምት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 18-23 ተመልከት።) ስለዚህ ደስታ የሚያስገኝልህ ነገር ምንድን ነው? ዓለም ከሚያቀርብልህ ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ዘላቂና ዋጋ የሚያስገኙ ግቦችን ከፍ አድርገህ የምትመለከት ከሆነ አቅኚነት አንድን ሥራ ከማከናወን የሚገኝ እውነተኛ ደስታ እንድታገኝ በማድረግ አስደሳች ስሜት ይሰጥሃል።

ጥያቄ 6፦ “አቅኚነት የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የግድ አስፈላጊ እስካልሆነ ድረስ አቅኚ መሆን ወይም አለመሆን የግል ምርጫዬ ነው ወይስ አይደለም?”

23 እርግጥ ነው አቅኚ ለመሆን መወሰን ያለብህ አንተው ራስህ ነህ። በሕይወትህ ውስጥ ያሉትን የግል ሁኔታዎችህን ማወቅ የሚችለው ይሖዋ ብቻ ነው። (ሮሜ 14:4) በሙሉ ልብህ፣ ነፍስህ፣ ሐሳብህና ኃይልህ እርሱን እንድታገለግለው መጠየቁ ትክክል ነው። (ማር. 12:30፣ ገላ. 6:4, 5) ይሖዋ እያጉረመረመ ወይም በግዴታ የሚያገለግለውን ሳይሆን በደስታ የሚያገለግለውን ደስተኛ ሰጪ ይወዳል። (2 ቆሮ. 9:7፤ ቆላ. 3:23) በሙሉ ጊዜ የምታገለግልበት ምክንያት ይሖዋንና በክልልህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ስለምትወድ መሆን አለበት። (ማቴ. 9:36-38፤ ማር. 12:30, 31) እንዲህ ዓይነት ስሜት ካለህ የአቅኚነት አገልግሎትን በቁም ነገር ልታስብበት ይገባል።

24 እዚህ ላይ የሰፈረው ነጥብ አቅኚ ለመሆን ያለህን አጋጣሚ ለማመዛዘን እንደሚረዳህ ተስፋ እናደርጋለን። በዘወትር አቅኚነት ለማገልገል ሁኔታዎችህን ማስተካከል ትችላለህን? ከታች “ሳምንታዊ የአቅኚነት አገልግሎት ፕሮግራሜ” የሚል ሰንጠረዥ አለ። በየሳምንቱ በአማካይ ወደ 23 ሰዓት ገደማ በአገልግሎት ለማሳለፍ የሚያስችልህን ተግባራዊ የሆነ ፕሮግራም ለማውጣት ትችል እንደሆነ ሞክር። ከዚያም እምነትህንና ትምክህትህን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣል። እሱ በሚሰጥህ ድጋፍ ሊሳካልህ ይችላል! ይሖዋ ‘በረከትንም አትረፍርፌ አፈስላችኋለሁ’ ሲል ቃል ገብቷል።—ሚል. 3:10

25 ስለዚህ “አቅኚ መሆን ትችላለህን?” በማለት እንጠይቅሃለን። “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ሳትዘገይ አቅኚነት ለመጀመር ቀን ወስን፣ ይሖዋ አስደሳች በሆነ ሕይወት እንደሚባርክህ እርግጠኛ ሁን!

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሳምንታዊ የአቅኚነት አገልግሎት ፕሮግራሜ

ሰኞ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

ማክሰኞ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

ረቡዕ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

ሐሙስ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

ዐርብ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

ቅዳሜ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

እሁድ፦ የጠዋት የመስክ አገልግሎት

ሰኞ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

ማክሰኞ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

ረቡዕ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

ሐሙስ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

ዐርብ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

ቅዳሜ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

እሁድ፦ የከሰዓት በኋላ የመስክ አገልግሎት

ሰኞ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

ማክሰኞ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

ረቡዕ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

ሐሙስ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

ዐርብ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

ቅዳሜ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

እሁድ፦ የምሽት የመስክ አገልግሎት

ለእያንዳንዱ የሳምንቱ ቀን የሚሆንህን ፕሮግራም በዕርሳስ ጻፍ።

በእያንዳንዱ ሳምንት ወደ 23 ሰዓት ገደማ በመስክ አገልግሎት ላይ ለማሳለፍ ፕሮግራም አውጣ።

በሳምንቱ ለማምጣት ያቀድኩት ሰዓት _________________

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ