የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/00 ገጽ 8
  • ስብሰባዎች ለወጣቶች ጠቃሚ ናቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስብሰባዎች ለወጣቶች ጠቃሚ ናቸው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ለአምልኮ አንድ ላይ መሰብሰብ ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ከስብሰባዎች የበለጠ ደስታ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ይሖዋ እየመራን ያለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 8/00 ገጽ 8

ስብሰባዎች ለወጣቶች ጠቃሚ ናቸው

1 አንዲት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የምትገኝ ወጣት እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “አንዳንድ ጊዜ ወጣቶች በሕይወት ውስጥ በጣም አስቸጋሪ በሆነው ወቅት ላይ እንደሚገኙ ይሰማኛል። ዝሙት በሚፈጽሙ፣ አደገኛ ዕፆች በሚወስዱ እንዲሁም የአልኮል መጠጦችን አላግባብ በሚጠቀሙ ሰዎች መካከል እንገኛለን።” እናንተስ እንደዚህ ይሰማችኋል? የሚሰማችሁ ከሆነ እንዲህ ያሉትን መጥፎ ተጽእኖዎች ለመዋጋት ምን የሚረዳችሁ ይመስላችኋል? እምነት ያስፈልጋችኋል። የይሖዋ መንገዶች ትክክል ስለመሆናቸው ጠንካራ እምነት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል። ይህንን የመሰለ እምነት ከሌላችሁ ይሖዋን ‘ደስ ማሰኘት አትችሉም።’ (ዕብ. 11:​6) በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘታችሁ የጸና ክርስቲያናዊ እምነታችሁን እንዲሁም ከመጥፎ ነገሮች ለመራቅ ያደረጋችሁትን ቁርጥ ውሳኔ ያጠናክርላችኋል።

2 ስብሰባዎች ብዙ ጥቅም ይሰጧችኋል:- ከቅርብ ጓደኞች ጋር ሆኖ ጣፋጭ ምግብ መመገብን አስደሳች የሚያደርገው ምንድን ነው? ለጤና ተስማሚ የሆነ ምግብ መመገቡ ብቻ ሳይሆን ዘና ያለ ሁኔታ የሰፈነበት የወዳጅነት መንፈስ መኖሩ ጭምር አይደለምን? ስብሰባዎቻችንም በመንፈሳዊ ሁኔታ ከዚህ ጋር የሚመሳሰል አስደሳች አጋጣሚ ይፈጥሩላችኋል።

3 ስብሰባዎች ላይ ውይይት የሚደረግባቸው ነጥቦች የሚያንጹ ናቸው። ነጥቦቹ በዕለታዊ ሕይወታችሁ ከሚያጋጥሙአችሁ ችግሮች አንስቶ አስደናቂ በሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ላይ እስከሚደረገው ጥናት ድረስ ብዙ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚሸፍኑ ናቸው። የተሻለ ሕይወት መኖር የምትችሉትና በመንገዳችሁ ላይ የሚያጋጥሟችሁን ችግሮች መወጣት የምትችሉት እንዴት እንደሆነ የሚያስተምሩ ተግባራዊ ሐሳቦች ይቀርባሉ። በስብሰባዎች ላይ ከሁሉ የተሻሉ ጓደኞች ማግኘት ትችላላችሁ። በተጨማሪም አስደሳችና አስተማማኝ መንፈሳዊ ሁኔታ ሰፍኖ ትመለከታላችሁ። (መዝ. 133:​1) አንዲት ወጣት የሚከተለውን ማለቷ አያስገርምም:- “ቀኑን ሙሉ ትምህርት ቤት ስውል በጣም እዳከማለሁ። ሆኖም ስብሰባዎች ለሚቀጥለው የትምህርት ቀን መንፈሴ የሚታደስባቸው እንደ በረሃ ገነት ያሉ ቦታዎች ናቸው።” ሌላኛዋም ወጣት እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “ይሖዋን ከሚያፈቅሩ ጋር ይበልጥ መቀራረብ ወደ እርሱ ተጠግቼ እንድኖር እንደሚረዳኝ ተገንዝቤአለሁ።”

4 በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በመመዝገብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች መሰብሰብ፣ ንግግር ማዘጋጀት ከዚያም በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ለአድማጮች በውይይት መልክ ማቅረብን ትማራላችሁ። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ሕይወት አድን እውነት በጥሩ ችሎታ ለሌሎች ለማስተማር የሚያስችል ሥልጠና ማግኘት ያለውን ጥቅም እስቲ አስቡት! ወጣቶች እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሥልጠና ከጉባኤ ሌላ የት ማግኘት ይችላሉ?

5 ከስብሰባዎች ይበልጥ መጠቀም የሚቻልበት መንገድ:- ከስብሰባዎች የላቀ ጥቅም ለማግኘት ሦስት ወሳኝ ነገሮች ያስፈልጋሉ። እነዚህም ዝግጅት፣ ተሳትፎና የተማሩትን ተግባራዊ ማድረግ ናቸው።

6 ለስብሰባዎች ተዘጋጁ:- ዘወትር ለስብሰባዎች ለመዘጋጀት ጊዜ መድቡ። የትምህርት ቤት ሥራ፣ የትርፍ ጊዜ ሥራ ወይም መዝናኛዎች በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ የሚጠኑትን ጽሑፎች አስቀድማችሁ ለመዘጋጀት የሚያስፈልጋችሁን ጊዜ እንዲያሟጥጥባችሁ አትፍቀዱ። ለዚህም ጥሩ የሆነ ልማድ ማዳበር ይጠቅማችኋል። በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ የሚቀርበውን ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ኘሮግራም ተከታትሎ ማንበብ የመጀመሪያውና ቅድሚያ ልትሰጡት የሚገባ ነገር ነው። የተመደቡትን ምዕራፎች ለማንበብና ባነበባችሁት ላይ ለማሰላሰል በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ መመደብ ይበቃል። ለጉባኤ የመጽሐፍ ጥናትና ለመጠበቂያ ግንብ ጥናት ለመዘጋጀት ጊዜ መድቡ። አንዳንዶች ይህን የሚያደርጉት ስብሰባዎቹ ከመደረጋቸው ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ቀን በፊት ነው። በተቻለ መጠን ለእያንዳንዱ ሳ ምንት የተመደቡትን የአገልግሎት ስብሰባ ክፍሎች ለመዘጋጀትም እንዲሁ አድርጉ።

7 ተሳትፎ አድርጉ:- ኢየሱስ በ12 ዓመቱ በቤተ መቅደሱ ተገኝቶ ያዳምጥ፣ ጥያቄዎች ይጠይቅ እንዲሁም መልስ ይሰጥ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ሉቃስ 2:​46, 47) በሌላ አነጋገር ኢየሱስ በውይይቱ ሙሉ በሙሉ ተካፋይ ነበር። ተሳትፎ ለማድረግ ይበልጥ በጣራችሁ መጠን ከስብሰባዎች የበለጠ ጥቅም ታገኛላችሁ።​—⁠ምሳሌ 15:​23

8 ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡትን ትምህርቶች በትኩረት መከታተል ያስፈልጋችኋል። አንዳንድ ጊዜ ንግግር ማዳመጥ ከመስጠት ይልቅ ይከብዳል። ለምን? ሌላ ሰው በሚናገርበት ወቅት አእምሮ ሽርሽር ሊሄድ ስለሚችል ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን ዝንባሌ መዋጋት የምትችሉት እንዴት ነው? ማስታወሻ በመያዝ ይህንን ዝንባሌ ማሸነፍ ትችላላችሁ። ከስብሰባው በኋላ መልሳችሁ ማየት የምትፈልጓቸውን አስፈላጊ ነጥቦች በማስታወሻችሁ ላይ አስፍሩ። ማስታወሻ መያዛችሁ አእምሮአችሁ በኘሮግራሙ ላይ እንዲያተኩር ይረዳችኋል። ተናጋሪው የሚያነባቸውን ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱሳችሁን አውጥታችሁ ተከታተሉ።

9 በተጨማሪም ስብሰባዎች ላይ በሚቀርበው በእያንዳንዱ የጥያቄና መልስ ውይይት ላይ ተሳትፎ የማድረግ ግብ ይኑራችሁ። ለማለት የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ በጥንቃቄ ካሰባችሁ ይበልጥ ትጠቀማላችሁ። ምሳሌ 15:​28 “የጻድቅ ልብ መልሱን ያስባል” ይላል።

10 የተማራችሁትን በተግባር ላይ አውሉት:- የመጨረሻው እርምጃ የተማራችሁት ነገር ‘በእናንተ እንዲሠራ’ ማድረግ ነው። (1 ተ⁠ሰ. 2:​13) በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ የተማራችኋቸውን ጥሩ ጥሩ ነጥቦች በተግባር ላይ ስታውሏቸው ወደ ይሖዋ አምላክ ይበልጥ ትቀርባላችሁ። ይሖዋ እውን ይሆንላችኋል። እንዲሁም እውነትን የራሳችሁ በማድረግ ‘በእውነት ስትሄዱ’ ታላቅ ደስታና እርካታ ታገኛላችሁ።​—⁠3 ዮሐ. 4

11 ወጣት ወንድሞችና እህቶች፣ ለስብሰባዎች አዘውትራችሁ ከተዘጋጃችሁ፣ ተሳትፎ ካደረጋችሁና የተማራችሁትን ተግባር ላይ ካዋላችሁ ስብሰባዎች ሙሉ በሙሉ አስደሳች ይሆኑላችኋል። ወዲያውም ከስብሰባዎች ማግኘት የሚገባችሁን ጥቅም ሁሉ ታገኛላችሁ። እምነታችሁም ሆነ ለሰማያዊው አባታችሁ ለይሖዋ ታማኝ ሆኖ ለመገኘት ያደረጋችሁት ቁርጥ ውሳኔ ይጠናከራል።​—⁠መዝ. 145:​18

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ