የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
  • የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት ምን አስተምሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ስለ አምላክ መንግሥት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯል
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 1 ገጽ 12-13
የፀሐይ ነጸብራቅ ምድር ላይ አርፎ

የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?

ኢየሱስ ተከታዮቹን እንደሚከተለው ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል፦ “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ። መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።” (ማቴዎስ 6:9, 10) ለመሆኑ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ምን ነገሮችን ያከናውናል? ይህ መንግሥት እንዲመጣ መጸለይ ያለብንስ ለምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ኢየሱስ ነው።

ሉቃስ 1:31-33፦ “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤ ይሖዋ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”

ኢየሱስ በዋነኝነት የሰበከው ስለ አምላክ መንግሥት ነው።

ማቴዎስ 9:35፦ “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በየከተማውና በየመንደሩ ይዞር ጀመር።”

ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት የሚመጣው መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ምልክት ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል።

ማቴዎስ 24:7፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤ በተለያየ ስፍራ የምግብ እጥረትና የምድር ነውጥ ይከሰታል።”

በአሁኑ ጊዜ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በዓለም ዙሪያ ስለ አምላክ መንግሥት እየሰበኩ ነው።

ማቴዎስ 24:14፦ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

የሚገኝበት ቦታ። የአምላክ መንግሥት አምላክ በሰማይ ላይ ያቋቋመው መስተዳድር ነው።—ዳንኤል 2:44፤ ማቴዎስ 4:17

ዓላማው። የአምላክ መንግሥት ምድር ገነት እንድትሆን እንዲሁም ከሕመምና ከሞት ነፃ በሆነ ዓለም ውስጥ ሁሉም ሰው በሰላምና በአንድነት እንዲኖር ያደርጋል።—መዝሙር 37:11, 29

ገዢዎቹ። አምላክ ኢየሱስን በሰማይ ላይ ንጉሥ እንዲሆን ሾሞታል፤ እንዲሁም ከምድር የተመረጡ 144,000 ሰዎች ከኢየሱስ ጋር ይገዛሉ።—ሉቃስ 1:30-33፤ 12:32፤ ራእይ 14:1, 3

ተገዢዎቹ። የዚህ መንግሥት ተገዢዎች በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች ለኢየሱስ ሥልጣን በፈቃደኝነት ይገዛሉ እንዲሁም የመንግሥቱን ሕጎች ይታዘዛሉ።—ማቴዎስ 7:21

የሰው ልጆችን ለመግዛት ከሁሉ የተሻለ ብቃት ያለው ኢየሱስ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ብቃት ያለውና አፍቃሪ መሪ እንደሚሆን አረጋግጧል። እንዴት?

  • ለድሆች ያዝን ነበር።—ሉቃስ 14:13, 14

  • ሙስናንና ግፍን ይጠላ ነበር።—ማቴዎስ 21:12, 13

  • የተፈጥሮ ኃይሎችን ይቆጣጠር ነበር።—ማርቆስ 4:39

  • በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግቧል።—ማቴዎስ 14:19-21

  • ለታመሙ ሰዎች ያዝን የነበረ ሲሆን ከበሽታቸው ፈውሷቸዋል።—ማቴዎስ 8:16

  • የሞቱ ሰዎችን አስነስቷል።—ዮሐንስ 11:43, 44

የአምላክ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

የአምላክ መንግሥት ተገዢ ከሆንክ በአሁኑ ጊዜም ደስተኛ ሕይወት መምራት ትችላለህ። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

  • የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች “ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጥረት” ያደርጋሉ።—ዕብራውያን 12:14

  • የአምላክ መንግሥት ተገዢ የሆኑ ባለትዳሮች ስለሚዋደዱና ስለሚከባበሩ ሰላምና አንድነት የሰፈነበት ቤተሰብ ይኖራቸዋል።—ኤፌሶን 5:22, 23, 33

  • የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች ‘ለመንፈሳዊ ነገሮች ጥማት’ ስላላቸው ደስተኛና አርኪ ሕይወት ይመራሉ።—ማቴዎስ 5:3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ