የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
  • የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መልካም አስተዳደር
  • ጥሩ ጤንነት
  • ዓለም አቀፋዊ ሰላም
  • ምድር በጥሩ ሰዎች ትሞላለች
  • ምድር ገነት ትሆናለች
  • ተስፋ
    ንቁ!—2018
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አምላክ ሥቃይና መከራ እንዲኖር የፈቀደበት ጊዜ ማብቂያው ተቃርቧል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የአምላክ መንግሥት—ከሁሉ የላቀ መስተዳድር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
ሰዎች ገነት ውስጥ በደስታ ሲኖሩ

የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?

‘የወደፊቱ ጊዜ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?’ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ በሁላችንም ሕይወት ላይ ለውጥ የሚያመጡ ወሳኝ ክስተቶች በቅርቡ እንደሚፈጸሙ ይናገራል።

ኢየሱስ “የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እርግጠኞች” መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ነግሮናል። (ሉቃስ 21:31) ታላላቅ ጦርነቶች፣ ከባባድ የምድር ነውጦች፣ የምግብ እጥረት፣ ቸነፈር እንዲሁም ሌሎች ነገሮች እንደሚከሰቱ ተንብዮአል። በአሁኑ ጊዜ እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ እየተመለከትን ነው።—ሉቃስ 21:10-17

መጽሐፍ ቅዱስ “በመጨረሻዎቹ ቀናት” የሰዎች ባሕርይ በእጅጉ እንደሚበላሽ ይናገራል። እባክህ 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ተመልከት። በዛሬው ጊዜ ያሉ ሰዎች ጥቅሱ ላይ የተዘረዘሩትን ባሕርያት እንደሚያንጸባርቁ አስተውለህ መሆን አለበት፤ ይህ ደግሞ ትንቢቱ በዘመናችን እየተፈጸመ እንዳለ ያረጋግጣል።

ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት የሚናገሩት ትንቢቶች መፈጸማቸው ምን ያመለክታል? የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ያለውን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የሚቀይርበት ጊዜ በጣም እንደቀረበ ያመለክታል። (ሉቃስ 21:36) አምላክ ለምድርም ሆነ ለሰው ልጆች መልካም ነገሮችን እንደሚያደርግ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቃል ገብቷል። አንዳንድ ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት።

መልካም አስተዳደር

“ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ እንዲያገለግሉት የገዢነት ሥልጣን፣ ክብርና መንግሥት [ለኢየሱስ] ተሰጠው። የገዢነት ሥልጣኑ የማያልፍና ዘላለማዊ፣ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።”—ዳንኤል 7:14

ምን ማለት ነው? አምላክ ዓለም አቀፋዊ መንግሥት ያቋቋመ ሲሆን ልጁን ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል፤ በዚህ አስደናቂ መንግሥት ሥር አስደሳች ሕይወት መምራት ትችላለህ።

ጥሩ ጤንነት

የአካል ጉዳተኛ የሆነች አንዲት ትንሽ ልጅ ከተሽከርካሪ ወንበሯ ተነስታ ስትራመድ

“በዚያም የሚቀመጥ ማንኛውም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ አይልም።”—ኢሳይያስ 33:24

ምን ማለት ነው? ሕመምም ሆነ የአካል ጉዳት ሳያጋጥምህ ለዘላለም መኖር ትችላለህ።

ዓለም አቀፋዊ ሰላም

የተሰባበረ ጠመንጃ

“ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:9

ምን ማለት ነው? ጦርነትም ሆነ የሚያስከትላቸው ችግሮች አይኖሩም።

ምድር በጥሩ ሰዎች ትሞላለች

“ክፉዎች አይኖሩም፤ . . . የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ።”—መዝሙር 37:10, 11

ምን ማለት ነው? ክፉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ ምድር ላይ የሚኖሩት አምላክን የሚታዘዙ ሰዎች ብቻ ናቸው።

ምድር ገነት ትሆናለች

“ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።”—ኢሳይያስ 65:21, 22

ምን ማለት ነው? መላዋ ምድር ውብ ገነት ትሆናለች። በዚያ ወቅት የአምላክ ‘ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም’ የምናቀርበው ጸሎት ምላሽ ያገኛል።—ማቴዎስ 6:10

ሰዎች ገነት ውስጥ በደስታ ሲኖሩ
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ