የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/01 ገጽ 4
  • ይሖዋ ኃይል ይሰጣል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ ኃይል ይሰጣል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ለደከሙት ኃይል ይሰጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • “ይሖዋንና እርሱ የሚሰጠውን ብርታት ፈልጉ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ይሖዋ ብርታት ይሰጣችኋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ይሖዋ ለደከሙት ኃይል ይሰጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 2/01 ገጽ 4

ይሖዋ ኃይል ይሰጣል

1 ስለ ሐዋርያው ጳውሎስ ስታስብ ምን ይሰማሃል? የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ስናነብ በይሖዋ አገልግሎት ያሳየውን ትጋት እናስተውላለን። ጳውሎስ ያደረጋቸውን ነገሮች በሙሉ ማከናወን የቻለው እንዴት ነው? “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ [“በእርሱ፣” NW ] ሁሉን እችላለሁ” በማለት ተናግሯል። (ፊልጵ. 4:​13) እኛም ይሖዋ ከሚሰጠው ኃይል ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን። እንዴት? እኛን በመንፈሳዊ ለማደስና ለማበረታታት በተደረገልን ስድስት ዝግጅቶች በመጠቀም ነው።

2 የአምላክ ቃል:- አካላዊ ጥንካሬ ለማግኘት የግድ ምግብ መብላት እንደሚያስፈልገን ሁሉ በመንፈሳዊ ሕያው ሆነን እንድንቀጥል ራሳችንን በአምላክ ቃል መመገብ ይገባናል። (ማቴ. 4:​4) መጽሐፍ ቅዱስ የሚያበረታ ኃይል ይሰጠናል። ለእውነት ያለንን ቅንዓትና ግለት ጠብቀን ለማቆየት ቢቻል በየዕለቱ ትርጉም ያለው የግል ጥናት ማድረግና ማሰላሰል ይኖርብናል።​—⁠መዝ. 1:​2, 3

3 ጸሎት:- በተለይ ልዩ ዕርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ወደ ይሖዋ መቅረብ በጣም አስፈላጊ ነው። በጸሎት ቀርበው ለሚጠይቁ ሰዎች በመንፈሱ አማካኝነት ብርታት የሚጨምር ኃይል ይሰጣቸዋል። (ሉቃስ 11:​13፤ ኤፌ. 3:​16) ቅዱሳን ጽሑፎች ‘በጸሎት እንድንጸና’ ያበረታቱናል። (ሮሜ 12:​12) አንተስ እንዲህ እያደረግህ ነው?

4 ጉባኤ:- በተጨማሪም ከጉባኤ ስብሰባዎችና ጉባኤ ላይ ከምናገኛቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ካለን ሞቅ ያለ ወዳጅነት ማበረታቻና ማጽናኛ ማግኘት እንችላለን። (ዕብ. 10:​24, 25) ወንድሞችና እህቶች ችግር በሚያጋጥመን ጊዜ ያበረታቱናል እንዲሁም ፍቅራዊ እገዛ ያደርጉልናል።​—⁠ምሳሌ 17:​17፤ መክ. 4:​10

5 የመስክ አገልግሎት:- በመስክ አገልግሎት አዘውትረን መካፈላችን ትኩረታችን በአምላክ መንግሥትና በበረከቶቹ ላይ እንዲያርፍ ይረዳናል። ስለ ይሖዋ እንዲያውቁ ሌሎችን ስንረዳ መንፈሳችን ይነቃቃል። (ሥራ 20:​35) የመንግሥቱ አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄደን ለማገልገል ወይም በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመካፈል የሚያስችል ሁኔታ ያለን ሁላችንም አይደለንም፤ ሆኖም በሌሎች መንገዶች በአገልግሎት ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማድረግ እንችላለን።​—⁠ዕብ. 6:​10-12

6 ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች:- ሽማግሌዎች ከሚሰጡት ማበረታቻና ድጋፍ ጥቅም እናገኛለን። ይሖዋ በሥራቸው የሚገኘውን የአምላክ መንጋ እንዲጠብቁ ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል። (1 ጴ⁠ጥ. 5:​2) ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች ጳውሎስ በዘመኑ እንዳደረገው ተዘዋውረው የሚጎበኟቸውን ጉባኤዎች ያንጻሉ።​—⁠ሮሜ 1:​11, 12

7 የታመኑ ሰዎች ምሳሌ:- ጥንት የኖሩትንም ሆነ በዘመናችን ያሉትን የታመኑ አገልጋዮች ገንቢ ምሳሌ መመርመሩ ኃይላችንን ያድስልናል። (ዕብ. 12:​1) ኃይልህን ማደስ በሚያስፈልግህ ጊዜ ከመጽሔቶቻችን ላይ አንድ አበረታች የሕይወት ታሪክ፣ በዓመት መጽሐፍ ላይ የወጣ ገንቢ ሪፖርት ወይም አዋጅ ነጋሪዎች ከተባለው መጽሐፍ ላይ በዚህ ዘመን ያሉ የይሖዋ ምሥክሮችን አስደናቂ ታሪክ ለምን አታነብብም?

8 ዛሬ በ90ዎቹ ዕድሜው አጋማሽ ላይ የሚገኝ አንድ ወንድም እውነትን የሰማው ገና ታዳጊ ወጣት ሳለ ነበር። ገና በወጣትነቱ እምነቱ ፈተና ላይ ወድቆ ነበር። በመጀመሪያ፣ በጉባኤ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች የይሖዋን ድርጅት ትተው ወጡ። ከዚያም ከቤት ወደ ቤት የሚደረገው አገልግሎት ፈተና ሆኖበት ነበር። የሆነ ሆኖ ሁልጊዜ በይሖዋ ይታመን ነበር። ብዙም ሳይቆይ ለአገልግሎቱ ፍቅር አደረበት። በአሁኑ ጊዜስ? የተሟላ ጤንነት ባይኖረውም እስከዚህ ጊዜ ድረስ የአስተዳደር አካል አባል ሆኖ የሚያገለግል የብሩክሊን ቤተሰብ አባል ነው። የይሖዋን ድርጅት ሙጥኝ ብሎ በመኖሩ ተጸጽቶ አያውቅም።

9 የብሪታኒያ ቤቴል ቤተሰብ አባል የሆነች አንዲት እህት የተጠመቀችው ገና የ13 ዓመት ወጣት ሳለች ነበር። በቀጣዩ ዓመት ከወንድሟ ጋር በአቅኚነት ማገልገል የጀመሩ ሲሆን በሁለተኛው ዓመት አባቷ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ባሳየው የገለልተኝነት አቋም ምክንያት ታሰረ። ይሖዋ ኃይል እንዲሰጣት በእሱ በመታመን እውነተኛውን አምላክ ማገልገሏን ቀጠለች። ከጊዜ በኋላ አንድ ታማኝ ወንድም አገባችና በአንድነት የይሖዋን ፈቃድ ማድረጋቸውን ቀጠሉ። በትዳር ዓለም 35 ዓመታት ካሳለፉ በኋላ ድንገት ባለቤትዋ አረፈ። በዚህ ጊዜም ይሖዋ አበርትቷታል። የይሖዋ ምድራዊ ቤተሰብ አባል በመሆን ለዘላለም ማገልገልን ግብ በማድረግ እስከአሁን ጸንታለች።

10 ይሖዋ የታመኑ አገልጋዮቹን ይደግፋቸዋል እንዲሁም ኃይላቸውን ያድስላቸዋል። “ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፣ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።” ከላይ የተጠቀሱትን ስድስት ዝግጅቶች በመጠቀም ከማይነጥፈው የኃይል ምንጭ መጠቀም እንችላለን። “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ . . . ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም” የሚለውን አስታውስ። (ኢሳ. 40:​29-​31) ጳውሎስ ብርታት ለማግኘት ሙሉ በሙሉ በይሖዋ እንደተማመነ ሁሉ እኛም እንዲሁ ማድረግ ይገባናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ