የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/01 ገጽ 1
  • በመከሩ ሥራ በሙሉ አቅማችሁ ተካፈሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በመከሩ ሥራ በሙሉ አቅማችሁ ተካፈሉ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዝመራው እንደነጣ ተመልከቱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • ደስተኛ የመከሩ ሠራተኞች ሁኑ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • በመከሩ ሥራ ወደፊት ግፉ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • በታላቁ መንፈሳዊ የመከር ሥራ የተሟላ ተሳትፎ ይኑራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 5/01 ገጽ 1

በመከሩ ሥራ በሙሉ አቅማችሁ ተካፈሉ

1 ጥንት የነበሩት የይሖዋ ነቢያትም ሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መሰብሰብ ሥራ ተናግረዋል። (ኢሳ. 56:​8፤ ሕዝ. 34:​11፤ ዮሐ. 10:​16) ዛሬ በመላው ዓለም በሚሰበከው የመንግሥት ምሥራች አማካኝነት እየተከናወነ ያለውም ተመሳሳይ ሥራ ነው። (ማቴ. 24:​14) አምላክን በሚያገለግሉትና በማያገለግሉት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት በግልጽ እየታየ ነው። (ሚል. 3:​18) ይህ ለእኛ ምን ማለት ነው?

2 የግል ኃላፊነት:- በክርስቲያናዊው አገልግሎት ግንባር ቀደም ሆኖ በመሰለፍ ሙሉ ተሳትፎ ያደረገው ጳውሎስ ከተወልን ምሳሌ መማር እንችላለን። ሰዎች ሁሉ ምሥራቹን የመስማት አጋጣሚ አግኝተው ይድኑ ዘንድ የመስበክ ግዴታ እንዳለበት ተሰምቶት ነበር። ይህም ሳያሰልስ ለሁሉም ሰው እንዲሰብክ አነሳስቶታል። (ሮሜ 1:​14-17) ዛሬ የሰው ዘር ከገባበት አስጨናቂ ሁኔታ አንጻር በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች በመስበክ ረገድ ያለብን ኃላፊነት ከእነርሱ የላቀ አይደለምን?​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 9:​16

3 አፋጣኝ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ:- የስብከቱ ሥራ ከሕይወት አድን ፍለጋ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ጊዜው ከማለፉ በፊት ሰዎችን ማግኘትና ከአደጋ እንዲያመልጡ መርዳት ይገባል። የቀረው ጊዜ አጭር ነው። የሰዎች ሕይወት አደጋ ተጋርጦበታል! ኢየሱስ “የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት” ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ማሳሰቡ ምንም አያስገርምም።​—⁠ማቴ. 9:​38

4 ብዙ የመንግሥቱ ሠራተኞች የጊዜውን አጣዳፊነት በመረዳት ሕይወት አድን በሆነው በዚህ ሥራ ያላቸውን ተሳትፎ ከፍ አድርገዋል። በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ሂሮሂሳ የተባለ ወጣት በነጠላ ወላጅ በሚተዳደር ቤት ውስጥ ከአራት ታናናሽ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ይኖራል። ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት እየተነሳ ጋዜጣ በማደል ቤተሰቡን ይደጉማል። ያም ሆኖ ሂሮሂሳ በአገልግሎት ይበልጥ መካፈል ስለፈለገ የዘወትር አቅኚ ሆኗል። ሁለተኛ በማይደገመው በዚህ ሥራ ይበልጥ ተሳትፎ ማድረግ የምትችሉበት መንገድ ይኖር ይሆን?

5 ‘የቀረው ዘመን አጭር ነው።’ (1 ቆ⁠ሮ. 7:​29) ስለሆነም በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ በመከናወን ላይ በሚገኘውና ከምንም በላይ አስፈላጊ በሆነው የመንግሥቱን ምሥራች የመስበክና ደቀ መዛሙርት የማድረግ ሥራ ለመካፈል የሚቻለንን ሁሉ እናድርግ። ኢየሱስ ይህን አገልግሎት ከመከር ሥራ ጋር አመሳስሎታል። (ማቴ. 9:​35-38) በመከሩ ሥራ በሙሉ አቅማችን ስንካፈል የድካማችን ፍሬ በራእይ 7:​9, 10 ላይ የተገለጹት እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው አምላኪዎች አባል የሚሆኑ ሰዎች እንዲጨመሩ መርዳት ሊሆን ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ