ኖኅ —አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ ከተሰኘው የቪዲዮ ፊልም ሁሉም ሰው ሊማር ይችላል
ከዘፍጥረት 6:1 እስከ 9:19 ያለውን አንብቡ ወይም ከልሱት። ከዚያም ኖኅ የተሰኘውን የቪዲዮ ፊልም ተመልከቱና እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ:- (1) በኖኅ ዘመን የነበረው ዓለም ምን ይመስል ነበር? እንደዚያ ሊሆን የቻለውስ ለምን ነበር? (2) ኖኅን በጣም የተለየ እንዲሆን ያደረገው ምን ነበር? አምላክ ምን ሥራ ሰጠው? ለምንስ? (3) መርከቡ የተሠራው የት ሊሆን ይችላል? ግንባታው ምን ያህል ጊዜ ፈጀ? መጠኑ ምን ያህል ነበር? (4) ኖኅና ቤተሰቡ መርከቡን ከመሥራት በተጨማሪ ምን ማድረግ ነበረባቸው? (5) በሩ ከተዘጋ በኋላ በመርከቡ ውስጥ ምን ዓይነት ሁኔታ የሚኖር ይመስልሃል? (6) አንተ ከጥፋት ውኃው ብትተርፍ ምን ይሰማህ ነበር? (7) የጥፋት ውኃውን የሚያስታውሰን ምን ነገር አልፎ አልፎ እንመለከታለን? ትርጉሙስ ምንድን ነው? (8) ስለ ኖኅ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ስለ ራስህ፣ ስለ ቤተሰብህና አምላክ እንድንሠራው ስለ ሰጠን ሥራ ምን አስተምሮሃል? (9) ኖኅና ቤተሰቡን በገነት ስታገኛቸው ልትጠይቃቸው የምትፈልጋቸው ጥያቄዎች ምንድን ናቸው? (10) ይህን የቪዲዮ ፊልም እንዴት ልትጠቀምበት አስበሃል?