የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/02 ገጽ 4
  • ባላችሁ የምትረኩ ሁኑ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ባላችሁ የምትረኩ ሁኑ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ባለጸጋ መሆን ትችላለህ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ቁሳዊ ነገሮችን ሳይሆን የአምላክን መንግሥት ፈልጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ‘ምን ጊዜም አስቀድመህ መንግሥቱን ፈልግ’
    እውነተኛው አንድ አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 6/02 ገጽ 4

ባላችሁ የምትረኩ ሁኑ

1 ቅዱሳን ጽሑፎች ለቤተሰባችን የሚያስፈልገውን ቁሳዊ ነገር እንድናሟላ የሚ​ያሳስቡን ቢሆንም የሕይወታችን ዋነኛ ግብ ግን ይህ ሊሆን አይገባውም። መቅደም ያለባቸው መንፈሳዊ ነገሮች ናቸው። (ማቴ. 6:33፤ 1 ጢ⁠ሞ. 5:8) በዚህ ‘የሚያስጨንቅ ዘመን’ ሚዛንን ጠብቆ መኖር ቀላል አይደለም። (2 ጢ⁠ሞ. 3:1) ሚዛናችንን ጠብቀን እንድንኖር ምን ሊረዳን ይችላል?

2 የመጽሐፍ ቅዱስን አመለካከት ያዙ፦ የአምላክ ቃል ሃብትን ማሳደድ መንፈሳዊ ውድቀት ሊያስከትል እንደሚችል ያስጠነቅቀናል። (መክ. 5:10፤ ማቴ. 13:22፤ 1 ጢ⁠ሞ. 6:9, 10) በዚህ ወሳኝ በሆነ የመጨረሻ ዘመን በሰብዓዊ ሥራ ወይም ገንዘብ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ከመጠን በላይ ተጠላልፈን እንደ ስብሰባ፣ የግል ጥናትና አገልግሎት የመሳሰሉ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን በሕይወታችን ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ብናስቀምጥ አደገኛ ይሆናል። (ሉቃስ 21:34-36) ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ “ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፣ እርሱ ይበቃናል” የሚል አመለካከት እንድናዳብር ይመክረናል።​—⁠1 ጢ⁠ሞ. 6:7, 8

3 እንዲህ ሲባል ግን ክርስቲያኖች በድህነት መኖር አለባቸው ማለት አይደለም። ከዚያ ይልቅ ይህ ምክር በቁሳዊ ረገድ በእርግጥ የሚያስፈልገን ምን እንደሆነ ለይተን እንድናውቅ ይረዳናል። እነዚህም ምግብ፣ ልብስና የምንኖርበት በቂ መጠለያ ናቸው። ለሕይወት የሚያስፈልጉንን ነገሮች ካገኘን የቅንጦት ኑሮ ለመኖር ስንል መድከም አይኖርብንም። ዕቃ ለመግዛት ወይም ተጨማሪ ሥራ ለመያዝ ስናስብ ‘ይህ በእርግጥ ያስፈልገኛል?’ ብለን ራሳችንን መጠየቃችን ተገቢ ነው። እንዲህ ማድረጋችን “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፣ ያላችሁም ይብቃችሁ” የሚለውን በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈውን ምክር ተግባራዊ እንድናደርግ ያስችለናል።​—⁠ዕብ. 13:5

4 በይሖዋ ከታመንን እርሱ ይደግፈናል። (ምሳሌ 3:5, 6) የዕለት ጉርስ ለማግኘት ጠንክረን መሥራት ያለብን ቢሆንም ሕይወታችን በእነዚህ ነገሮች ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ አይኖርብንም። ያለን ጥቂትም ይሁን ብዙ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ይሖዋ እንደሚሰጠን እንተማመናለን። (ፊልጵ. 4:11-13) በውጤቱም ባለን የምንረካ ከመሆናችንም በተጨማሪ ሌሎች ብዙ በረከቶችን እናገኛለን።

5 የሌሎችን የእምነት ምሳሌ ኮርጁ፦ ሴት ልጅዋን በእውነት መንገድ ኮትኩታ ታሳድግ የነበረች አንዲት ነጠላ ወላጅ ቀስ በቀስ ኑሮዋን ቀላል አደረገች። ምቾት ያለው ቤት የነበራት ቢሆንም ይህን ቤቷን ለቅቃ በመጀመሪያ አነስተኛ በሆነ ቤት ከጊዜ በኋላ ደግሞ በአፓርተማ ውስጥ መኖር ጀመረች። ይህም ለሥራ የምታውለውን ጊዜ እንድትቀንስና በአገልግሎቷ ረዥም ሰዓት እንድትካፈል አስችሏታል። ልጅዋ አድጋ ካገባች በኋላ ይህች እህት ገቢዋ እንዲቀንስ የሚያደርግባት ቢሆንም እንኳ ዕድሜዋ ከመድረሱ በፊት ጡረታ ወጣች። አሁን ይህች እህት የዘወትር አቅኚ ከሆነች ሰባት ዓመት የሞላት ሲሆን መንግሥቱን በሕይወቷ ውስጥ ለማስቀደም ስትል ቁሳዊ መሥዋዕቶችን በመክፈሏ ምንም አትጸጸትም።

6 አንድ ሽማግሌና ሚስቱ ሦስት ልጆች እያሳደጉ አቅኚ ሆነው ለብዙ ዓመታት አገልግለዋል። ቤተሰቡ በሙሉ ምኞታቸውን ለማሟላት ከመጣር ይልቅ የሚያስፈልጋቸውን ካገኙ በዚያ መርካትን ተምረዋል። ወንድም እንዲህ ይላል:- “ኑሯችንን በጣም ቀላል ማድረግ ነበረብን። የተቸገርንባቸው ጊዜያት ቢኖሩም ይሖዋ የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል። . . . ቤተሰቤ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ሲያስቀድም ስመለከት ትክክለኛውን ነገር እያደረግን እንዳለ ስለሚሰማኝ እርካታ አገኛለሁ።” ባለቤቱም “[ባሌ] በመንፈሳዊ ጉዳዮች ተጠምዶ ስመለከት ጥልቅ የሆነ የእርካታ ስሜት ይሰማኛል” ብላለች። ልጆቹም ቢሆኑ ወላጆቻቸው ይሖዋን በሙሉ ጊዜያቸው ለማገልገል በመወሰናቸው ደስተኞች ናቸው።

7 ቁሳዊ ነገሮችን ከማሳደድ ይልቅ በዚህ መንገድ ለአምላክ ያደሩ ሰዎች አሁንም ሆነ ወደፊት በሚመጣው ሕይወት የተትረፈረፉ በረከቶችን እንደሚያገኙ መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ይሰጣል።​—⁠1 ጢ⁠ሞ. 4:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ