የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፕሮግራም ወደፊት በመግፋት ላይ ነው
1 በ1983 “የመንግሥቱ አንድነት” በሚል ጭብጥ ዩናይትድ ስቴትስ በተደረገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ በመላው ዩናይትድ ስቴትስና ካናዳ የመንግሥት አዳራሾች ለመገንባትና ነባር ሕንጻዎችን አስተካክሎ ለስብሰባ ለመጠቀም የሚካሄደውን ሥራ ለመደገፍ የገንዘብ መዋጮ የሚደረግበት ልዩ ዝግጅት መቋቋሙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ተነግሮ ነበር። እንዲህ ካለው አነስተኛ ጅምር ተነስተን ምን ዓይነት በረከቶች እንደምናገኝ በጊዜው አልተገነዘብንም ነበር። በመዝሙር 92:4 ላይ “አቤቱ፣ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና” የሚለው ጥቅስ ሙሉ ፍጻሜውን ሲያገኝ ለመመልከት ችለናል።
2 በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ ያሉትን ነገሮች ስንመለከት በጣም እንደሰታለን። በዛሬው ጊዜ የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፕሮግራም ዓለም አቀፋዊ በሆነ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት በመካሄድ ላይ ነው። ሁላችንም በዚህ እንቅስቃሴ በሆነ መልኩ የመካፈል መብት አግኝተናል። እንደ አቅማችን የገንዘብ መዋጮ በማድረግ በዓለም ዙሪያ ተጨማሪ የአምልኮ ቦታዎች ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በገንዘብ መደገፍ እንችላለን። በተጨማሪም በርካታ ወንድሞች በፈቃደኝነት ተነሳስተው ንብረታቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ችሎታቸውንና ሙያቸውን በእንደዚህ ዓይነት ፕሮጄክቶች ላይ ያውላሉ። ይሖዋ መመሪያና ድጋፍ በመስጠቱና የጋራ ጥረታችንን አብዝቶ በመባረኩ መላው ዝግጅት ስኬታማ ሊሆን ችሏል።—መዝ. 127:1
3 ብዙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ጉባኤዎች ከተደረገው ጋር የሚመሳሰል ዝግጅት አድርገዋል። በበርካታ አገሮች በሚገኙ የመንግሥት አዳራሾች ውስጥ አስፋፊዎች ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ የሚያደርጉትን መዋጮ የሚከትቱበት የአስተዋጽኦ ሣጥን አለ። የመጋቢት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን በዚህ ፕሮግራም ላይ አንድ ማስተካከያ መደረጉን ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ጉባኤዎች ገልጾ ነበር። እንዲህ ይላል:- “ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ መዋጮ የሚደረግበት ዝግጅት በ1983 ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ወንድሞች ያደረጉት ልግስና ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታዎች የብድር ዝግጅት ለማቅረብ አስችሏል። እስካሁን ድረስ በዚህ አገር ውስጥ 2, 700 የሚያህሉ ጉባኤዎች ከዚህ ዝግጅት ተጠቃሚ ሆነዋል። ይህ ዝግጅት ባይኖር ኖሮ ብዙ ጉባኤዎች አዳዲስ የመንግሥት አዳራሾች መገንባትም ሆነ ሕንፃዎችን አድሶ መጠቀም አይችሉም ነበር። በአሁኑ ወቅት በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ ለሚገኙ ጉባኤዎች ብድር ለመስጠት ከዚህ የመዋጮ ገንዘብ ውስጥ የተወሰነውን መጠቀም በጣም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ማኅበሩና ካደረጋችሁት አስተዋጽኦ ተጠቃሚ የሚሆኑት ጉባኤዎች ይህንን ዝግጅት ለመደገፍ የምታደርጉትን ያልተቋረጠ ጥረት ያደንቃሉ።”
4 ይህ ማስታወቂያ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ጉባኤዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተካሄደ ባለው የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፕሮግራም ላይ እንዲካፈሉም ግብዣ አቅርቧል። ለመንግሥት አዳራሽ ግንባታ የተዋጣው ገንዘብ በዚህ አገር የሚካሄደውን የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ለማካሄድ የገንዘብ ብድር መስጠቱን ከመቀጠሉም በላይ በሌሎች አገሮች የሚገኙ ጉባኤዎች ያለባቸውን የመሰብሰቢያ ቦታ ችግር ለማቃለልም ያገለግላል። በነሐሴ 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ የወጣ አንድ ርዕስ እንዲህ በማለት ገልጿል:- “በመላው ዓለም መንግሥት አዳራሽ የሚያስፈልጋቸው ጉባኤዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ብቻ 3, 288 የሚያህሉ አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በመካከለኛውና በደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በምሥራቅ አውሮፓ የሚገኙ ናቸው።”
5 ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምን ውጤቶች ተገኝተዋል? የ2001 የዓመት መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- “በዚህ ዝግጅት በመጠቀም እስካሁን ድረስ በ30 አገሮች ውስጥ 453 የሚያህሉ የመንግሥት አዳራሾች የተገነቡ ሲሆን ሌሎች 727 የሚያህሉ አዳራሾች ደግሞ በመገንባት ላይ ናቸው። በእያንዳንዱ አገር በአካባቢው የተለመደውን የግንባታ ጥሬ ዕቃና የሕንጻ አሠራር ዘዴ በመጠቀም መደበኛ የመንግሥት አዳራሾችን ለመንደፍ ልዩ ትኩረት ሲሰጥ ቆይቷል። በኬንያ ጥርብ ድንጋይ ይጠቀማሉ፤ በቶጎ የሸክላ ጡብ መጠቀም የተለመደ ነው፤ በካሜሩን ደግሞ በሲሚንቶ የሚለሰኑ የአርማታ ግድግዳዎች በስፋት ይሠራባቸዋል። በዚህ መንገድ በአካባቢው ያሉ ወንድሞች በአገሪቱ የግንባታ ፕሮግራም ላይ ቁልፍ ቦታዎችን ሸፍነው ለመሥራት የሚያስፈልጋቸውን ችሎታ በፍጥነት እንዲቀስሙ ማድረግ ይቻላል።”
6 ይሖዋ ይህን ፕሮግራም እየባረከው እንዳለ በአፍሪካ አህጉር እየተካሄደ ያለውን ግንባታ መመልከት ይቻላል። በዚህ ዝግጅት የተገነቡትን አንዳንድ የመንግሥት አዳራሾችን ፎቶ ስትመለከት እንዲህ ዓይነቱ ግንባታ በይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ላይ ያመጣውን ውጤት አስብ! ይህንን ውጤት በተለይ በሦስት ዘርፎች መመልከት ይቻላል። የዓለም አቀፋዊው የወንድማማች ማኅበር አንድነት እንዲጠናከር፣ የአካባቢው ኅብረተሰብ አመለካከቱ እንዲለወጥና በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የሚገኙ የተሰብሳቢዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል። ይህ አባሪ በአፍሪካ ስለተገነቡ የመንግሥት አዳራሾች ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ሲሆን በሌሎች አኅጉራት እየተካሄደ ስላለው የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ደግሞ ወደፊት በመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ላይ ይወጣል።
[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ
ቢምቦ፣ ባንጊ
ቤጎዋ፣ ባንጊ
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ኡኮንጋ፣ ታንዛኒያ
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አክራ፣ ጋና
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሳላላ፣ ላይቤርያ
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ካሮኢ፣ ዚምባብዌ
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አላዳ፣ ቤኒን—የቀድሞው የመንግሥት አዳራሽ
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አላዳ፣ ቤኒን—አዲስ የመንግሥት አዳራሽ
[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ፔሜ፣ ቶጎ
[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሶኮዴ፣ ቶጎ
[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ፌጅሮስ፣ ቤኒን
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሊንጋ፣ ዛምቢያ—የቀድሞው የመንግሥት አዳራሽ
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሊንጋ፣ ዛምቢያ—አዲስ የመንግሥት አዳራሽ
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ኪንሻሳ፣ ኮንጎ
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ሙሳምቢራ፣ ሩዋንዳ