የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/03 ገጽ 1
  • የይሖዋን ጥሩነት ኮርጁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋን ጥሩነት ኮርጁ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ጥሩነቱ ምንኛ ታላቅ ነው!”
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • ጥሩነት—እንዴት ልታዳብረው ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • የይሖዋ ጥሩነት ብዛት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይሖዋ—ከሁሉ የላቀው የጥሩነት ምሳሌ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 8/03 ገጽ 1

የይሖዋን ጥሩነት ኮርጁ

1 ጀምበር ስትጠልቅ በአድማሱ ላይ የሚፈጠረውን ውብ ትዕይንት ስንመለከት ወይም እጅ የሚያስቆረጥም ምግብ ስንመገብ የመልካም ነገሮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ለማመስገን አንገፋፋም? የይሖዋ ጥሩነት እርሱን እንድንኮርጅ ይገፋፋናል። (መዝ. 119:66, 68፤ ኤፌ. 5:1) ጥሩነትን ማንጸባረቅ የምንችለው እንዴት ነው?

2 አማኝ ላልሆኑ ሰዎች:- የይሖዋን ጥሩነት መኮረጅ የምንችልበት አንደኛው መንገድ አማኝ ላልሆኑ ሰዎች ልባዊ አሳቢነት በማሳየት ነው። (ገላ. 6:10) ጥሩነትን በተግባር ማሳየታችን ሰዎች በአጠቃላይ ስለ ይሖዋ ምሥክሮችና ስለምንሰብከው መልእክት ባላቸው አመለካከት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

3 ለምሳሌ ያህል አንድ ወጣት አቅኚ ወንድም በክሊኒክ ውስጥ ወረፋ በሚጠብቅበት ወቅት ከእርሱ ቀጥሎ የተቀመጡት አረጋዊት ሴት በዚያ ከነበሩት ከሁሉም ይልቅ በጣም እንደታመሙ አስተዋለ። ተራው ሲደርስ ሴትየዋ ቀድመው እንዲገቡ ፈቀደላቸው። በሌላ ጊዜ በገበያ ቦታ ሲገናኙ ሴትየዋ በጣም ደስ አላቸው። ከዚያ ቀደም ምሥራቹን ለመስማት ፈቃደኛ ያልነበሩ ቢሆንም አሁን ግን የይሖዋ ምሥክሮች ለሰዎች ፍቅር እንዳላቸው እንደተገነዘቡ ተናግረዋል። ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመሩ።

4 ለወንድሞቻችን:- የእምነት አጋሮቻችንን ለመርዳት ራሳችንን በፈቃደኝነት ስናቀርብም የይሖዋን ጥሩነት እንኮርጃለን። አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ከማንም በፊት ለወንድሞቻችን የምንደርሰው እኛ ነን። ወደ ስብሰባዎች ለመሄድ መጓጓዣ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት፣ በዕድሜ የገፉትንም ሆነ የጤና ችግር ያለባቸውን ለመጠየቅ እንዲሁም በጉባኤ ውስጥ በደንብ የማናውቃቸውን ይበልጥ ለመቅረብ ጥረት ለማድረግ ግንባር ቀደም መሆን ይኖርብናል።​—⁠2 ቆ⁠ሮ. 6:11-13፤ ዕብ. 13:16

5 ይሖዋ ጥሩነቱን ያሳየበት ሌላው መንገድ “ይቅር ባይ” መሆኑ ነው። (መዝ. 86:5) እኛም ሌሎችን ይቅር በማለት ጥሩነትን እንደምንወድ ማሳየት እንችላለን። (ኤፌ. 4:32) ይህም ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ያለን ግንኙነት ‘መልካምና ያማረ’ እንዲሆን ይረዳናል።​—⁠መዝ. 133:1-3

6 የይሖዋ ጥሩነት በአድናቆትና በደስታ እንድንሞላ የሚያደርገን እንዲሁም በሁሉም ነገሮች ጥሩነቱን እንድንኮርጅ የሚገፋፋን እንዲሆን ምኞታችን ነው።​—⁠መዝ. 145:7፤ ኤር. 31:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ