የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/03 ገጽ 8
  • አቅኚነት የሚያስገኛቸው በረከቶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አቅኚነት የሚያስገኛቸው በረከቶች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኛቸው በረከቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • አቅኚዎች በረከትን ይሰጣሉ፤ መልሰውም በረከት ያገኛሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • አቅኚነት ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና ያጠናክርልናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • አቅኚነት—ጊዜያችንን በጥበብ የምንጠቀምበት መንገድ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 8/03 ገጽ 8

አቅኚነት የሚያስገኛቸው በረከቶች

1, 2. አቅኚነት ምን በረከቶችን ያስገኛል? ለምንስ?

1 አንድ አቅኚ “እውነትን ለሌሎች በማካፈል ያገኘሁትን ዓይነት እርካታ ሊሰጠኝ የሚችል ሌላ ሥራ እንደሌለ አውቃለሁ” በማለት ተናግሮ ነበር። አንዲት ሌላ አቅኚ ደግሞ “በእያንዳንዱ ዕለት ጣፋጭ እንቅልፍ እተኛለሁ፤ ልቤም በደስታ ይሞላል” ብላለች። አቅኚነት የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች የቀመሱ ወንድሞችና እህቶች ሁሉ ከላይ በተጠቀሱት ሐሳቦች እንደሚስማሙ ምንም ጥርጥር የለውም።​—⁠ምሳሌ 10:22

2 ሌሎች ሕይወት አድን የሆነውን የአምላክ ቃል እውቀት እንዲያገኙ መርዳት እውነተኛ እርካታ ያስገኛል። (ሥራ 20:35፤ 1 ተ⁠ሰ. 2:19, 20) ለረጅም ዓመታት በአቅኚነት ያገለገለ አንድ ወንድም እንዲህ ሲል ጽፏል:- “የአምላክ ቃል ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያደርጉ በማንቀሳቀስ ረገድ ምን ያህል ኃይል እንዳለው መመልከት የሚያስደስትና እምነትን የሚያጠነክር ነው።” አዎን፣ አቅኚዎች ሰዎችን ለመርዳትና መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት ራሳቸውን በፈቃደኝነት በማቅረብ እንዲህ ያሉ በረከቶችን ማግኘት ይችላሉ።

3, 4. አንድ ሰው አቅኚ መሆኑ በይሖዋ እንዲታመን የሚያደርገው እንዴት ነው? ይህስ በመንፈሳዊ እንዲያድግ የሚረዳው እንዴት ነው?

3 በይሖዋ መታመን:- አቅኚዎች አገልግሎታቸውን ሲያከናውኑ ምንጊዜም በይሖዋ መታመናቸው “የመንፈስ ፍሬ” እንዲያፈሩ የሚረዳቸው ከመሆኑም በላይ ጥበቃ ይሆንላቸዋል። (ገላ. 5:16, 22, 23) በተጨማሪም የአምላክን ቃል ዘወትር ስለሚጠቀሙ በቅዱሳን ጽሑፎች አማካኝነት ለእ​ውነት ጥብቅና በመቆምና ሌሎችን በማበረታታት ረገድ የተካኑ ናቸው። (2 ጢ⁠ሞ. 2:​15) ለብዙ አሥርተ ዓመታት በአቅኚነት ያገለገለ አንድ ወንድም እንዲህ ብሏል:- “አቅኚነት ጥልቀት ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እንዳገኝ አስችሎኛል፤ በዚህም እውቀት ብዙ ሰዎች ይሖዋንና ዓላማውን እንዲያውቁ መርዳት ችያለሁ።” በእርግጥም አቅኚነት በረከት ያስገኛል!

4 የዘወትር አቅኚዎች በሌሎች መንገዶችም በይሖዋ መታመን ይኖርባቸዋል። የሚያስፈልጋቸውን ቁሳዊ ነገሮች ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ይሖዋ እንደባረከላቸው ሲመለከቱ እምነታቸው ይጠናከራል። ለ55 ዓመታት በዘወትር አቅኚነት ያገለገሉ አንድ የ72 ዓመት አረጋዊ ወንድም “ይሖዋ ጥሎኝ አያውቅም” ብለዋል። ከዚህም በላይ አቅኚዎች አኗኗራቸውን ቀላል በማድረግ ከተለያዩ የኑሮ ጭንቀቶች መዳን ይችላሉ። ከኑሮ ጭንቀቶች እፎይ ማለት የሚያስደስት አይደለምን?​—⁠ማቴ. 6:22፤ ዕብ. 13:5, 6

5. አቅኚነት አንድን ሰው ወደ ይሖዋ እንዲቀርብ የሚረዳው እንዴት ነው?

5 ወደ አምላክ መቅረብ:- ከይሖዋ ጋር ከመሠረትነው ዝምድና የሚበልጥ ምንም ሃብት የለንም። (መዝ. 63:3) ለይሖዋ ባለን ፍቅር ተነሳስተን በአገልግሎት ሙሉ ተሳትፎ ስናደርግ ይህ ዝምድናችን ይበልጥ ይጠናከራል። (ያዕ. 4:8) ከ18 ዓመታት በላይ በአቅኚነት ያገለገለ አንድ ወንድም “የአቅኚነት አገልግሎት ከፈጣሪያችን ጋር የመሠረትነውን ዝምድና በየዕለቱ እያጠናከርን እንድንሄድ ስለሚያስችለን ‘ይሖዋ ጥሩ መሆኑን እንድንቀምስና እንድናይ’ አጋጣሚ ይሰጠናል” ብሏል።​—⁠መዝ. 34:8

6. አቅኚዎች ምን ሊኖራቸው ይገባል? ከአቅኚዎች ሌላ እነማን ይጠቀማሉ?

6 አቅኚዎች አቅኚ ለመሆን ሁኔታዎቻቸውን ከማመቻቸታቸው በተጨማሪ ጠንካራ እምነት፣ ለአምላክና ለሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንዲሁም መሥዋዕትነቶችን ለመክፈል የፈቃደኝነት መንፈስ ሊኖራቸው ይገባል። (ማቴ. 16:​24፤ 17:​20፤ 22:​37-​39) ይሁን እንጂ አቅኚነት የሚያስገኛቸው በረከቶች ከመሥዋዕትነቶቹ በእጅጉ እንደሚልቁ በአቅኚዎች ፊት ላይ የሚነበበው የደስተኝነት ስሜት ምሥክር ነው። (ሚል. 3:10) እነዚህን በረከቶች የሚያገኙት አቅኚዎቹ ብቻ አይደሉም፤ እነርሱ በሚያሳዩት መልካም መንፈስ ቤተሰቦቻቸውና ጉባኤውም በእጅጉ ይጠቀማሉ።​—⁠ፊልጵ. 4:23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ