የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/04 ገጽ 4
  • የኢየሱስን አስተሳሰብ ኮርጁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኢየሱስን አስተሳሰብ ኮርጁ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የክርስቶስን አስተሳሰብ አንጸባርቁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ሌሎችን በማገልገል የኢየሱስን ምሳሌ ተከተሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ልታወጣው የምትችለው ጠቃሚ ግብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • የክርስቶስ ፍቅር እኛም ለሌሎች ፍቅር እንዲኖረን ያነሳሳናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 4/04 ገጽ 4

የኢየሱስን አስተሳሰብ ኮርጁ

1. ኢየሱስ ምን ዓይነት አስተሳሰብ ነበረው?

1 የአምላክን ልጅ አይተነው የማናውቅ ቢሆንም እንኳ የኢየሱስን ሕይወትና አገልግሎት በሚመለከት በጽሑፍ በሰፈረው ዘገባ አማካኝነት እርሱን ከልብ ልንወደው እንችላለን። (1 ጴ⁠ጥ. 1:8) ኢየሱስ ለአባቱ ፈቃድ ታዛዥ በመሆን በሰማይ የነበረውን ክብር ትቶ ወደ ምድር መጥቷል። ሰው ሆኖ ባሳለፋቸው ዓመታት የራሱን ጥቅም በመሠዋት ሌሎችን ከማገልገሉም በላይ ለመላው የሰው ዘር ሕይወቱን አሳልፎ ሰጥቷል። (ማቴ. 20:28) የአምላክ ቃል “በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን” በማለት ያበረታታናል። ታዲያ እርሱ ያሳየውን የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?​—⁠ፊልጵ. 2:5-8

2. በርካታ ክርስቲያኖች ምን ፈታኝ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል? ችግሩን ለማሸነፍ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

2 በሚደክመን ጊዜ፦ ኢየሱስ ፍጹም ቢሆንም ይደክመው ነበር። በአንድ ወቅት “ከጉዞው የተነሣ ደክሞት” ሳለ ለአንዲት ሳምራዊት ሴት በሚገባ መስክሮላታል። (ዮሐ. 4:6) ዛሬም ብዙ ክርስቲያኖች ተመሳሳይ ችግር ያጋጥማቸዋል። በሳምንቱ ውስጥ አድካሚ ሥራ ስንሠራ ቆይተን በስብከቱ ሥራ ለመካፈል የሚያስችል ብርታት ማግኘት አስቸጋሪ ሊሆንብን ይችላል። ይሁን እንጂ በመስክ አገልግሎት አዘውትረን የምንካፈል ከሆነ ክርስቲያናዊ አገልግሎታችን መንፈስን የሚያድስ ይሆንልናል።​—⁠ዮሐ. 4:32-34

3. ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር የነበረውን የፈቃደኝነት ዝንባሌ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?

3 በአንድ ሌላ አጋጣሚ ደግሞ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ትንሽ አረፍ ለማለት ጭር ወዳለ አካባቢ ሄዱ። ይሁን እንጂ በርካታ ሰዎች ወዴት እንደሚሄዱ ገብቷቸው ቀድመው እቦታው ደረሱ። ኢየሱስ በሁኔታው ከመበሳጨት ይልቅ ‘አዘነላቸውና ብዙ ነገር ያስተምራቸው’ ጀመር። (ማር. 6:30-34) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማግኘትም ሆነ ማስጠናት ተመሳሳይ አስተሳሰብ ወይም ዝንባሌ ይጠይቃል። እንዲሁም ትጋት የታከለበት ጥረት ማድረግና ለሰዎች እውነተኛ ፍቅር ማዳበርም አስፈላጊ ነው። አንተም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከሌለህ ተስፋ ሳትቆርጥ መፈለግህን ቀጥል።

4. ረዳት አቅኚ መሆን የክርስቶስን አስተሳሰብ እንድንኮርጅ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?

4 ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ቅድሚያ ስጡ፦ ረዳት አቅኚ መሆን ይበልጥ በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ላይ እንድናተኩር ሊረዳን ይችላል። አንዲት ወጣት ክርስቲያን እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “የአንዲት ጓደኛዬ እናት ሁለታችንም እንደ እርሷ ለአንድ ወር ረዳት አቅኚ እንድንሆን አበረታታችን። ማበረታቻዋን በመቀበላችን በጣም ደስ ብሎኛል። ወንድሞችንና እህቶችን ይበልጥ ለማወቅ ያስቻለኝ ከመሆኑም በላይ ብዙም ሳይቆይ እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነናል። ከዚህም በላይ ለሌሎች ስለ ይሖዋ የመናገርና አስደሳች ስለሆኑት የመንግሥቱ እውነቶች የማስተማር ሰፊ አጋጣሚ ከፍቶልኛል። ይህ ሁሉ ወደ ይሖዋና ወደ ድርጅቱ ይበልጥ እንደቀረብኩ እንዲሰማኝ አድርጎኛል።”​—⁠መዝ. 34:8

5. የኢየሱስን አስተሳሰብ ለመኮረጅ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ የሚኖርብን ለምንድን ነው?

5 ሁላችንም ፍጹም ባልሆነው ሥጋችንና ይሖዋን ለማስደሰት ባለን ፍላጎት መካከል ውጊያ አለብን። (ሮሜ 7:21-23) የራሳችንን ጥቅም መሥዋዕት እንዳናደርግ የሚገፋፋንን የዓለምን መንፈስ መታገል ይኖርብናል። (ማቴ. 16:22, 23) በዚህ ረገድ እንዲሳካልን ይሖዋ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ሊረዳን ይችላል። (ገላ. 5:16, 17) ጽድቅ ወደሚሰፍንበት ወደ አምላክ አዲስ ዓለም ለመግባት በምንጠባበቅበት ጊዜ የመንግሥቱን ጉዳዮች እንዲሁም የሌሎችን ጥቅም ከራሳችን ፍላጎቶች በማስቀደም የኢየሱስን አስተሳሰብ የምንኮርጅ እንሁን።​—⁠ማቴ. 6:33፤ ሮሜ 15:1-3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ