የአውራጃ ስብሰባው ከአምላክ ጋር እንድንሄድ አበረታቶናል
“ከአምላክ ጋር መሄድ” የተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚለውን የይሖዋን ግልጽ መመሪያ እንድንከተል የሚያበረታታ ነበር። (ኢሳ. 30:21) በስብሰባው ላይ ያገኘነውን ትምህርት ተግባራዊ ማድረጋችን ‘በጥንቃቄ እንድንመላለስ’ ይረዳናል። (ኤፌ. 5:15 የ1954 ትርጉም) በተማርነው ነገር ላይ ማሰላሰላችን ‘በእውነት ለመመላለስ’ ያግዘናል።—3 ዮሐ. 3
ከዚህ ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎችና በስብሰባው ላይ በያዝከው ማስታወሻ በመጠቀም በዚህ ዓመት በተካሄደው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ተመሥርቶ ለሚደረገው ክለሳ መዘጋጀትና ተሳትፎ ማድረግ ትችላለህ።
1. ሄኖክ ሁከት በነገሠበት ዘመን ቢኖርም ከአምላክ ጋር መሄድ የቻለው ለምንድን ነው? (ዕብ. 11:1, 5, 6፤ ይሁዳ 14, 15፤ “ሁከት በነገሠበት በዚህ ዘመን ከአምላክ ጋር መሄድ”)
2. በሉቃስ 16:10 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት በየትኞቹ የሕይወታችን ዘርፎች ተግባራዊ ልናደርገው እንችላለን? (“‘በትንሽ ነገር ታማኝ’ ናችሁ?”)
3. (ሀ) በሆሴዕ ምዕራፍ 6 እስከ 9 ላይ የሚገኙ ከአምላክ ጋር ለመመላለስ የሚረዱን አራት ተግባራዊ ትምህርቶችን ጥቀስ። (ሆሴዕ 6:6, 7፤ 7:14፤ 8:7) (ለ) በሆሴዕ ምዕራፍ 10 እስከ 14 ላይ ከአምላክ ጋር ለመመላለስ የሚረዱን ምን ተጨማሪ ነጥቦች ተገልጸዋል? (“የሆሴዕ ትንቢት ከአምላክ ጋር እንድንሄድ ይረዳናል”—ተከታታይ ንግግር)
4. ክርስቲያን ባሎችና ሚስቶች ትዳራቸውን ለማጠናከር ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? (ምሳሌ 12:4፤ ኤፌ. 5:29፤ “‘እግዚአብሔር ያጣመረውን’ እናንተ አትለያዩት”)
5. ቅዱስ ለሆኑት ስብሰባዎቻችን አክብሮት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (መክ. 5:1፤ ኢሳ. 66:23፤ “ቅዱስ ለሆኑት ስብሰባዎቻችን አክብሮት ማሳየት”)
6. (ሀ) በአገልግሎታችን ጠቃሚ ድርሻ ማበርከት እንድንችል ልንመረምራቸው የሚገቡ ሦስት የስብከት ሥራችን ዋና ዋና ገጽታዎች የትኞቹ ናቸው? (ኢሳ. 52:7፤ ዘካ. 8:23፤ ማር. 6:34) (ለ) ለሰዎች ሁሉ የሚሆን ምሥራች ከተባለው ቡክሌት የተለያዩ ገጽታዎች መካከል በተለይ ጠቃሚ ሆኖ ያገኛችሁት የትኛውን ነው? (“ለሰዎች ሁሉ የሚሆን ምሥራች”፤ “ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን መርዳት”)
7. አዲሶች የመንግሥቱን መልእክት በልበ ሙሉነት እንዲሰብኩ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው? (መሳ. 7:17፤ “አዲሶች አብረውን እንዲያገለግሉ መርዳት”)
8. “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ” መሆኑን እንደምናምን እንዴት ማሳየት እንችላለን? (ሶፎ. 1:14፤ ‘በማየት ሳይሆን በእምነት መመላለስ’)
9. (ሀ) ሌሎችን ማሰናከልም ሆነ በሌሎች መሰናከል ምን ያህል አሳሳቢ ነው? (ማር. 9:42-48) (ለ) በሌሎች ከመሰናከል መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? (መዝ. 119:165) (ሐ) ሌሎችን ከማሰናከል መራቅ የምንችለው እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 10:24፤ “‘ዕንቅፋት’ የሚሆኑ ነገሮችን አስወግዱ”)
10. የትዳር ጓደኛ ለማግኘት በምናደርገው ጥረት፣ ለጤንነታችን በምንሰጠው ትኩረትና የንግድ ሥራዎችን በመሳሰሉ ጉዳዮች ረገድ ሚዛናዊ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (መዝ. 26:4፤ ማቴ. 6:25፤ 1 ጢሞ. 6:9፤ “የማስተዋል ስሜታችሁን ጠብቁ”)
11. (ሀ) ኢየሱስ ሰዎች ቤት በተጋበዘባቸው ጊዜያት ምን አድርጓል? (ሉቃስ 10:42፤ 24:32) (ለ) ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች መንፈስን የሚያድስ መዝናኛ ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 10:31-33፤ “መንፈስ የሚያድሱ ጤናማ መዝናኛዎች”)
12. በ23ተኛው መዝሙር መሠረት የይሖዋ በጎች በመሆናችን ምን በረከቶች እናገኛለን? ምን ኃላፊነቶችስ አሉብን? (1 ቆሮ. 10:21፤ “ይሖዋ እረኛችን ነው”)
13. ክርስቲያኖች “ዘመኑን በሚገባ ዋጁ” የሚለውን መለኮታዊ ምክር ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? (ኤፌ. 5:16፤ “ዘመኑን በሚገባ ዋጁ”)
14. (ሀ) በራእይ 14:7 ላይ የተጠቀሰው ‘የፍርድ ሰዓት’ የትኛውን ጊዜ ያጠቃልላል? (ለ) ከታላቂቱ ባቢሎን ሙሉ በሙሉ መውጣታችንን የምናሳየው እንዴት ነው? (“የፍርዱ ሰዓት ደርሷልና—‘ነቅታችሁ ጠብቁ’”) (ሐ) በአዲሱ ብሮሹር ላይ ካሉት ነጥቦች የማረኩህ የትኞቹ ናቸው?
15. ‘ቀናውን መንገድ ትተን’ እንዳንወጣ የሚጠብቁንን ሦስት ባሕርያት ጥቀስ። (2 ጴጥ. 2:15፤ “‘ቀናውን መንገድ ትታችሁ’ እንዳትወጡ ተጠንቀቁ”)
16. ወጣቶች ‘ከክፉዎች መንገድ’ መራቅ የሚችሉት እንዴት ነው? (ምሳሌ 4:14፤ “ወጣቶች—በጽድቅ ጎዳና ተመላለሱ”)
17. (ሀ) ጳውሎስ በጽናት ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆነው በየትኞቹ መንገዶች ነው? (ሥራ 14:19, 20፤ 16:25-33) (ለ) የእውነተኛውን አምልኮ ተቃዋሚዎች ልንፈራ የማይገባው ለምንድን ነው? (ድራማውና “ተቃውሞ ቢኖርም ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ ስበኩ” የሚለው ንግግር)
18. አካሄዳቸውን ከአምላክ ጋር የሚያደርጉ ምን በረከቶች ያገኛሉ? (“አካሄድን ከአምላክ ጋር ማድረግ አሁንም ሆነ ለዘላለም በረከት ያስገኛል”)
‘ከኋላችን ያለውን ድምፅ’ በመስማት በሰማይ ከሚኖረው አባታችን ጋር ለዘላለም ለመጓዝ ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ።—ኢሳ. 30:21፤ ዮሐ. 3:36