መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“የሰው ልጅ እርስ በርስ በተከፋፈለበት በዚህ ዘመን ብዙዎች ለዓለም ሰላም ማምጣት የሚቻለው አንድ ዓለም አቀፋዊ መንግሥት በማቋቋም ብቻ ነው ብለው ያስባሉ። ይህ የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ዳንኤል 2:44ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክ መንግሥት በአሁኑ ወቅት ምን እያከናወነ እንዳለና በቅርቡ ዓለም አቀፋዊ ሰላም የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ ይናገራል።”
ንቁ! ነሐሴ 2004
“ለብዙዎች የአፍላነት ዕድሜያቸው አስደሳች ገጠመኞችንም ሆነ የተለያዩ ችግሮችን የሚመለከቱበት ወቅት ነው ቢባል አይስማሙም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ስለሚያጋጥሟቸው ለውጦች ይናገራል። ከዚህም በላይ ይህን የአፍላነት ዕድሜያቸውን በተሻለ መንገድ እንዲጠቀሙበት የሚረዷቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች ይሰጣል።” መክብብ 12:1ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 15
“በዛሬው ጊዜ ሰዎች ትዳርንና የልጆች አስተዳደግን በሚመለከት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ምክር ይፈልጋሉ። ከሁሉ የተሻለውን ምክር ማግኘት የሚቻለው ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም የሰው ልጅ ፈጣሪ የቤተሰብ ሕይወትን በሚመለከት ከሰጣቸው ጠቃሚ ምክሮች ውስጥ አንዳንዶቹን ያብራራል።” መዝሙር 32:8ን አንብብ።