የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/05 ገጽ 8
  • አገልግሎታችን ምን ውጤት ያስገኛል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አገልግሎታችን ምን ውጤት ያስገኛል?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ምሥራቹን በጉጉት አውጁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በአገልግሎት መጽናት የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የጥድፊያ ስሜታችሁን አታጥፉ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
km 11/05 ገጽ 8

አገልግሎታችን ምን ውጤት ያስገኛል?

1. ይሖዋ አገልግሎታችንን የሚመለከተው እንዴት ነው? የምንሰብክላቸው ሰዎችስ ምን ዓይነት ምላሽ ይሰጣሉ?

1 የአምላክ ቃል ክርስቲያኖችን በይሖዋ አገልግሎት ድል እያደረገ እንደሚገሰግስ ሠራዊት አድርጎ ይገልጻቸዋል። (2 ቆሮ. 2:14-16) የአምላክን እውቀት ለሌሎች በመናገር የምናቀርበው አገልግሎት ለይሖዋ ደስ የሚል ሽታ እንዳለው ዕጣን ነው። አንዳንዶች ለምሥራቹ ጥሩ ምላሽ ሲሰጡ ሌሎቹ ግን ሳይቀበሉት ይቀራሉ። ሆኖም ብዙ ሰዎች መጥፎ ምላሽ ስለሚሰጡን ሥራችን ውጤታማ አይደለም ብለን መደምደም የለብንም። አገልግሎታችን የሚያከናውናቸውን ነገሮች እንመልከት።

2. አገልግሎታችን ምን ለመግለጽ ያስችለናል?

2 ይሖዋን ከፍ ከፍ ያደርጋል:- ሰይጣን የሰው ልጆች ይሖዋን የሚያገለግሉት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ነው የሚል ክስ አንስቷል። (ኢዮብ 1:9-11) ክርስቲያናዊ አገልግሎታችን ለአምላክ ያለን ፍቅር ከልብ የመነጨ እንደሆነ ለማሳየት ግሩም አጋጣሚ ይሰጠናል። በርካታ አስፋፊዎች በግላቸው የሚያጋጥሟቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎችም ሆኑ የሰዎች ግድ የለሽነት ሳይበግሯቸው በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ታዛዥ ሆነው ይቀጥላሉ። በዚህ መንገድ በታማኝነት መጽናታችን የይሖዋን ልብ ደስ ያሰኛል!—ምሳሌ 27:11

3. የአምላክን ስምና ዓላማ በማሳወቁ ሥራ መቀጠላችን ይህን ያህል አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

3 ከዚህም በተጨማሪ አገልግሎታችን የአምላክ ዓላማ ፍጻሜውን እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ይሖዋ ከመጪው የሰይጣን ዓለም ጥፋት ጋር በተያያዘ “አሕዛብም እኔ እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] . . . እንደ ሆንሁ ያውቃሉ” ብሏል። (ሕዝ. 39:7) አሕዛብ ይህን እንዲያውቁ፣ የአምላክ አገልጋዮች “ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋና ለወገን ሁሉ” ስሙንና ዓላማውን ማወጃቸውን መቀጠላቸው እጅግ አስፈላጊ ነው።—ራእይ 14:6, 7

4. የስብከቱ ሥራ ፍርድ ለመስጠት መሠረት ሆኖ የሚያገለግለው እንዴት ነው?

4 ፍርድ ለመስጠት መሠረት ይሆናል:- ምሥራቹ መሰበኩ ፍርድ ለመስጠትም መሠረት ሆኖ ያገለግላል። ኢየሱስ ክርስቶስ “እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችንም ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል” በማለት ሐዋርያው ጳውሎስ ተናግሯል። (2 ተሰ. 1:8, 9) ሰዎች ለምሥራቹ በሚሰጡት ምላሽ መሠረት ይፈረድባቸዋል። ይህ ደግሞ የአምላክ አገልጋዮች ከባድ ኃላፊነት እንደተጣለባቸው ያሳያል! የደም ዕዳ እንዳይኖርብን ሕይወት አድን የሆነውን የመንግሥቱን መልእክት ከማሳወቅ ወደኋላ ማለት የለብንም።—ሥራ 20:26, 27

5. የአምላክ ምሕረት በአገልግሎታችን ላይ የሚንጸባረቀው እንዴት ነው?

5 ሰዎች የአምላክን ሞገስ እንዲያገኙ የምናደርገው ቀጣይነት ያለው ጥረት የይሖዋ ምሕረት መገለጫ ነው። (1 ጢሞ. 2:3, 4) የሰዎች ሕይወት ከዕለት ወደ ዕለት የሚለዋወጥ በመሆኑ ጊዜው ሳያልፍ ይሖዋን እንዲፈልጉ ደግመን ደጋግመን እናሳስባቸዋለን። እንዲህ በማድረግ ‘ማንም እንዳይጠፋና ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ’ የሚፈልገውን ‘የአምላካችንን በጎ ምሕረት’ ለማንጸባረቅ እንችላለን።—ሉቃስ 1:78፤ 2 ጴጥ. 3:9

6. በይሖዋ አገልግሎት ራሳችንን ማስጠመዳችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?

6 ራሳችንን እንጠቅማለን:- በይሖዋ አገልግሎት ራሳችንን ማስጠመዳችን ለእኛው ጥበቃ ነው። ‘የእግዚአብሔርን ቀን እየተጠባበቅን መምጫውን እንድናፋጥን’ ይረዳናል፤ በዚህ ክፉ ሥርዓት እንዳንቆሽሽም ይጠብቀናል። (2 ጴጥ. 3:11-14፤ ቲቶ 2:11, 12) እንግዲያው በክርስቲያናዊ አገልግሎታችን የምናደርገው ጥረት ከንቱ አለመሆኑን በማወቅ፣ ‘ጸንተን በመቆምና በምንም ነገር ባለመናወጥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምንተጋ እንሁን።’—1 ቆሮ. 15:58

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ