ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! በተባለው መጽሐፍ ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች
ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! በተባለው በ1988 በተዘጋጀው መጽሐፍ ላይ የተደረጉት ዋና ዋና ማስተካከያዎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል። በቅርቡ በወጣው የዓመት መጽሐፍ ወይም በሌሎች ጽሑፎች ላይ ሊገኙ የሚችሉ አንዳንድ አኃዛዊ ማስተካከያዎች በዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።
ምዕራፍ 4
ገጽ 19 አን. 4፣ የመጨረሻው ጥቅስ ይሰረዝ፦ ማቴዎስ 25:31-33
ምዕራፍ 5
ገጽ 24 አን. 3፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦
* ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 88-92, 215-218 ተመልከት።
ምዕራፍ 6
ገጽ 30 አን. 12፣ ስድስተኛውና ሰባተኛው ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ በመጨረሻም ቆስጠንጢኖስ የተባለው የሮም ንጉሠ ነገሥት “የክርስትና” ሃይማኖት በመንግሥት ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ አደረገ። ይህም ድርጊት ለሕዝበ ክርስትና መስፋፋት ምክንያት ከመሆኑም ሌላ ቤተ ክህነትና መንግሥት ሰዎችን ለሺህ ዓመት ለመግዛት ኃይላቸውን አጣመሩ።
ገጽ 32 ሣጥኑ፣ የመጀመሪያው አንቀጽ በዚህ ይተካ፦ ኢየሱስ እጩ ንጉሥ ሆኖ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀውና የተቀባው በ29 እዘአ በጥቅምት ወር አካባቢ ነበር። ይህ ከሆነ ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ በ33 እዘአ በኢየሩሳሌም ወደነበረው ቤተ መቅደስ መጥቶ ቤተ መቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ ያደረጉትን ሰዎች አባረረ። ኢየሱስ ጥቅምት 1914 በሰማይ ከነገሠ በኋላ፣ ፍርድ ከአምላክ ቤት ስለሚጀምር ክርስቲያን ነን ይሉ የነበሩትን ሁሉ ለመመርመር እስኪመጣ ድረስ ሶስት ዓመት ተኩል ማለፉ ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል። (ማቴዎስ 21:12, 13፤ 1 ጴጥሮስ 4:17) የይሖዋ ሕዝቦች ያካሂዱት የነበረው የመንግሥት የሥራ እንቅስቃሴ በ1918 መጀመሪያ ላይ ትልቅ ተቃውሞ ደርሶበት ነበር። በምድር በሙሉ የፈተና ጊዜ ሆኖ ነበር። ፍርሐት የነበራቸው ሁሉ በዚህ ጊዜ ተበጥረዋል። በግንቦት ወር 1918 የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት የመጠበቂያ ግንብ ማህበርን ባለ ሥልጣኖች አሳስረው ነበር። ከዘጠኝ ወር በኋላ ግን ከእሥራት ተፈቱ። በኋላም የቀረቡባቸው የሐሰት ክሶች ሁሉ ተነሱላቸው። ከ1919 ጀምሮ የአምላክ ሕዝቦች ድርጅት ከተፈተነና ከተጣራ በኋላ የሰው ልጆች ብቸኛ ተስፋ በክርስቶስ ኢየሱስ መሪነት የሚገዛው የአምላክ መንግሥት መሆኑን ለማወጅ በቅንዓት ወደፊት መገስገስ ጀመረ።—ሚልክያስ 3:1-3
ምዕራፍ 8
ገጽ 40 አን. 8፣ ስድስተኛው መሥመር ላይ “125 ስህተቶች” የሚለው በዚህ ይተካ፦ 130 ስህተቶች
ገጽ 40 አን. 10፣ የመጨረሻው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ በዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብቻ የይሖዋ ምሥክሮች 50 ክሶችን ረትተዋል።
ምዕራፍ 10
ገጽ 50 አን. 11፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦
* ለምሳሌ ያህል፣ በኅዳር 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ እትም ላይ የወጣውን “ታማኝ ክርስቲያን ሴቶች—በአምላክ ፊት ውድ ናቸው” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
ምዕራፍ 11
ገጽ 56 አን. 9፣ ከሰባተኛው መሥመር በኋላ ያለው ሐሳብ በዚህ ይተካ፦ በዚህም ረገድ መጠበቂያ ግንብ “ራሳችሁን ፈትኑ” እና “ከእንግዲህ ለራሳችን አንኖርም” እንደሚሉት ያሉትን ትምህርቶች በማውጣት ማበረታቻ ሰጥቶአል።* እንደነዚህ ባሉት ቅዱስ ጽሑፋዊ እርዳታዎች በመጠቀም በይሖዋ ፊት ፍጹም አቋማችንን ጠብቀን በትህትናና በጸሎተኝነት መንፈስ ለመመላለስ በምንጥርበት ጊዜ ውስጣዊ ልቦናችንን ዘወትር እንመርምር።—መዝሙር 26:1-3፤ 139:23, 24
ገጽ 56 አን. 9፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦ * የሐምሌ 15, 2005 እና የመጋቢት 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ እትሞችን ተመልከት።
ምዕራፍ 12
ገጽ 61 አን. 14፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦
# በዮሐንስ ክፍል የሚታተመው መጠበቂያ ግንብ መጽሔት በዚህ አጋጣሚ መጠቀምና በተቻለ መጠን በስብከቱ ሥራ መካፈል በጣም አጣዳፊ መሆኑን ሲያስገነዝብ ቆይቶአል። ለምሳሌ ያህል፣ በጥር 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ላይ “ሰው ሁሉ የይሖዋን ክብር ያውጅ” እና “ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ወጣ” በሚሉ ርዕሶች የቀረቡትን ትምህርቶች ተመልከት። በሰኔ 1, 2004 እትም ላይ “ለአምላክ ክብር የሚሰጡ የተባረኩ ናቸው” በሚል ርዕስ በቀረበው ትምህርት ላይ ‘በተከፈተው በር’ ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት መግባት በጣም አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል። በ2005 በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 1,093,552 የደረሰ ከፍተኛ የአቅኚዎች ቁጥር ሪፖርት ተደርጓል።
ምዕራፍ 13
ገጽ 69 አን. 11፣ የመጨረሻው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት መሠረት የአሕዛብ ዘመን የሚፈጸመው በ1914 እንደሆነና በዚህም ዓመት በምድር ላይ አስደንጋጭ ሁኔታዎች እንደሚከሰቱ 40 ዓመት ያህል ቀደም ብለው አስታውቀው ነበር።—ራእይ 1:10
ገጽ 71 አን. 14፣ ዘጠነኛውና አሥረኛው መሥመር ላይ “በ1990 በጋራ ከ27 ሚልዮን በላይ” የሚለው ሐረግ በዚህ ይተካ፦ በ2006 በጋራ ከ59 ሚሊዮን በላይ
ገጽ 73 አን. 23፣ አሥራ አንደኛው መሥመር ላይ ያለው ጥቅስ ይውጣ፦ ማቴዎስ 25:31
ምዕራፍ 16
ገጽ 90 አን. 4፣ ሁለተኛው የግርጌ ማስታወሻ በዚህ ይተካ፦ * ኢየሱስ በ1914 ወደ መንግሥቱ እንደመጣ ተጨማሪ ማስረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 215-218 ተመልከት።
ገጽ 90 አን. 6 በዚህ ይተካ፦ ይሁን እንጂ አዲሱ ንጉሥ ወደ ጦርነት ለመውጣት የተገደደው ለምንድን ነው? ንግሥናው የተቋቋመው የእርሱን ንግሥና አምርሮ የሚቃወመው የይሖዋ ቀንደኛ ጠላት ሰይጣን ዲያብሎስና አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ሰይጣንን የሚያገለግሉ የምድር ሰዎች ባሉበት ጊዜ ላይ በመሆኑ ነው። የመንግሥቱ መወለድ ራሱ በሰማይ ላይ ታላቅ ጦርነት እንዲደረግ የሚያስገድድ ሁኔታ ፈጥሮአል። ኢየሱስ ሚካኤል (“እንደ አምላክ ያለ ማን ነው?” ማለት ነው) በተባለው ስሙ ተዋግቶ ሰይጣንንና አጋንንቱን ድል በማድረግ ወደ ምድር ወርውሮአቸዋል። (ራእይ 12:7-12) የኢየሱስ የድል አድራጊነት ግልቢያ በግ መሰል ሰዎች እየተሰበሰቡ ባሉበት በጌታ ቀን የመክፈቻ አሥርተ ዓመታት ቀጥሎአል። አሁንም መላው ዓለም ገና “በክፉው እንደ ተያዘ” ቢሆንም ኢየሱስ ግን ቅቡዓን ወንድሞቹንና ባልንጀሮቻቸውን የእምነትን ድል እንዲያገኙ በመርዳት በእረኝነት በፍቅር መጠበቁን ቀጥሎአል።—1 ዮሐንስ 5:19
ገጽ 92 አን. 9፣ የመጨረሻዎቹ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ በጣም ከፍተኛ የሆነ እድገት የተገኘው በካቶሊክ አገሮችና እንደ ጀርመን፣ ኢጣልያና ጃፓን በመሰሉት ከባድ ስደት በነበረባቸው አገሮች ነው። በአሁኑ ጊዜ በእነዚህ አገሮች በአጠቃላይ ከ600,000 የሚበልጡ የመስክ አገልጋዮች አሉ።—ኢሳይያስ 54:17፤ ኤርምያስ 1:17-19
ገጽ 94 አን. 18 በዚህ ይተካ፦ ታዲያ ይህን ሁሉ እልቂት የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ድል አድራጊነት ነው ልንል እንችላለንን? ከዚህ ይልቅ ምህረት የማያውቀው የቀይ ፈረስ ጋላቢ በከፍተኛ ፍጥነት በመጋለብ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው። ታዲያ ይህ ግልቢያ የሚያቆመው የት ነው? አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ታስቦበትና ሆን ተብሎ የሚደረገው የኑክሌር ጦርነት ግምት ውስጥ ሳይገባ፣ ሳይታሰብ በድንገት የኑክሌር ጦርነት ሊፈነዳ እንደሚችል ይናገራሉ። ይሁን እንጂ የነጩ ፈረስ ጋላቢ ስለዚህ ጉዳይ ያሰበው ሌላ ነገር መኖሩ ያስደስተናል።
ገጽ 97 አን. 28 በዚህ ይተካ፦ አሁን ይበልጥ ትኩረታችንን የሚስበው ‘ገዳይ የሆነው ቸነፈር’ ነው። ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እልቂት በኋላ ከ1918 እስከ 1919 በነበሩት ጥቂት ወራት ብቻ ስፓኒሽ ፍሉ ወይም የህዳር በሽታ የተባለው ቸነፈር ከ20 ሚልዮን በላይ ሰዎችን አጭዶአል። በምድር ገጽ ላይ ከዚህ ቸነፈር ያመለጠችው ሴይንት ሔሌና የተባለች አነስተኛ ደሴት ብቻ ነበረች። ብዙ ሰዎች በሞቱባቸው አካባቢዎች የሞቱትን ሰዎች አስከሬን መቅበር ስላልተቻለ አንድ ላይ ከምሮ ማቃጠል ግድ ሆኖአል። ዛሬም ቢሆን በአብዛኛው በትንባሆ ጭስ ምክንያት የሚመጣው የልብ በሽታና ካንሰር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተባዛ ሄዶአል። “አስቀያሚ አሥርተ ዓመት” ተብለው በተገለጹት የ1980ዎቹ ዓመታት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሕግጋት አንፃር ሲታይ ሕገወጥ በሆነው አኗኗር ምክንያት የኤድስ ‘ገዳይ ቸነፈር’ ወይም መቅሠፍት ተጨማሪ እልቂት የሚያስከትል ቸነፈር ሆኖአል። የዩናይትድ ስቴትስ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ከፍተኛ ባለ ሥልጣን በ2000 ስለ ኤድስ ሲናገሩ “በዓለም ላይ እስከ ዛሬ ከተከሰቱት ወረርሽኞች ሁሉ የከፋ ሳይሆን አይቀርም” ብለው እንደገለጹት ሪፖርት ተደርጓል። እኚህ ሰው በዓለም ዙሪያ 52 ሚልዮን ሰዎች በኤች አይ ቪ/ኤድስ እንደተያዙና ከእነዚህም ውስጥ 20 ሚልዮን የሚሆኑት እንደሞቱ ተናግረዋል። የይሖዋ ሕዝቦች ከቃሉ በሚያገኙት የጥበብ ምክር ምክንያት በዛሬው ጊዜ የብዙ በሽታዎች መተላለፊያ ምክንያት ከሆኑት ከምንዝርና ደም ከመውሰድ ስለሚጠበቁ ምን ያህል አመስጋኞች ናቸው!—ሥራ 15:28, 29፤ ከ1 ቆሮንቶስ 6:9-11 ጋር አወዳድር።
ምዕራፍ 17
ገጽ 100 አን. 2፣ አሥረኛው መሥመር “መቅረዞቹና” የሚለው በዚህ ይተካ፦ መብራቶቹና
ምዕራፍ 18
ገጽ 106 አን. 7 በዚህ ይተካ፦ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ደግሞ ሌላ የነውጥ ማዕበል አምጥቷል። አነስተኛ ጦርነቶችና ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ምድርን ማናወጣቸውን ቀጥለዋል። አሸባሪዎች ጥቃት ይሰነዝሩ ይሆናል ወይም መንግሥታት ጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ የሚለው ሥጋት ብዙ ሰዎችን ያሳስባቸዋል። ደስ የሚያሰኘው ነገር ግን የዚህ ጥያቄ መልስ በሰው ልጆች ላይ ሳይሆን በአምላክ ላይ የተመካ መሆኑ ነው።—ኤርምያስ 17:5
ገጽ 106፣ ጥያቄ ቁጥር 7-9 (ለ) በዚህ ይተካ፦ ከኢየሱስ መገኘት ጋር በተያያዘ ሰብዓዊውን ኅብረተሰብ ያናወጡት ነገሮች የትኞቹን ሁኔታዎች ይጨምራሉ?
ገጽ 107 አን. 9፣ አራተኛውና አምስተኛው ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ከዚያ በኋላ የተከሰቱት የጨለማ ጊዜያት ኢየሱስ መገኘቱን አስመልክቶ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜ ክፍል መሆናቸው ግልጽ ነበር። ከእነዚህም መካከል “አሕዛብ . . . እያመነቱ ይጨነቃሉ፣ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሳ ይደክማሉ” የሚለው ይገኝበታል። (ሉቃስ 21:7-9, 25-31)*
ገጽ 107 አን. 11፣ አራተኛው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ በዚህ ምድር አቀፍ የማስጠንቀቅ ዘመቻ አማካኝነት የሰይጣን ዓለማዊ ሥርዓት ስለ ፍርዱ እንዲያውቅ ተደርጓል።*
ገጽ 109 አን. 17፣ መሥመር 8-10 ላይ የሚገኘው የሚከተለው ዓረፍተ ነገር ይውጣ፦ ኢየሱስ ቀደም ሲል በማቴዎስ 24:29 ላይ ተንብዮት የነበረውን መዓት የሚቋጭ ሁኔታ ነው።
ምዕራፍ 20
ገጽ 123 አን. 11፣ አራተኛውና አምስተኛው ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ይህ መጽሐፍ እስከ ታተመበት ጊዜ ድረስ በምድር ዙሪያ በሚገኙ ከ125 በሚበልጡ ቦታዎች የተለያዩ ዓይነት የሜፕስ ፕሮግራሞች በሥራ ላይ ውለዋል። ይህም መጠበቂያ ግንብ የተባለው በየሁለት ሣምንት የሚወጣ መጽሔት በአንድ ጊዜ ከ130 በሚበልጡ ቋንቋዎች ታትሞ እንዲወጣ አስችሏል።
ገጽ 128 አን. 30፣ የመጨረሻው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ ‘የሚቆሙት’ ወይም ከጥፋቱ የሚተርፉት ጥቂት የሰው ልጆች ብቻ ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል በወቅቱ በምድር ላይ የሚገኙ የ144,000 አባሎች ካሉ እነርሱና የሌሎች በጎች ክፍል የሆኑት እጅግ ብዙ ሰዎች ይገኙበታል።—ኤርምያስ 35:19፤ 1 ቆሮንቶስ 16:13
ምዕራፍ 22
ገጽ 143፣ ንዑስ ርዕሱ በዚህ ይተካ፦ በዛሬው ጊዜ ያለው የአንበጣ መቅሰፍት
ገጽ 146 አን. 16፣ ከራእይ 9:10 በኋላ ያሉት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ታዲያ ይህ ነገር ምን ትርጉም ይኖረዋል? የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት ሥራቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በቃላቸውና በጽሑፎች አማካኝነት በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረቱ ኃይለኛ መግለጫዎችን ያስተላልፋሉ። ስለ መጪው የይሖዋ የበቀል ቀን ማስጠንቀቂያ ስለሚሰጡ መልእክታቸው እንደ ጊንጥ ይናደፋል። (ኢሳይያስ 61:2) የዚህ ትውልድ መንፈሳዊ አንበጦች የሕይወት ዘመናቸውን ከመፈጸማቸው በፊት የተሰጣቸውን የይሖዋን ፍርድ የማሰማትና አንገተ ደንዳና ተሳዳቢዎችን የመጉዳት መለኮታዊ ሥራ ይፈጽማሉ።
ገጽ 146 አን. 17፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦
* ይህ መጽሔት በ1937 ኮንሶሌሽን በ1946 ደግሞ ንቁ! የሚል ስም ተሰጥቶታል።
ገጽ 147 አን. 19፣ ጥቅሱ በዚህ ይተካ፦ (ማቴዎስ 24:3-14፤ ራእይ 12:1-10)
ምዕራፍ 24
ገጽ 160 አን. 21 ስምንተኛው መሥመር፣ “ለፍየል መሰል ሰዎች” የሚለው በዚህ ይተካ፦ ለተቃዋሚዎች
ገጽ 160 አን. 21 አሥራ ሦስተኛው መሥመር፣ “ማቴዎስ 25:31-34, 41, 46” በዚህ ይተካ፦ ፊልጵስዩስ 1:27, 28
ገጽ 160፣ ጥያቄ ቁጥር 21 (ለ) በዚህ ይተካ፦ ምሥራቹ ለተቃዋሚዎች አሳዛኝ ዜና የሆነባቸው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 25
ገጽ 162 አን. 4፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦ * ስለዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ሙሉ ማብራሪያ ለማግኘት በሐምሌ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “ታላቁ የይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ” የሚለውን ርዕስ እንዲሁም በታኅሣሥ 1, 1972 (እንግሊዝኛ) መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “አምልኮ የሚፈጸምበት እውነተኛ ቤተ መቅደስ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
ገጽ 162 አን. 5፣ ሦስተኛው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ትንቢቶች ውስጥ የቤተ መቅደስ መለካት ፍጹም በሆነው የይሖዋ ሕግ መሠረት ፍትሕ እንደሚፈጸም ዋስትና የሚሰጥ ድርጊት ነው።
ገጽ 162 አን. 7፣ መሥመር 9-12 ላይ ያለው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ ቀጥለን እንደምንመለከተው እዚህ ላይ የተጠቀሰው 42 ወር ቃል በቃል የሚወሰድ ሲሆን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሁሉ በከባድ ፈተና ላይ የነበሩበትን ከታኅሣሥ 1914 እስከ ሰኔ 1918 ያለውን ጊዜ ያመለክታል።
ገጽ 164 አን. 12፣ አምስተኛው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ ይህም ከታኅሣሥ 1914 እስከ ሰኔ 1918 ድረስ ያለው ጊዜ ነው።
ገጽ 165፣ ከሥዕሉ ሥር ያለው ሐሳብ በዚህ ይተካ፦ ዘሩባቤልና ኢያሱ ያከናወኑት የግንባታ ሥራ በጌታ ቀን የይሖዋ ምሥክሮች ከአነስተኛ ሁኔታ ተነስተው ትልቅ ጭማሪ እንደሚያገኙ ያመለክታል። እያደገ የሄደውን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል በብሩክሊን ኒው ዮርክ የሚገኙትን ከላይ የሚታዩትን የመሳሰሉ ሕንጻዎች ማስፋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል
ገጽ 165 አን. 15 የመጀመሪያው መሥመር፣ “(ማቴዎስ 17:1-3፤ 25:31)” በዚህ ይተካ፦ (ማቴዎስ 17:1-3)
ምዕራፍ 26
ገጽ 175 አን. 12፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦
* ታሲተስ የተባለው ሮማዊ ታሪክ ጸሐፊ፣ ኢየሩሳሌም በ63 ከዘአበ በተወረረች ጊዜ ክኔዩስ ፖምፒየስ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቶ ምንም ነገር እንዳላገኘ ጽፎአል። በውስጡ የቃል ኪዳኑ ታቦት አልነበረም።—ታሲተስ ታሪክ፣ 5.9
ምዕራፍ 27
ገጽ 185 ሣጥኑ፣ ስድስተኛው አንቀጽ በዚህ ይተካ፦ በእስፓኝ አገር የክርስቲያኖች ቤት ይደፈርና ክርስቲያኖችም ስለ አምላክ ስለተናገሩና ክርስቲያናዊ ስብሰባዎችን ስላደረጉ የገንዘብና የእሥራት ቅጣት ይበየንባቸው ነበር። በ1970 መንግሥት ካቶሊክ ያልሆኑ ሃይማኖቶችን በተመለከተ ይከተለው በነበረው ፖሊሲ ላይ ለውጥ በማድረጉ የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ እውቅና ሲያገኙ ይህ ሁሉ ስደት አበቃ።
ገጽ 185 አን. 28፣ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ይህ ጭካኔ የተሞላበት የስደት ጎርፍ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ። በአውሮፓ ውስጥ 12,000 የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች በናዚ የማጎሪያ ካምፖችና ወኅኒ ቤቶች ውስጥ ታጉረው ነበር። ሁለት ሺህ የሚያህሉም ተገድለዋል።
ምዕራፍ 28
ገጽ 187 አን. 3፣ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ይህ የሚያስፈራ አውሬ ምንድን ነው? መልሱን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ይነግረናል። ባቢሎን በ539 ከዘአበ ከመውደቋ በፊት ዳንኤል የተባለው አይሁዳዊ ነቢይ ስለ አስፈሪ አራዊት ራእይ ተመልክቶ ነበር።
ገጽ 187 አን. 4፣ የግርጌ ማስታወሻው በዚህ ይተካ፦
* ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! የተባለውን በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ መጽሐፍ ገጽ 165-179 ተመልከት።
ገጽ 192 አን. 22፣ ሁለተኛው አምድ ዘጠነኛውና አሥረኛው መሥመር በዚህ ይተካ፦ ይህ ፈተና ድል በተነሱበት ዓመት ማለትም በሰኔ ወር 1918 ከፍተኛውን ደረጃ ያዘ።
ምዕራፍ 29
ገጽ 202 አን. 14፣ ከ1-3 ያሉት መሥመሮች በዚህ ይተኩ፦ 144,000ዎቹ “በምድር ላይ ከሚገኙት የሰው ልጆች መካከል የተዋጁ” ናቸው። የአምላክ ልጆች ሆነው ተቆጥረዋል።
ምዕራፍ 30
ገጽ 206 አን. 3፣ ሁለተኛው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ በ539 ከዘአበ የጥንትዋ ባቢሎን ከወደቀች በኋላ ምን ሆኖ ነበር?
ገጽ 208 የሣጥኑ አምስተኛው አንቀጽ፣ የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ “ዮሐንስ 10ኛ፣ ዘመነ ጵጵስናው ሊፈጸም በተቃረበበት ጊዜ . . . የሮማ ቅድስት እናት ትባል ከነበረችው ከማሮዚያ ጋር ተጣላና ታስሮ ተገደለ።”
ገጽ 212 አን. 23፣ ሦስተኛው፣ አራተኛውና አምስተኛው ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ኢየሱስም ወዲያውኑ ትዕዛዙን ተቀበለ። በመጀመሪያ ደረጃ ከ1919 ጀምሮ በነበረው ጊዜ መላእክቱ 144,000ዎቹን የማጨዱን ሥራ እንዲያጠናቅቁ አደረገ። (ማቴዎስ 13:39, 43፤ ዮሐንስ 15:1, 5, 16) ከዚያም የሌሎች በጎች ክፍል የሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎች የመከር ስብሰባ ሥራ ቀጠለ። (ዮሐንስ 10:16፤ ራእይ 7:9)
ምዕራፍ 32
ገጽ 231 አን. 27፣ “ማቴዎስ 24:42, 44” ከተጠቀሰ በኋላ ያለው የአንቀጹ ክፍል በዚህ ይተካ፦ (ማቴዎስ 24:42, 44፤ ሉቃስ 12:37, 40) ሐዋርያው ጳውሎስም ይህንኑ ማስጠንቀቂያ ሲያስተጋባ የሚከተለውን ጽፎአል:- “የጌታ [የይሖዋ አዓት] ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። ሰላምና ደህንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጉዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፣ ከቶም አያመልጡም።” “ሰላምና ደህንነት” ሆኗል የሚለውን የውሸት አዋጅ የሚያስነግረው ሰይጣን ነው።—1 ተሰሎንቄ 5:2, 3
ምዕራፍ 33
ገጽ 238 ሣጥኑ፣ አንቀጹና የጋዜጣው ቁራጭ በዚህ ይተካ፦ ለራይኩ የተደረገ ‘የጦርነት ቡራኬ’ ቀጥሎ የቀረበው ጽሑፍ ከላይ ባለው ርዕስ ሥር በታኅሣሥ 7, 1941 የኒው ዮርክ ታይምስ የመጀመሪያ እትም ላይ ወጥቶ ነበር:- “በፉልዳ የካቶሊክ አቡኖች በረከትና ድል እንዲገኝ ለመኑ . . . የጀርመን ካቶሊክ አቡኖች በፉልዳ ባደረጉት ስብሰባ በሁሉም መለኮታዊ ቅዳሴዎች መጀመሪያና መጨረሻ ላይ የሚነበብ ልዩ ‘የጦርነት ቡራኬ’ እንዳወጡ አስታወቁ። ቡራኬው አምላክ የጀርመንን የጦር ሠራዊት በመባረክ ድል እንዲሰጣቸውና የሁሉንም ወታደሮች ሕይወትና ጤንነት እንዲጠብቅ የተደረገ ልመና ነው። በተጨማሪም የካቶሊክ ቀሳውስት ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ በልዩ የሰንበት ስብከት ላይ ‘በምድር፣ በባሕርና በአየር’ ያሉ የጀርመን ወታደሮችን እንዲያስቡ አቡኖች አዘዋል።” ይህ ጽሑፍ በጋዜጣው ቀጣይ እትሞች ላይ ሳይካተት ቀርቷል። ታኅሣሥ 7, 1941 የናዚ ጀርመን ተባባሪ የነበረችው ጃፓን፣ ፐርል ሃርበር በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር መርከቦች ላይ ጥቃት የፈጸመችበት ዕለት ነው።
ገጽ 243 አን. 21፣ ከመጨረሻው በፊት ያለው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ ሊቀ ጳጳሱ በንግግራቸው ላይ ለኢየሱስ ክርስቶስም ሆነ ለአምላክ መንግሥት እምብዛም ትኩረት አለመስጠታቸው ሊስተዋል የሚገባው ነው።
ገጽ 245 አን. 25፣ የመጀመሪያው መሥመር “(ራእይ 14:8፤ 17:2)” በዚህ ይተካ፦ (ራእይ 14:8፤ 17:4)
ምዕራፍ 34
ገጽ 246 አን. 1፣ ከ12-14 ያሉት መሥመሮች በዚህ ይተኩ፦ ይሁን እንጂ ራእዩ በዘመናችን በአስገራሚ ሁኔታ እውነት ሆኖአል።
ገጽ 250 አን. 12፣ የግርጌ ማስታወሻው ላይ “1981” የሚለው በዚህ ይተካ፦ 1993
ገጽ 251 አን. 14 በዚህ ይተካ፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የፖለቲካ ሰዎች፣ የተለያዩ ሰብዓዊ እቅዶችን ለመግለጽ “ሰላምና ደኅንነት” በሚለው ሐረግ ሲጠቀሙ ይሰማል። የዓለም መሪዎች ሰላም ለማስፈን የሚያደርጓቸው እንደነዚህ ያሉት ጥረቶች 1 ተሰሎንቄ 5:3 ፍጻሜውን ማግኘት መጀመሩን ያመለክቱ ይሆን? ወይስ ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ሲጽፍ የዓለምን ትኩረት በሙሉ የሚስብ አንድ አስደናቂ ክንውን እንደሚኖር መጠቆሙ ነበር? አብዛኛውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች ሙሉ በሙሉ መረዳት የሚቻለው ፍጻሜያቸውን ካገኙ በኋላ አሊያም እየተፈጸሙ እያሉ ብቻ በመሆኑ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት መታገስ ይኖርብናል። እስከዚያው ድረስ ግን መንግሥታት ሰላምና ደኅንነት በማስፈን ረገድ የቱንም ያህል የተሳካላቸው ቢመስልም ያን ያህል ትልቅ ለውጥ እንደማያመጡ ክርስቲያኖች ያውቃሉ። ራስ ወዳድነት፣ ጥላቻ፣ ወንጀል፣ የቤተሰብ መፈራረስ፣ ብልግና፣ በሽታ፣ ሐዘንና ሞት መኖራቸው አይቀርም። ስለዚህ የዓለም ሁኔታዎችን ትርጉም የምትከታተልና በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ ልብ የምትል ከሆነ “ሰላምና ደኅንነት ነው” የሚለው ጩኸት አንተን ሊያስትህ አይገባም።—ማርቆስ 13:32-37፤ ሉቃስ 21:34-36
ምዕራፍ 36
ገጽ 259 አን. 4፣ የመጨረሻዎቹ ሦስት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ በ1914 ኢየሱስ በሰማይ ንጉሥ ሆነ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የይሖዋ ተባባሪ ንጉሥና ፈራጅ በመሆን በምድር ላይ በሥልጣኑ ሲጠቀም ቆይቷል። በዚህ ምክንያት የታላቂቱ ባቢሎንን ውድቀት የሚያሳውቀው መልአክ ኢየሱስ መሆኑ ተገቢ ነበር።
ገጽ 260 አን. 9፣ የመጀመሪያዎቹ አራት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ በ539 ከዘአበ የደረሰው የጥንትዋ ባቢሎን ውድቀት ለበርካታ ዓመታት ለቀጠለው ማሽቆልቆልና በመጨረሻ ለደረሰባት ፍጹም ባድማነት መጀመሪያ ነበር። በተመሳሳይም የባቢሎናዊው ሃይማኖት ተጽዕኖ ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአስገራሚ ሁኔታ ሲያሽቆለቁል ቆይቶአል። በጃፓን አገር የሺንቶዎች የንጉሠ ነገሥት አምልኮ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ እየከሰመ መጥቶአል።
ገጽ 265 አን. 22፣ የመጨረሻው ጥቅስ ይውጣ፦ ከማቴዎስ 24:15, 16 ጋር አወዳድር።
ገጽ 266 አን. 28፣ ሦስተኛውና አራተኛው ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ እርስዋ ካደረገችው በእጥፍ የሚበልጥ እንድትቀበል ይደረጋል። ታላቂቱ ባቢሎን ለበደለቻቸው ሰዎች ምንም ዓይነት ምህረት ስላላሳየች ለእርሷም ምህረት አይደረግላትም።
ምዕራፍ 38
ገጽ 277 አን. 17፣ የመጨረሻዎቹ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ በዚህ ወቅት በምድር ላይ በሕይወት የሚቆዩ ቅቡዓን ካሉ ክርስቶስ ጠላቶቹን ድል እንደነሳ ወደ ሰማያዊ ውርሻቸው እንደሚገቡና ከቀሩት የሙሽራይቱ ክፍል አባሎች ጋር እንደሚተባበሩ አያጠራጥርም። ከዚያ በኋላ አምላክ በወሰነው ጊዜ የበጉ ሰርግ ሊፈጸም ይችላል!
ገጽ 277 አን. 18፣ የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር በዚህ ይተካ፦ በመዝሙር 45 ላይ የሰፈረው ትንቢታዊ ዘገባ ክንውኖቹ የሚፈጸሙበትን ቅደም ተከተል ያሳያል።
ምዕራፍ 39
ገጽ 281 አን. 10፣ የመጨረሻዎቹ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ ከዚህም በላይ ኢየሱስ የምድርን አሕዛብና ወገኖች ለመፍረድ ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ “መላእክቱ ሁሉ” ዙፋኑን አጅበው ያገለግሉታል። (ማቴዎስ 25:31, 32) ወሳኝ በሆነው በዚህ ውጊያ የአምላክ ፍርድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሲፈጸም ኢየሱስ በመላእክቱ እንደሚታጀብ የተረጋገጠ ነው።
ምዕራፍ 41
ገጽ 296 አን. 5፣ የመጀመሪያዎቹ አራት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ አሮጌው ምድርና አሮጌው ሰማይ ከሸሹ በኋላ ለፍርድ የሚቀሩት እነማን ናቸው? የ144, 000ዎቹ ቅቡዓን ቀሪዎች ሊሆኑ አይችሉም። ምክንያቱም እነዚህ ቀደም ሲል ተፈርዶላቸው ታትመዋል። ከአርማጌዶን በኋላ በምድር ላይ በሕይወት የሚገኙ ቅቡዓን ካሉ፣ እነርሱም ብዙ ሳይቆዩ መሞትና በትንሣኤ አማካኝነት ሰማያዊ ሽልማታቸውን ማግኘት ይገባቸዋል። (1 ጴጥሮስ 4:17፤ ራእይ 7:2-4)
ምዕራፍ 43
ገጽ 311 አን. 19፣ “ራእይ 11:15፤ 12:10” ከሚሉት ጥቅሶች በኋላ ያሉት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ በመጨረሻው ዘመን፣ መንፈስና ሙሽራይቱ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች የሕይወትን ውኃ በነጻ እንዲወስዱ ሲጋብዙ ቆይተዋል። የወንዙ ውኃ እስከ ሥርዓቱ መደምደሚያ ድረስ እንደዚህ ላሉት ሰዎች የሚቀርብ ሲሆን ከዚያም በኋላ በአዲሱ ሥርዓት ውስጥ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ‘ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ በምትወርድበት’ ጊዜም መፍሰሱን ይቀጥላል።—ራእይ 21:2
ገጽ 312 አን. 26፣ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓረፍተ ነገሮች በዚህ ይተኩ፦ እነዚህ ከወንዙ የሚጠጡት ዛፎች የበጉን ሚስት 144,000 አባሎች ሊጨምሩ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች በምድር ላይ በነበሩበት ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከተደረገላቸው የሕይወት ዝግጅት ጠጥተው ነበር። በመንፈስ የተቀቡት እነዚህ የኢየሱስ ወንድሞች በትንቢት “የጽድቅ ዛፎች” ተብለው መጠራታቸው ትኩረት የሚስብ ነው። (ኢሳይያስ 61:1-3፤ ራእይ 21:6)