መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“በየቀኑ ማለት ይቻላል የክፋት ድርጊቶችን ስለፈጸሙ ሰዎች የሚናገሩ ዜናዎችን እንሰማለን። [በአካባቢው የሚታወቅ በቅርቡ የተፈጸመ አንድ ምሳሌ ጥቀስ።] ሰዎች እንዲህ ዓይነት ነገሮችን እንዲፈጽሙ የሚገፋፋ የማይታይ ክፉ ኃይል ይኖር ይሆን ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ራእይ 12:12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ 2007
“ለመኖር ሁላችንም ገንዘብ ያስፈልገናል። ሆኖም ገንዘብ ለማግኘት ከልክ በላይ መጨነቅ አለብን ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ሀብትን ማሳደድ የሚያስከትላቸውን ችግሮች በተመለከተ ይህ ጥቅስ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [1 ጢሞቴዎስ 6:10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንድ ሰው ኑሮውን በማቅለል በአነስተኛ ገቢ መኖር የሚችለው እንዴት እንደሆነ የሚገልጹ ተግባራዊ ሐሳቦችን ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“በዛሬው ጊዜ በርካታ ሰዎች ጥሩና መጥፎ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ የራሳቸውን መሥፈርቶች እንደሚያወጡ አስተውለዋል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት ጊዜ የማይሽራቸው መመሪያዎች ውስጥ አንዱን ይመልከቱ። [በገጽ 6 እና 7 ላይ ከሚገኘው ሣጥን ውስጥ አንድ ጥቅስ አንብብ።] ይህ መጽሔት የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ምግባር መመሪያዎች በመከተል ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሐምሌ 2007
“ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን በራሳቸው መንገድ ይመራሉ፤ እንዲሁም ጥሩ ሰው መሆን አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ይህን በሚመለከት ምን ይላሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እኛ ጥሩ ነው ያልነው ነገር አምላክ ጥሩ ነው ከሚለው ነገር ከተለየ ምን አደጋ እንደሚኖረው ይመልከቱ። [ምሳሌ 14:12ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በአምላክ አመለካከት ጥሩ ሰው መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል።” በገጽ 20 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።