የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 2 ገጽ 8-10
  • የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ የትኞቹ ክንውኖች እንደሚፈጸሙ ተናግሯል?
  • ምልክቱ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?
  • “የዓለም መጨረሻ” ደርሷል!
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • የመጨረሻ ቀኖች
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ታላላቅ የምድር ነውጦች—የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 2 ገጽ 8-10
አንዲት የይሖዋ ምሥክር ወደ ጽሑፍ ጋሪው ለመጣች አንዲት ሴት መጋበዣ ወረቀት ስትሰጣት

የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?

ከኢየሱስ ታማኝ ተከታዮች መካከል አንዳንዶቹ የአምላክ መንግሥት መግዛት የሚጀምረው መቼ እንደሆነ ማወቅ ፈልገው ነበር። ኢየሱስም ለጥያቄያቸው መልስ ሲሰጥ የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛበትን ትክክለኛ ጊዜ ማወቅ እንደማይችሉ ነግሯቸዋል። (የሐዋርያት ሥራ 1:6, 7) ከዚያ ቀደም ብሎ ግን ኢየሱስ፣ አንዳንድ ክንውኖች በተመሳሳይ ጊዜ ላይ መፈጸም ሲጀምሩ “የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ” እና ይህ መንግሥት ምድርን የሚገዛበት ጊዜ እንደደረሰ ተከታዮቹ ማወቅ እንደሚችሉ ነግሯቸው ነበር።—ሉቃስ 21:31

ኢየሱስ የትኞቹ ክንውኖች እንደሚፈጸሙ ተናግሯል?

ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል። ታላላቅ የምድር ነውጦች ይከሰታሉ፤ በተለያየ ስፍራም የምግብ እጥረትና ቸነፈር ይሆናል።” (ሉቃስ 21:10, 11) ጣታችን ላይ ያሉት የተለያዩ መስመሮች አንድ ላይ ተደምረው የጣት አሻራ እንደሚሆኑ ሁሉ እነዚህ ክንውኖችም አንድ ላይ ተደምረው የማያሻማ ምልክት ይሰጣሉ። በተጨማሪም የጣት አሻራ አንድን ሰው ለመለየት እንደሚያስችል ሁሉ በተመሳሳይ ጊዜ ላይ የሚፈጸሙት እነዚህ ክንውኖችም “የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ” ለመለየት ያስችላሉ። ታዲያ እነዚህ ክንውኖች በሙሉ በተመሳሳይ ጊዜ ላይ ተፈጽመዋል? በዓለም አቀፍ ደረጃስ እየታዩ ነው? እስቲ ማስረጃዎቹን እንመልከት።

1. ጦርነት

የጦር ጄቶች፣ ታንክና ሚሳይሎች

በ1914 በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማያውቅ ታላቅ ጦርነት ፈነዳ! ብዙ ጊዜ የታሪክ ምሁራን 1914⁠ን ‘አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የተከፈተበት ዓመት’ በማለት ይጠሩታል፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የፈነዳው በዚህ ዓመት ነው። እንደ ታንኮች፣ ከአውሮፕላን የሚወረወሩ ቦምቦች፣ መትረየሶችና መርዛማ ጋዞች ያሉ አውዳሚ የጦር መሣሪያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉት በዚህ ጦርነት ላይ ነበር። ይህ ጦርነት አቶሚክ የጦር መሣሪያዎች ጥቅም ላይ መዋል ወደጀመሩበት ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አምርቷል። ከ1914 አንስቶ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጦርነቶችን ያካሄዱ ሲሆን በእነዚህ ጦርነቶች ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

2. የመሬት መንቀጥቀጥ

በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት እየፈራረሱ ያሉ ሕንፃዎች

ብሪታኒካ አካዴሚክ እንደገለጸው በየዓመቱ “ከፍተኛ ጉዳት” ሊያስከትሉ የሚችሉ 100 ገደማ የሚሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች ይከሰታሉ። የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂ ጥናት ተቋም የሚከተለውን ሪፖርት አቅርቧል፦ “ለረጅም ጊዜ (ከ1900ዎቹ ገደማ ጀምሮ) በተመዘገበው መረጃ መሠረት በማንኛውም ዓመት ውስጥ 16 ገደማ የሚሆኑ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጦች እንደሚከሰቱ እንጠብቃለን።” አንዳንዶች በዓለማችን ላይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ቁጥር የጨመረ የሚመስለው ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ይህን ክስተት ማወቅ ስለተቻለ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱ ታላላቅ የመሬት መንቀጥቀጦች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን ለብዙ ሰዎች መሠቃየትና መሞት ምክንያት እየሆኑ ነው።

3. የምግብ እጥረት

የእህል ምርት እየቀነሰ እንደሆነ የሚያሳይ ግራፍ

በዓለም ዙሪያ የምግብ እጥረት የሚከሰተው በጦርነት፣ በሙስና፣ በኢኮኖሚ ውድቀት፣ ኋላቀር በሆነ የግብርና አሠራር አሊያም ለከባድ የአየር ጠባይ ቅድመ ዝግጅት ባለማድረግ ነው። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ያወጣው “የ2018 ሪፖርት” እንዲህ ይላል፦ “በዓለም ዙሪያ 821 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች በቂ ምግብ አያገኙም፤ ከእነዚህ ውስጥ 124 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በከባድ ረሃብ ይሠቃያሉ።” በየዓመቱ 3.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ልጆች በተመጣጠነ ምግብ እጦት ምክንያት ለሞት ይዳረጋሉ። ይህም በ2011 በዓለም ዙሪያ ከተመዘገበው የልጆች ሞት መካከል 45 በመቶ የሚሆነው ማለት ነው።

4. በሽታና ወረርሽኝ

ባዮኬሚካላዊ አደጋዎችንና ባክቴሪያዎችን የሚያሳይ ምልክት

የዓለም የጤና ድርጅት ያወጣው ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “21ኛው መቶ ዘመን ገና ከወዲሁ ከባድ ወረርሽኞች የተመዘገቡበት ዘመን ሆኗል። እንደ ኮሌራና ቢጫ ወባ ያሉ ነባር በሽታዎች ዳግመኛ ያገረሹ ሲሆን እንደ ሳርስ፣ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ፣ መርስ፣ ኢቦላና ዚካ ያሉ አዳዲስ በሽታዎች ደግሞ ብቅ ብቅ ብለዋል።” በቅርቡ ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተከስቷል። የሳይንስ ሊቃውንትና ሐኪሞች ስለ በሽታ ብዙ ነገር ማወቅ የቻሉ ቢሆንም ለበርካታ በሽታዎች መድኃኒት ማግኘት አልቻሉም።

5. ዓለም አቀፍ የስብከት ሥራ

ዙሪያዋን ቀስት ያላት ምድር፤ ከጎኗ የተከፈተ መጽሐፍ ቅዱስ አለ

ኢየሱስ የምልክቱን ተጨማሪ ገጽታ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24:14) ዓለም በችግር እየታመሰ ባለበት በዚህ ጊዜ፣ ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ከስምንት ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች የአምላክን መንግሥት ምሥራች በ240 አገሮች ከ1,000 በሚበልጡ ቋንቋዎች እየሰበኩ ነው። በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ እንዲህ ያለ መጠነ ሰፊ የስብከት ዘመቻ ተደርጎ አያውቅም።

ምልክቱ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?

ኢየሱስ የተናገረው ምልክት ክፍል የሆኑት ክንውኖች በዛሬው ጊዜ እየተፈጸሙ ነው። ይህ ጉዳይ ትኩረታችንን ሊስበው የሚገባው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ኢየሱስ “እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ ስታዩ የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እርግጠኞች ሁኑ” ብሏል።—ሉቃስ 21:31

ኢየሱስ በሰማይ በንጉሣዊ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ገነት የሆነችውን ምድር ሲገዛ

የአምላክ መንግሥት በቅርቡ የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም ያደርጋል

ኢየሱስ የሰጠው ምልክት እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚጠቅሰው የዘመን ስሌት፣ አምላክ መንግሥቱን በሰማይ ያቋቋመው በ1914 እንደሆነ ለመረዳት ያስችለናል።a በዚያን ጊዜ አምላክ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። (መዝሙር 2:2, 4, 6-9) በቅርቡ የአምላክ መንግሥት ምድርን መግዛት የሚጀምር ሲሆን ሌሎች መንግሥታትን በሙሉ አጥፍቶ ምድርን ወደ ገነትነት በመለወጥ ሰዎች ለዘላለም በዚያ እንዲኖሩ ያደርጋል።

ኢየሱስ ባስተማረው የጸሎት ናሙና ላይ የሚገኘው “መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም” የሚለው ልመና በቅርቡ ምላሽ ያገኛል። (ማቴዎስ 6:10) ይሁንና የአምላክ መንግሥት በ1914 ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ምን ነገሮችን ሲያከናውን ቆይቷል? ይህ መንግሥት ሙሉ በሙሉ የሰው ልጆችን ማስተዳደር ሲጀምርስ ምን ነገሮች እንደሚፈጸሙ መጠበቅ እንችላለን?

a ስለ 1914 ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 32 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ