የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/09 ገጽ 2
  • ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የበላይ አካሉ መልእክት
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • የበላይ አካሉ መልእክት
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • “አምላክን መውደድ” ሲባል ምን ማለት ነው?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • የአምላክ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 1/09 ገጽ 2

‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’

1. ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለው መጽሐፍ የተዘጋጀበት ዓላማ ምንድን ነው?

1 ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን አዲስ መጽሐፍ በማግኘታችን በጣም ተደስተናል! የበላይ አካሉ፣ ይሖዋን ለሚወዱ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ መደምደሚያ ላይ እንደሚከተለው ብሏል፦ “ይህ መጽሐፍ እውነትን በዕለት ተዕለት ሕይወትህ በሥራ ላይ እንድታውል እንዲሁም ‘የዘላለምን ሕይወት እየተጠባበቅክ ከአምላክ ፍቅር’ ሳትወጣ እንድትኖር የሚረዳህ እንዲሆን ምኞታችን ነው።—ይሁዳ 21”

2. ይህ አዲስ መጽሐፍ በየትኞቹ የሕይወታችን ዘርፎች ይረዳናል?

2 ከመጽሐፉ የምናገኘው ነገር፦ በጓደኛ ምርጫ፣ በመዝናኛ፣ በትዳር፣ በአንደበት አጠቃቀም፣ ለሥልጣን አክብሮት በማሳየት፣ በልማዶቻችን እንዲሁም በአኗኗር ዘይቤያችንና በመሳሰሉት ነገሮች ረገድ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ይህ መጽሐፍ፣ በአምላክ ቃል ውስጥ ተገልጸው በሚገኙት ላቅ ያሉ የጽድቅ መሥፈርቶች አማካኝነት ሕሊናችንን ለማሠልጠን ይረዳናል። (መዝ. 19:7, 8) የይሖዋን አስተሳሰብ ይበልጥ እየተረዳን በሄድን መጠን እሱን ለማስደሰት ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረናል፤ ይህ ደግሞ በመላው የሕይወታችን ዘርፍ ታዛዥ እንድንሆን ያደርገናል።—ምሳሌ 27:11፤ 1 ዮሐ. 5:3

3. ይህ መጽሐፍ በሚጠናበት ወቅት ጥሩ ተሳትፎ ለማድረግ የቻልነውን ያህል መጣር ያለብን ለምንድን ነው?

3 በዚህ መጽሐፍ ለመጠቀም ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ፦ ይህን መጽሐፍ ወደፊት በጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ለማጥናት በጉጉት እየተጠባበቅን ቢሆንም የመጽሐፉን ይዘት በሚገባ ለማወቅ አሁኑኑ ማንበብ እንድትጀምሩ እናበረታታችኋለን። እንዲህ ማድረጋችን ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት ብቻ ሳይሆን ምሽት ላይ በምናደርገው የቤተሰብ የአምልኮ ፕሮግራም ላይ አንዳንድ ጊዜ ይህን መጽሐፍ ለመጠቀምም ያስችለናል። ወደፊት ይህን መጽሐፍ በምናጠናበት ጊዜ የምንሰጣቸው በደንብ የታሰበባቸው እጥር ምጥን ያሉ ሐሳቦች ሌሎች ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች እንዲነቃቁ ያደርጋሉ፤ እንዲሁም በጥናቱ ወቅት ሞቅ ያለና ትርጉም ያለው ውይይት እንዲኖር አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። (ዕብ. 10:24) ከዚህም በተጨማሪ በምንሰጣቸው ሐሳቦች አማካኝነት እምነታችንን በሌሎች ፊት መግለጻችን ደስታ ያስገኝልናል።

4. የይሖዋን ትእዛዛት ማክበራችን እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

4 ኢየሱስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ ባሳለፈው የመጨረሻ ምሽት፣ የይሖዋን ትእዛዛት ማክበር ከአምላክ ፍቅር ሳይወጡ ከመኖር ጋር ግንኙነት እንዳለው ገልጿል። (ዮሐ. 15:10) ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለው መጽሐፍ በሚሰጠን እርዳታ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በአኗኗራችን ተግባራዊ ለማድረግና ‘ከአምላክ ፍቅር ሳንወጣ ለመኖር’ ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ።—ይሁዳ 21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ