የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/11 ገጽ 1
  • “ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ርኅሩኆች” ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • እንደ ይሖዋ ሩኅሩኅ ሁኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ይሖዋ የሚገዛው በርኅራኄ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
km 7/11 ገጽ 1

“ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ”

1. በዛሬው ጊዜ ሰዎች በጣም የሚያስፈልጋቸው ነገር ምንድን ነው?

1 በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ እንደ አሁኑ ጊዜ ያህል ርኅራኄ የታከለበት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች ኖረው አያውቁም። በዓለም ላይ የሚታዩት ሁኔታዎች እያሽቆለቆሉ መሄዳቸው የደስታ ማጣትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዲሁም የመንፈስ ጭንቀት እንዲስፋፋ አድርጓል። በመሆኑም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፤ እኛ ደግሞ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት የማሳየት አጋጣሚ ተከፍቶልናል። (ማቴ. 22:39፤ ገላ. 6:10) እንዲህ ዓይነቱን አሳቢነት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

2. ለሰዎች ርኅራኄ ማሳየት የምንችልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው?

2 ርኅራኄ የሚንጸባረቅበት ሥራ፦ እውነተኛና ዘላቂ የሆነ መጽናኛ ሊገኝ የሚችለው ከአምላክ ብቻ ነው። (2 ቆሮ. 1:3, 4) ይሖዋ የእሱን ምሳሌ በመከተል እኛም ‘ከአንጀት የምንራራ እንድንሆን’ ያሳስበናል፤ እንዲሁም ለሰዎች የመንግሥቱን ምሥራች እንድንሰብክ ተልእኮ ሰጥቶናል። (1 ጴጥ. 3:8) በሥቃይ ላይ ላለው የሰው ዘር ብቸኛው ተስፋ የአምላክ መንግሥት ስለሆነ “ልባቸው የተሰበረውን” ሰዎች ማጽናናት የምንችልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ በዚህ ሥራ በንቃት መሳተፍ ነው። (ኢሳ. 61:1) ይሖዋ ለሕዝቡ ካለው ርኅራኄ የተነሳ ክፋትን ለማስወገድና ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ዓለም ለማስፈን በቅርቡ እርምጃ ይወስዳል።​—2 ጴጥ. 3:13

3. ኢየሱስ ለሰዎች የነበረው ዓይነት አመለካከት ማንጸባረቅ የምንችለው እንዴት ነው?

3 ኢየሱስ ለሰዎች የነበረው ዓይነት አመለካከት ይኑራችሁ፦ ኢየሱስ ለብዙ ሰዎች ይሰብክ በነበረበት ጊዜም እንኳ ሕዝቡን እንዲሁ በጥቅሉ አልተመለከተም። ለሰዎቹ መንፈሳዊ ፍላጎት በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ሰጥቷል። ሰዎቹ የሚመራቸው እረኛ እንደሌላቸው በጎች ነበሩ። ኢየሱስ በተመለከተው ነገር ልቡ ስለተነካ እነሱን በትዕግሥት ለማስተማር ተገፋፍቷል። (ማር. 6:34) ኢየሱስ ለሰዎች የነበረው ዓይነት አመለካከት ማዳበራችን በግለሰብ ደረጃ ልባዊ ርኅራኄ እንድናሳያቸው ያነሳሳናል። ይህ ደግሞ በድምፃችን ቃና የሚታወቅ ከመሆኑም በላይ ፊታችን ላይ ይነበባል። የስብከቱ ሥራ በሕይወታችን ውስጥ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ይሆናል፤ እንዲሁም ሰዎቹ በግለሰብ ደረጃ የሚያሳስባቸውን ነገር አንስተን ለማወያየት ጥረት እናደርጋለን።​—1 ቆሮ. 9:19-23

4. የርኅራኄ ባሕርይ መላበስ ያለብን ለምንድን ነው?

4 ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ እጅግ ብዙ ሕዝቦች ለመንግሥቱ መልእክትና በግለሰብ ደረጃ ለተሰጣቸው ትኩረት ጥሩ ምላሽ እየሰጡ ነው። የርኅራኄ ባሕርይ መላበሳችንን በቀጠልን መጠን ሩኅሩኅ የሆነውን አምላካችንን ይሖዋን እናስከብረዋለን፤ ደግሞም እናስደስተዋለን።​—ቆላ. 3:12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ