የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/13 ገጽ 1
  • ለመስበክ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለመስበክ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጎረቤትን መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ፍቅራችሁ ምን ያህል ሰፊ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ትወዳለህ?’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 5/13 ገጽ 1

ለመስበክ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

1. በፍቅርና በአገልግሎታችን መካከል ምን ዝምድና አለ?

1 የአምላክን መንግሥት ምሥራች መስበክ በዛሬው ጊዜ ልናከናውናቸው ከምንችላቸው ትርጉም ያላቸው ሥራዎች ሁሉ የላቀው ነው። ይህን ሥራ መሥራታችን ከሁሉ የላቁትን ሁለት ትእዛዛት እንደምንፈጽም ማለትም ይሖዋንና ሰዎችን እንደምንወድድ ያሳያል። (ማር. 12:29-31) በመሆኑም ቀናተኛ አገልጋዮች ለመሆን የሚያነሳሳን ዋነኛ ምክንያት ፍቅር ነው።—1 ዮሐ. 5:3

2. በስብከቱ ሥራ መካፈላችን ለአምላክ ያለንን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው?

2 ለይሖዋ ያለን ፍቅር፦ የቅርብ ወዳጃችን ለሆነው ለይሖዋ ያለን ፍቅር ስለ እሱ እንድንመሠክር ያነሳሳናል። ለ6,000 ዓመታት ገደማ ሰይጣን የይሖዋን ስም ሲያጠፋ ቆይቷል። (2 ቆሮ. 4:3, 4) ከዚህም የተነሳ ብዙዎች አምላክ ኃጢአተኞችን በእሳት ለዘላለም እንደሚያሠቃይ፣ ሚስጥረ ሥላሴ እንደሆነ እንዲሁም ስለ ሰው ዘር ምንም እንደማያስብ ይሰማቸዋል። እንዲያውም በርካታ ሰዎች አምላክ የለሽ ሆነዋል። ታዲያ ሰዎች በሰማይ ስለሚኖረው አባታችን እውነቱን እንዲያውቁ ለማድረግ ከፍተኛ ጉጉት ሊያድርብን አይገባም? ስለ አምላክ ለመመሥከር የምናደርገው ልባዊ ጥረት ይሖዋን በጣም የሚያስደስተው ሲሆን ሰይጣንን ግን ያበሳጨዋል።—ምሳሌ 27:11፤ ዕብ. 13:15, 16

3. አገልግሎታችን ለሰዎች ያለንን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት ነው?

3 ለሰዎች ያለን ፍቅር፦ ለአንድ ሰው ስንመሠክር ለግለሰቡ ፍቅር እንዳለን በግልጽ እናሳያለን። ለመቋቋም በሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ በሆነው በዚህ ዘመን ውስጥ ሰዎች ምሥራቹን መስማት በጣም ያስፈልጋቸዋል። በዮናስ ዘመን እንደነበሩት የነነዌ ነዋሪዎች ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎችም “ቀኝና ግራቸውን” መለየት የማይችሉ ናቸው። (ዮናስ 4:11) የምናከናውነው አገልግሎት ሰዎች ደስተኛና ስኬታማ ሕይወት እንዲመሩ ይረዳቸዋል። (ኢሳ. 48:17-19) እንዲሁም ተስፋ ይሰጣቸዋል። (ሮም 15:4) የተማሩትን ነገር ሰምተው በዚያ መሠረት የሚኖሩ ከሆነ ‘ይድናሉ።’—ሮም 10:13, 14

4. ይሖዋ የትኛውን ነገር ፈጽሞ አይረሳም?

4 ጥሩ ልጆች ለወላጆቻቸው ያላቸውን ፍቅር የሚገልጹት በፕሮግራም ብቻ አይደለም። ምንጊዜም ለወላጆቻቸው ያላቸውን ፍቅር ለማሳየት ጥረት ያደርጋሉ። በተመሳሳይም ለይሖዋና ለሰዎች ያለን ልባዊ ፍቅር መደበኛ አገልግሎታችንን ስናከናውን ብቻ ሳይሆን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለመመሥከር ንቁ እንድንሆን ያነሳሳናል። እንዲሁም ምሥራቹን ያለማሰለስ እንሰብካለን። (ሥራ 5:42) ይሖዋ ደግሞ እንዲህ ያለውን ፍቅር ፈጽሞ አይረሳም።—ዕብ. 6:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ