በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ስለ መንግሥቱ በድፍረት መናገር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በ2 ጢሞቴዎስ 1:7, 8 ላይ የሚገኘውን ግልጽ መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከፈለግን ስለ መንግሥቱ በድፍረት መናገር ይኖርብናል። ታዲያ መንግሥቱን በድፍረት ማሳወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
ምሥራቹን ለማን እንደምትነግሩ አስቡ። ይሖዋ ድፍረት እንዲሰጣችሁና ለመስበክ የሚያስችል አጋጣሚ እንዲከፍትላችሁ ጸልዩ።