የወሩ ጭብጥ፦ “ቃሉን ስበክ፣ . . . በጥድፊያ ስሜት አገልግል።”—2 ጢሞ. 4:2
ስለ 1914 ያለንን እምነት ማስረዳት
መጽሐፍ ቅዱስ እምነታችንን አስመልክቶ ለሚቀርቡልን ጥያቄዎች “መልስ ለመስጠት ዘወትር ዝግጁዎች” እንድንሆን ያበረታታናል፤ እንዲሁም ይህን የምናደርገው “በገርነት መንፈስና በጥልቅ አክብሮት” መሆን እንዳለበት ይናገራል። (1 ጴጥ. 3:15) እርግጥ ነው፣ ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን ማብራራት ከባድ ሊሆንብን ይችላል፤ ለምሳሌ የአምላክ መንግሥት መግዛት የጀመረው በ1914 ነው ብለን የምናምንበትን ምክንያት ማብራራት ሊከብደን ይችላል። በዚህ ረገድ እኛን ለመርዳት ሲባል “መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት—የአምላክ መንግሥት መግዛት የጀመረው መቼ ነው?” የተባለ ባለሁለት ክፍል ተከታታይ ርዕስ ተዘጋጅቶልናል። እነዚህ ርዕሶች የሚወጡት በጥቅምትና በኅዳር ወር በምናበረክታቸው የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ ነው። እነዚህን ርዕሶች ስታነብቡ ዳዊት የተባለው አስፋፊ ለአገልግሎት የተጠቀመበትን አቀራረብ በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ በሉ።
የሚከተሉትን ዘዴዎች የተጠቀመባቸው እንዴት ነው?
በጋራ በሚያስማሙ ነጥቦች ላይ ለማተኮር ሲል አድናቆቱን የገለጸው እንዴት ነው? —ሥራ 17:22
ስለ እምነቱ ሲናገር ትሕትና ያሳየው እንዴት ነው?—ሥራ 14:15
የሚከተሉትን ነገሮች ማድረጉ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው?
አዲስ ሐሳብ ከማንሳቱ በፊት አለፍ አለፍ እያለ የተወያዩባቸውን ነጥቦች ጠቅለል አድርጎ መከለሱ
ሲያብራራለት የቆየውን ሐሳብ ተረድቶት እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ በየመሃሉ መጠየቁ
በአንድ ጊዜ ብዙ ነጥቦችን ለመሸፈን አለመሞከሩ—ዮሐ. 16:12
ታላቁ ‘አስተማሪያችን’ ይሖዋ ጥልቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን እውነትን ለተጠሙ ሰዎች ማስረዳት የምንችልበትን መንገድ ስላስተማረን በጣም አመስጋኞች ነን!—ኢሳ. 30:20