የወሩ ጭብጥ፦ “ቃሉን ስበክ፣ . . . በጥድፊያ ስሜት አገልግል።”—2 ጢሞ. 4:2
በስብከቱ ሥራችን የጥድፊያ ስሜት እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
የጥድፊያ ስሜት እንዲኖረን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል፤ በተለይም ይህ ሥርዓት በሚጠፋበት ጊዜ በሕይወት ለመትረፍ እንዲህ ማድረጋችን በጣም አስፈላጊ ነው። ለሚከተሉት ማሳሰቢያዎች ትኩረት በመስጠት የጥድፊያ ስሜታችን እንዳይጠፋ ማድረግ እንችላለን።
ስለ መንግሥቱ አዘውትረን መጸለይ።—ማቴ. 6:10
መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ በማንበብ ልባችንን መጠበቅ።—ዕብ. 3:12
ጊዜያችንን በጥበብ መጠቀም።—ኤፌ. 5:15, 16፤ ፊልጵ. 1:10
ዓይናችን ምንጊዜም “አጥርቶ የሚያይ” እንዲሆን ማድረግ። ትኩረታችን በዓለማዊ ምኞቶች እንዳይከፋፈል መጠንቀቅ።—ማቴ. 6:22, 25፤ 2 ጢሞ. 4:10
የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን አፈጻጸም ትኩረት ሰጥቶ በመከታተል ነቅቶ መጠበቅ።—ማር. 13:35-37
የጥድፊያ ስሜት ያለን መሆኑ አሁን እየተከናወነ ባለው ሥራ ላይ የተሟላ ተሳትፎ እንድናደርግ ያነሳሳናል።—ዮሐ. 4:34, 35