ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ዕንባቆም
1. ነቢዩ ዕንባቆም የተሰማው ዓይነት ስሜት ሊሰማን የሚችለው ለምንድን ነው?
1 በዙሪያችን ባለው ዓለም ላይ ክፋት እየበዛ መሄዱን ስንመለከት እኛም ልክ እንደ ዕንባቆም ሊሰማን ይችላል፤ ዕንባቆም “ለምን በደል ሲፈጸም እንዳይ ታደርገኛለህ? ጭቆናንስ ለምን ዝም ብለህ ታያለህ?” ሲል ይሖዋን ጠይቋል። (ዕን. 1:3፤ 2 ጢሞ. 3:1, 13) ዕንባቆም በጻፈው መልእክትና በተወው የታማኝነት ምሳሌ ላይ ማሰላሰላችን የይሖዋን የፍርድ ቀን በጽናት እንድንጠብቅ ሊረዳን ይችላል።—2 ጴጥ. 3:7
2. በዛሬው ጊዜ በእምነት እንደምንኖር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
2 በእምነት ኑሩ፦ ዕንባቆም በወቅቱ በነበረው መጥፎ ሁኔታ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በመንፈሳዊ ንቁ ሆኖ ቀጥሏል። (ዕን. 2:1) ይሖዋም የገባው ቃል በተወሰነለት ጊዜ እንደሚፈጸምና ‘ጻድቅ በእምነቱ በሕይወት እንደሚኖር’ ለነቢዩ ማረጋገጫ ሰጥቶታል። (ዕን. 2:2-4 ግርጌ) በመጨረሻው ዘመን መደምደሚያ ላይ ለሚገኙ ክርስቲያኖች ይህ ምን ትርጉም ይኖረዋል? መጨረሻው እንደሚመጣ በእርግጠኝነት ማመን፣ መቼ እንደሚመጣ ከማወቅ የበለጠ ጥቅም አለው። እምነት፣ ንቁ እንድንሆንና ለአገልግሎት ቅድሚያ እንድንሰጥ ያነሳሳናል።—ዕብ. 10:38, 39
3. ከይሖዋ አገልግሎት የምናገኘውን ደስታ ይዘን መቀጠል ያለብን ለምንድን ነው?
3 በይሖዋ ሐሴት አድርጉ፦ የማጎጉ ጎግ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ እምነታችን ይፈተናል። (ሕዝ. 38:2, 10-12) ጦርነት፣ በድል አድራጊዎቹ ላይም እንኳ ችግር ማስከተሉ አይቀርም። የምግብ እጥረት ሊያጋጥም፣ ንብረት ሊጠፋና የኑሮ ደረጃ ሊያሽቆለቁል ይችላል። ታዲያ ችግሮች በሚከሰቱበት ወቅት ምን እናደርጋለን? ዕንባቆም ችግር እንደሚኖር ስለጠበቀ በይሖዋ አገልግሎት የሚያገኘውን ደስታ ይዞ ለመቀጠል ቆርጦ ነበር። (ዕን. 3:16-19) በተጨማሪም “የይሖዋ ደስታ” ወደፊት የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጽናት እንድንወጣ ይረዳናል።—ነህ. 8:10፤ ዕብ. 12:2
4. አሁንም ሆነ ወደፊት ምን ደስታ ማጣጣም እንችላለን?
4 ይሖዋ ከሚመጣው የፍርድ ቀን በሕይወት እንዲተርፉ የሚያደርጋቸው ሰዎች፣ የእሱን የሕይወት መንገድ መማራቸውን ይቀጥላሉ። (ዕን. 2:14) ከሞት የሚነሱ ሰዎችም ስለ ይሖዋ ይማራሉ። አሁንም ቢሆን፣ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ስለ ይሖዋና ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንናገር!—መዝ. 34:1፤ 71:17