ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢዮብ 16-20 ደግነት በተሞላበት መንገድ በመናገር ሌሎችን ማበረታታትና ማጠናከር አንድ ሰው ምክር ሲሰጥ የሚናገራቸው ቃላት ሌሎችን ማበረታታት አለባቸው 16:4, 5 ኢዮብ ተስፋ ስለቆረጠና ሥቃይ ስለበዛበት ድጋፍና ማበረታቻ ያስፈልገው ነበር ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች እሱን የሚያጽናና ምንም ነገር አልተናገሩም። እንዲያውም እሱን በመወንጀል ጭንቀቱን አባብሰውበታል በልዳዶስ የተናገራቸው ደግነት የጎደላቸው ቃላት ኢዮብን በጣም ጎድተውት ነበር 19:2, 25 ኢዮብ አምላክ ከሥቃዩ እንዲገላግለው ተማጽኗል፤ ሌላው ቀርቶ ሞትን እንኳ ተመኝቷል ኢዮብ ትኩረቱን በትንሣኤ ተስፋ ላይ ያደረገ ሲሆን እስከ መጨረሻው ድረስ በታማኝነት ጸንቷል