ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 87-91
ከልዑሉ አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ አትውጡ
የይሖዋ “ሚስጥራዊ ቦታ” መንፈሳዊ ጥበቃ ያስገኛል
በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ሚስጥራዊ ቦታ ለመኖር ራሳችንን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብናል
በአምላክ የማይታመኑ ሰዎች ይህን ቦታ አያውቁትም
በይሖዋ ሚስጥራዊ ቦታ ያሉ ሰዎችን ማንም ሰው ወይም ምንም ነገር በአምላክ ላይ ያላቸውን እምነት ወይም ለእሱ ያላቸውን ፍቅር ሊያሳጣቸው አይችልም
“ወፍ አዳኙ” እኛን ለማጥመድ ጥረት ያደርጋል
ወፎች ንቁ ስለሆኑ እነሱን ማጥመድ ከባድ ነው
ወፍ አዳኙ የወፎቹን ባሕርይና እነሱን ማጥመድ የሚችልበትን መንገድ በጥንቃቄ ያጠናል
“ወፍ አዳኙ” የተባለው ሰይጣን የይሖዋን ሕዝቦች ያጠናል፤ ከዚያም መንፈሳዊ ጉዳት የሚያስከትልባቸውን ወጥመድ ያስቀምጣል
ሰይጣን የሚጠቀምባቸው አራት አደገኛ ወጥመዶች፦
ሰውን መፍራት
ፍቅረ ንዋይ
ጤናማ ያልሆነ መዝናኛ
በግለሰቦች መካከል የሚፈጠር አለመግባባት