ዳዊት የይሖዋን ምሕረት ለማስረዳት ዘይቤያዊ አነጋገር ተጠቅሟል።
-
103:11
በከዋክብት በተሞላው ሰማይና በምድር መካከል ያለውን ርቀት ሙሉ በሙሉ መረዳት እንደማንችለው ሁሉ የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነም መረዳት አንችልም
-
103:12
የፀሐይ መውጫ ከፀሐይ መግቢያ እንደሚርቅ ሁሉ ይሖዋ ኃጢአታችንን እኛ ልናስበው ከምንችለው በላይ ከእኛ ያርቀዋል
-
103:13
አንድ አባት ችግር ላይ ለወደቀ ልጁ እንደሚራራ ሁሉ ይሖዋም በሠሩት ኃጢአት ምክንያት ለተደቆሱ ንስሐ የገቡ ሰዎች ምሕረት ያሳያል