የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 3 ገጽ 11
  • አምላክን የሚታዘዙ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን የሚታዘዙ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1. አምላክን መታዘዝ ጥበበኛ ያደርገናል
  • 2. አምላክን መታዘዝ ደስተኛ ያደርገናል
  • የአምላክ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • “አምላክን መውደድ” ሲባል ምን ማለት ነው?
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • “ለመታዘዝ ዝግጁ” ነህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 3 ገጽ 11
አንድ ቤተሰብ በደስታ አብረው ጊዜ ሲያሳልፉ። እናትየው ከአንደኛዋ ሴት ልጃቸው ጋር ኩሽና ውስጥ ምግብ እያዘጋጀች ነው። ሳሎን ውስጥ አባትየውና ሌላኛዋ ሴት ልጃቸው የፎቶግራፍ አልበም እየተመለከቱ ነው።

የአምላክን ትእዛዛት መጠበቃችን እውነተኛ ደስታ ያስገኝልናል

አምላክን የሚታዘዙ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች

የአምላክን ትእዛዛት የምንፈጽም ከሆነ የእሱን በረከት እንደምናገኝ ነቢዩ ሙሴ ተናግሯል። (ዘዳግም 10:13፤ 11:27) አምላክን የምንታዘዘው እንዳይቀጣን ፈርተን አይደለም። አምላክን የምንታዘዘው ግሩም በሆኑ ባሕርያቱ የተነሳ ስለምንወደውና እሱን የሚያሳዝን ነገር ማድረግ ስለማንፈልግ ነው። “አምላክን መውደድ ማለት ትእዛዛቱን መጠበቅ ማለት ነው።”—1 ዮሐንስ 5:3

ይሁንና አምላክን መታዘዝ በረከት የሚያስገኝልን እንዴት ነው? እስቲ ሁለት መንገዶችን እንመልከት።

1. አምላክን መታዘዝ ጥበበኛ ያደርገናል

“የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ፣ ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህ እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።”—ኢሳይያስ 48:17

ፈጣሪያችን ይሖዋ አምላክ በሚገባ ያውቀናል፤ የሚያስፈልገንን መመሪያም ይሰጠናል። አምላክ ባስተማረን ነገር ላይ የተመሠረተ ጥሩ ውሳኔ ማድረግ ከፈለግን፣ አምላክ ስለሚጠብቅብን ነገር ከቅዱሳን መጻሕፍት መማርና የተማርነውን ነገር ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል።

2. አምላክን መታዘዝ ደስተኛ ያደርገናል

“ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!”—ሉቃስ 11:28

በዛሬው ጊዜ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የአምላክን ቃል በመታዘዛቸው እውነተኛ ደስታ አግኝተዋል። በስፔን የሚኖርን አንድ ሰው እንደ ምሳሌ እንውሰድ፤ ይህ ሰው ግልፍተኛ የነበረ ሲሆን ሚስቱን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችን የሚይዘው አክብሮት በጎደለው መንገድ ነበር። አንድ ቀን፣ ነቢዩ ሙሴ በጻፈው መጽሐፍ ላይ የያዕቆብ ልጅ የሆነው ዮሴፍ ስላሳየው ግሩም ባሕርይ አነበበ። ዮሴፍ በባርነት ተሽጦ በግፍ ቢታሰርም ልዝብ፣ ሰላማዊና ይቅር ባይ ሰው ነበር። (ዘፍጥረት ምዕራፍ 37-45) በስፔን የሚኖረው ሰው እንዲህ ብሏል፦ “ዮሴፍ ስለተወው ምሳሌ ማሰቤ ልዝብና ደግ እንድሆን እንዲሁም ራሴን እንድገዛ አነሳሳኝ። በዚህም የተነሳ አሁን በሕይወቴ ደስተኛ መሆን ችያለሁ።”

ቅዱሳን መጻሕፍት ከሌሎች ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት ተጨማሪ መመሪያዎች ይሰጡናል። በቀጣዩ ርዕስ ላይ ስለዚህ ጉዳይ ይበልጥ እንመለከታለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ