ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኤርምያስ 22-24
ይሖዋን የሚያውቅ ልብ አለህ?
ይሖዋ ሰዎችን ከበለስ ጋር አመሳስሏቸዋል
ወደ ባቢሎን በግዞት ከተወሰዱት አይሁዳውያን መካከል ታማኝ የሆኑት በጥሩ በለስ ተመስለዋል
ታማኝ ያልሆነው ንጉሥ ሴዴቅያስና መጥፎ የሆነውን ነገር ያደርጉ የነበሩ ሌሎች አይሁዳውያን በመጥፎ በለስ ተመስለዋል
ይሖዋን የሚያውቅ ልብ ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?
የይሖዋን ቃል ካጠናንና ቃሉን በተግባር ላይ ካዋልን ይሖዋ እሱን የሚያውቅ ልብ ይሰጠናል
ልባችንን በሐቀኝነት በመመርመር ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና አደጋ ላይ የሚጥሉ ዝንባሌዎችንና ምኞቶችን ነቅለን መጣል ይኖርብናል