ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሰቆቃወ ኤርምያስ 1-5
በትዕግሥት መጠባበቅ ለመጽናት ይረዳናል
ኤርምያስ ከባድ መከራ ቢደርስበትም አዎንታዊ አመለካከት ይዞ እንዲጸና የረዳው ምንድን ነው?
ኤርምያስ፣ ይሖዋ ከሕዝቡ መካከል ንስሐ የገቡትን ለመርዳት ‘እንደሚያጎነብስ’ እና ካሉበት አሳዛኝ ሁኔታ እንደሚያወጣቸው እርግጠኛ ነበር
ኤርምያስ “በልጅነቱ ቀንበር [መሸከምን]” ተምሯል። አንድ ሰው በወጣትነቱ የእምነት ፈተናዎችን በጽናት መወጣቱ፣ ከጊዜ በኋላ በሕይወቱ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት ይረዳዋል