ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሕዝቅኤል 1-5
ሕዝቅኤል የአምላክን መልእክት ማወጅ ያስደስተው ነበር
ሕዝቅኤል፣ ይሖዋ አንድ ጥቅልል ሲሰጠው በራእይ ተመልክቷል፤ ከዚያም ጥቅልሉን እንዲበላው ይሖዋ ነግሮታል። የዚህ ራእይ ትርጉም ምንድን ነው?
ሕዝቅኤል የአምላክ መልእክት ወደ ውስጡ ጠልቆ እንዲገባ ማድረግ ነበረበት። በጥቅልሉ ላይ በተጻፈው መልእክት ላይ ማሰላሰሉ ስሜቱ በጥልቅ እንዲነካ የሚያደርግ ሲሆን ይህም መልእክቱን እንዲናገር ያነሳሳዋል
ሕዝቅኤል ጥቅልሉ የጣፈጠው ለተሰጠው የሥራ ምድብ አዎንታዊ አመለካከት ስለነበረው ነው