ክርስቲያናዊ ሕይወት
ራስህን ይቅር ትላለህ?
ይሖዋ ከዚህ ቀደም የሠራናቸውን ስህተቶች ይቅር ቢለንም እኛ ግን ራሳችንን ይቅር ማለት ሊከብደን ይችላል። “ምንጊዜም ለይሖዋ ታማኝ ሁኑ!” በተባለው የ2016 የክልል ስብሰባ ላይ ይህን ጉዳይ የሚያብራራ ንግግርና ቪዲዮ ቀርቦ ነበር። JW Library ላይ የሚገኘውን ይህን ቪዲዮ በድጋሚ ከተመለከታችሁ በኋላ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሞክሩ፦
ሶንያ ተወግዳ የቆየችው ለምን ያህል ጊዜ ነበር?
የጉባኤ ሽማግሌዎች ለሶንያ የትኛውን ጥቅስ አሳዩአት? ይህስ የጠቀማት እንዴት ነው?
ሶንያ ከውገዳ ስትመለስ ጉባኤው ምን ዓይነት አቀባበል አደረገላት?
ሶንያ ከየትኛው ስሜት ጋር መታገል አስፈልጓታል? አባቷ በዚህ ረገድ የረዳት እንዴት ነው?