ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሕዝቅኤል 24-27
በጢሮስ ላይ የተነገረው ትንቢት በይሖዋ ቃል ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል
በወረቀት የሚታተመው
የሕዝቅኤል መጽሐፍ የጢሮስን ጥፋት አስመልክቶ ዝርዝር ጉዳዮችን በትንቢት ተናግሯል።
ከ607 ዓ.ዓ. በኋላ የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ በየብስ ላይ ትገኝ የነበረችውን የጢሮስ ከተማ ያጠፋው ማን ነው?
በ332 ዓ.ዓ. በየብስ ላይ ያለውን የጢሮስ ከተማ ክፍል ፍርስራሽ ባሕሩ ውስጥ በመደልደል ደሴት ላይ ወደሚገኘው የከተማዋ ክፍል የሚወስድ መተላለፊያ ከሠራ በኋላ በደሴት ላይ ያለውን የከተማዋን ክፍል ያጠፋው ማን ነው?