ክርስቲያናዊ ሕይወት
አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—ትሕትና
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ትሕትና ከይሖዋ ጋር የቅርብ ዝምድና ለመመሥረት ያስችላል።—መዝ 138:6
ትሕትና ከሌሎች ሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን ይረዳናል።—ፊልጵ 2:3, 4
ኩራት ለውድቀት ይዳርጋል።—ምሳሌ 16:18፤ ሕዝ 28:17
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ሌሎች ዝቅ አድርገው የሚመለከቷቸውን ሥራዎች ለመሥራት ፈቃደኛ ሁን።—ማቴ 20:25-27
የተለየ ችሎታ ወይም መብት ያለህ መሆኑ ኩራት እንዲያሳድርብህ አትፍቀድ።—ሮም 12:3
ከአሁኑ የበለጠ ትሑት መሆን የምችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
ታማኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን አስወግዱ—ኩራት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ምክር ሲሰጠን የምንሰጠው ምላሽ ስለ ዝንባሌያችን ምን ይጠቁማል?
ጸሎት፣ ትሕትና ለማዳበር የሚረዳን እንዴት ነው?
ትሕትና ማሳየት የሚቻልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?