ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዳንኤል 10-12
ይሖዋ ነገሥታት ወደፊት ስለሚጠብቃቸው ነገር አስቀድሞ ተናግሯል
በፋርስ ምድር አራት ነገሥታት ይነሳሉ። አራተኛው ንጉሥ “ሁሉንም ነገር በግሪክ መንግሥት ላይ ያስነሳል።”
ታላቁ ቂሮስ
ዳግማዊ ካምቢሰስ
ቀዳማዊ ዳርዮስ
ቀዳማዊ ጠረክሲስ (አስቴርን ያገባው ንጉሥ አሐሽዌሮስ እንደሆነ ይታመናል)
አንድ ኃያል የግሪክ ንጉሥ የሚነሳ ሲሆን ይህ ንጉሥ ሰፊ ግዛት ይቆጣጠራል።
ታላቁ እስክንድር
አራቱ የእስክንድር ጄኔራሎች የግሪክን ግዛት ይከፋፈሉታል።
ካሳንደር
ላይሲመከስ
ቀዳማዊ ሰሉከስ
ቀዳማዊ ቶሌሚ