ስህተት በምንሠራበት ጊዜ ይሖዋ፣ መስተካከል እንደማንችል አድርጎ በማሰብ ተስፋ እንደማይቆርጥብን የዮናስ ታሪክ ያሳያል። ሆኖም ይሖዋ ከስህተታችን እንድንማርና አስፈላጊውን ለውጥ እንድናደርግ ይጠብቅብናል።
ዮናስ 1:3
ዮናስ ከይሖዋ ተልእኮ በተሰጠው ወቅት ምን ስህተት ሠርቷል?
ዮናስ 2:1-10
ዮናስ ምን በማለት ጸልዮ ነበር? ይሖዋስ ምን ምላሽ ሰጥቶታል?
ዮናስ 3:1-3
ዮናስ ከስህተቱ እንደተማረ ያሳየው እንዴት ነው?