ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሶፎንያስ 1–ሐጌ 2
የቁጣው ቀን ሳይመጣ ይሖዋን ፈልጉ
ይሖዋ በቁጣው ቀን እንዲሰውረን ከፈለግን ራሳችንን ለእሱ መወሰናችን ብቻ በቂ አይደለም። ሶፎንያስ ለእስራኤላውያን የሰጠውን መመሪያ መከተል ይኖርብናል።
ይሖዋን ፈልጉ፦ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር ከይሖዋ ጋር የተቀራረበ ዝምድና ይዞ መኖር
ጽድቅን ፈልጉ፦ በጽድቅ ላይ የተመሠረቱትን የይሖዋን ሕጎች ማክበር
የዋህነትን ፈልጉ፦ ለአምላክ ፈቃድ በትሕትና መገዛት እንዲሁም የእሱን ተግሣጽ መቀበል
ይሖዋን፣ ጽድቅንና ትሕትናን ይበልጥ መፈለግ የምችለው እንዴት ነው?