የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb18 መጋቢት ገጽ 7
  • “ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ነቅታችሁ ትጠብቃላችሁ?’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ንቁ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ደናግሉ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ማስጠንቀቂያዎቹን ልብ እያልክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ስለ “ነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” የተገኘው የእውቀት ብርሃን
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
mwb18 መጋቢት ገጽ 7
ኢየሱስ ስለ አሥሩ ደናግል የተናገረው ምሳሌ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 25

“ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ”

25:1-12

ኢየሱስ ስለ አሥሩ ደናግል የሚናገረውን ምሳሌ የጠቀሰው ለቅቡዓን ተከታዮቹ ቢሆንም መሠረታዊ ሐሳቡ ለሁሉም ክርስቲያኖች ይሠራል። (w15 3/15 12-16) “ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” በማለት ተናግሯል። (ማቴ 25:13) ኢየሱስ የተናገረውን ይህን ምሳሌ ማብራራት ትችላለህ?

  • ሙሽራው (ቁጥር 1)—ኢየሱስ

  • ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩት ልባሞቹ ደናግል (ቁጥር 2)—የተሰጣቸውን ሥራ በታማኝነት ለመወጣት ዝግጁ የሆኑትና እስከ መጨረሻው ድረስ እንደ ብርሃን አብሪዎች የሚያበሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች (ፊልጵ 2:15)

  • “ሙሽራው እየመጣ ነው” የሚለው ጫጫታ (ቁጥር 6)—የኢየሱስን መገኘት የሚያሳውቁ ማስረጃዎች

  • ሞኞቹ ደናግል (ቁጥር 8)—ሙሽራውን ለመቀበል ቢወጡም እስከ መጨረሻው ንቁዎች ያልሆኑና ንጹሕ አቋማቸውን ያልጠበቁ ቅቡዓን ክርስቲያኖች

  • ልባሞቹ ደናግል ዘይታቸውን ለመስጠት ፈቃደኞች አለመሆናቸው (ቁጥር 9)—የመጨረሻው ማኅተም ከተደረገ በኋላ ታማኞቹ ቅቡዓን፣ ታማኝነታቸውን ያጓደሉትን ቅቡዓን መርዳት አይችሉም፤ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግ የሚችሉበት ጊዜ አልፏል

  • ‘ሙሽራው መድረሱ’ (ቁጥር 10)—ወደ ታላቁ መከራ ማብቂያ አካባቢ ኢየሱስ ፍርድ ለመስጠት ይመጣል

  • ልባሞቹ ደናግል ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ድግስ መግባታቸው፤ ከዚያም በሩ መዘጋቱ (ቁጥር 10)—ኢየሱስ ታማኝ ቅቡዓኑን ወደ ሰማይ ይሰበስባቸዋል፤ ታማኝ ያልሆኑት ቅቡዓን ግን ሰማያዊ ሽልማታቸውን ያጣሉ

ይህ ምሳሌ በርካታ ቅቡዓን ታማኝነታቸውን እንደሚያጓድሉና በዚህም ምክንያት በሌሎች እንደሚተኩ የሚጠቁም አይደለም። ከዚህ ይልቅ ምሳሌው እያንዳንዱ ቅቡዕ ክርስቲያን ዝግጁና ንቁ ለመሆን አሊያም በሞኝነት ታማኝነቱን ለማጉደል ሊመርጥ እንደሚችል የሚያሳይ ማስጠንቀቂያ ነው። ኢየሱስ “ዝግጁ ሁኑ” የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል። (ማቴ 24:44) ተስፋችን ምንም ይሁን ምን ኢየሱስ ሁላችንም ልባችንን ዝግጁ በማድረግ በታማኝነት እንድናገለግል እንዲሁም ንቁ ሆነን እንድንጠብቅ ይፈልግብናል።

ንቁ መሆኔን እያሳየሁ ያለሁት እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ