ፋሲካ ለመታሰቢያው በዓል ጥላ ባይሆንም አንዳንድ የፋሲካ በዓል ገጽታዎች ለእኛ የሚጠቅም ትምህርት ይዘዋል። ለምሳሌ ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስን “የፋሲካችን በግ” በማለት ጠርቶታል። (1ቆሮ 5:7) በበር መቃን ላይ የተቀባው የበግ ደም ሕይወት እንዳዳነ ሁሉ የኢየሱስም ደም ሕይወት ያድናል። (ዘፀ 12:12, 13) በተጨማሪም የፋሲካ በግ አጥንቱ አይሰበርም ነበር። በተመሳሳይም በወቅቱ የተሰቀለን ሰው አጥንት የመስበር ልማድ የነበረ ቢሆንም ከኢየሱስ አጥንቶች መካከል አንዱም አልተሰበረም።—ዘፀ 12:46፤ ዮሐ 19:31-33, 36